የጦር መሳሪያቸውን ያስመዘገቡ ሰዎች አስገዳጅ መመሪያ ተላለፈባቸው
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የኢህአዴግ መንግስት የግል የጦር መሳሪያ የያዙ ዜጎች ህጋዊ ፈቃድ ከመንግስት በመውሰድ፣ የጦር መሳሪያቸውን እንደንብረት እንዲይዙ አዲስ መመሪያ በማውጣት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች መሳሪያዎቻቸውን እያስመዘገቡ ፈቃድ ውሰደዋል። ይሁን እንጅ ገንዘብ...
View Articleኢሳት ቴሌቪዥን ስርጭቱን በአዲስ ሳተላይት እንደገና ጀመረ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ ወር በላይ ተቋርጦ የነበረው የኢሳት ቴሌቪዥን አገልግሎት በአዲስ ሳተለይት ስራ ጀምሯል። ከኢህአዴግ መንግስት በሚደርስበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ ስርጭቱ በተደጋጋሚ ሲቋረጥ የቆየው ኢሳት ቴሌቪዥን ኤ ኤም 44 በሚባል ሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭቱን ከትናንት...
View Articleአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ካሳ ተከፍሏቸው ከእስር እንዲፈቱ ተጠየቀ
ኢሳት ዜና (ሰኔ 28 2007 አም) የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የአንድ አመት የእስር ቤት ቆይታ ሲከታተል የቆየው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የካሳ ክፍያ በመፈጸም አቶ አንዳርጋቸውን በአስችኳይ እንዲፈታ ማሳሰቡን አለማቀፍ ሚዲያዎች ዘገቡ። ባለስምንት ገጽ ውሳኔውን በተባበሩት መንግስታት...
View Articleየሸህ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ ንብረት ከሆነው ከሚድሮክ ጎልድ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መንግስት ማጣቱን የፌዴራል...
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ግን ማስተባበያውን አጣጥለውታል። የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት፣ የማዕድን ሚኒስቴር የሼክ መሐመድ አል አሙዲ የወርቅ ልማት ኩባንያ ከሆነው ሚድሮክ ጐልድ በሕግ የተወሰነውን ገቢ...
View Articleየኢህአዴግ መንግስት የስለላ ስራ ለሚሰራለት ለአንድ ኩባንያ ብቻ 1 ሚሊዮን ዶላር ከፈለ
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጣሊያን ውስጥ የሚገኘውና ሃኪንግ ቲም ” hacking team” በመባል የሚታወቀው ለደህንነትና ለስለላ የሚያስፈልጉ የኮምፒዩተር ሶፍት ዌሮችን የሚሸጠው ድርጅት፣ የራሱ መረጃዎች በሌሎች ሃይሎች የተዘረፈ ሲሆን፣ እስካሁን ይፋ በሆኑት መረጃዎችን ቢንያም ተወልደ...
View Articleበዘይሴ ቀበሌ አንድ ግለሰብ 4 የመንግስት ሹሞችን ገደለ
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን ዘይሴ በሚባል ቀበሌ፣ ከ4 ቀናት በፊት አንድ ግለሰብ ከመሬት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት፣ የመሬት አስተዳደር ሃላፊውን ጨምሮ ሌሎች 3 የወረዳ ሹሞችን ገድሏል። ግለሰቡ በ2007 ምርጫ የተቃዋሚ አባሎችን ደግፈሃል በሚል...
View Articleየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ካውንስል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጠየቀ
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋርድያን እንደዘገበው የተመድ የሰብአዊ መብቶች ካውንስል፣ ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ በአስቸኳይ አስፈላጊውን ካሳ በመክፈል እንድትለቃቸው ጠይቋል። የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተለው የተመድ የሰብአዊ መብት ካውንስል በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በጭካኔ...
View Articleከፍተኛው ፍርድ ቤት እነ አቶ አቡበክር አህመድን ጥፋተኞች ናቸው ሲል ወሰነ
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 18 የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በሙሉ ጥፋተኞች ሲባሉ የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤት ለሃምሌ 27 ቀጠሮ ሰጠ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ወንጀል ችሎት በ አቶ አቡበከር አህመድ፣...
View Articleአረብ አገር ትሄዳላችሁ ተብለው የተሰበሰቡ ወጣቶች በግድ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መጓዛቸው ተሰማ
ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት 3 ቀናት ወደ አረብ አገር እንወስዳችሁዋለን በሚል የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፕ ለማጓጓዝ መሞከሩን ወጣቶች ተናግረዋል። ወጣቶች እንዳሉት ወደ አረብ አገራት ትሄዳላችሁ ተብለው ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም...
View Articleየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃወሙት
ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለማቀፍ ታላላቅ የመገኛኛ ብዙሃን አውታሮች መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጐብኘት ውጥን አሜሪካ አምባገነን መንግስታትን ከመደገፍ የመነጨ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡...
View Articleበሶማሊያ ፑትላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ውስጥ 82 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ
ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ፑትላንድ ራስ ገዝ ዋና ከተማ ጋሮው በከባድ መኪና ድንበር አቋርጠው ሲጓዙ የነበሩትን ሰማንያ ሁለት ሕገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና የተሽከርካሪውን ሹፌር አብሮ መያዙን የፑትላንድ ፀጥታ ሹም ኃላፊ ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከአስር ሽህ በላይ...
View Articleየኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ
ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዛሬ ለፓርላማ አባሎች እንደተናገሩት የኤርትራ መንግስት አካባቢውን የማተራማስ አጀንዳውን ካላቆመ ፣ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። አቶ ሃይለማርያም ሻእቢያ ኢትዮጵያና ጅቡቲን ለማተራመስ እየሰራ ነው ሲሉ ከሰዋል።...
View Articleየዋጋ ግሽበቱ በከፍተኛ ደረጃ ጨመረ
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ወርሃዊ የዋጋ መረጃው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም የሸቀጦች ዋጋ ካለፈው ጋር ሲነጻጸር መጨመሩን ይፋ አደረገ፡፡ በኤጀንሲው መረጃ መሰረት በግንቦት ወር 9 ነጥብ 4 በመቶ የነበረው የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ወደ 10 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ...
View Articleበእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ በተከሰሱት ላይ ብይን ሳይሰጥ ቀረ
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮች የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሺበሽን ጨምሮ 10 ተከሳሾች ሐምሌ 1/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ...
View Articleየሚኒስትር ሬድዋን አማካሪ መኮብለላቸው ተሰማ
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አማካሪ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አዱኛ አሞኘ ከሀገር መኮብለላቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል። አቶ አንዱዓለም በ2007 ምርጫ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለቅስቀሳ የሚሆኑ ሰነዶችን እንዲያዘጋጁ ከመንግስት ኮሚኒኬሽን...
View Articleበአዲስ አበባ ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ እየተካሄደ ነው
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞችም እየታፈሱ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአዲስ አበባ የተቃዋሚ ሃይሎች ሰርገው ሳይገቡ ገብተዋል የሚል...
View Articleከ24 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የጦር መሳሪያ ሊገዛ ነው
ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ፣ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ የጦር አዛዦች በተገኙበት የወታደራዊ ጥቅል አቋማቸውን አቅርበዋል። በከፍተኛ ሚስጢር በተካሄደው ስብሰባ ላይ ፣ ጄ/ል ሳሞራ ” ጦራችን ከጊዜው ጋር እየዘመነ አይደለም፣...
View Articleበኢነሳና በሃኪንግ ቲም መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር መረጃዎች አጋለጡ
ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃኪንግ ቲም ለተባለ ኩባንያ 1 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የስለላ መሳሪያዎችን የገዛው በአብዛኛው በህወሃት አባላት የሚመራው የደህንነት መስሪያ ቤት፣ ከኩባንያው ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ እንደነበርና ውዝግቡ ሳይፈታ መረጃው ይፋ መሆኑን ለህዝብ ይፋ ከሆነው መረጃ...
View Articleከባድ መሳሪያ የታጠቁ ከሶስት ሽህ በላይ የኢህአዴግ ወታደሮች አልሸባብን ለመውጋት በሚል ወደ ጌዶ ዘመቱ
ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘ ደይሊ ኔሽን የኢትዮጵያ ሰራዊት በታንክና በከባድ መሳሪያ ታግዞ በከተማዋ ውስጥ መታየቱን የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ሰራዊቱ የተንቀሳቀሰው ከኢትዮጵያ መሆኑንም የገለጸው ጋዜጣው፣አልሸባብ የሚቆጣጠረውን የባርደሬ ግዛት ለማስለቀቅ ሳያቅድ እንዳልቀረ...
View Articleየምእራብ አርማጭሆ ወረዳ የሴቶች ሃላፊ ታሰረች
ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት የኢህአዴግ አባል የሆነችው ወ/ሮ አስቴር ስዩም የወረዳው የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ፣ በቅርቡ ደግሞ በጎንደር ከተማ የጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅት ሃላፊ በመሆን ስትሰራ ቆይታለች። አስቴር የኢህአዴግ አባል ብትሆንም ከበላይ አካል የሚመጣውን ትእዛዝ ሁሉ...
View Article