የኢህአዴግ አመራሮች ቀደም ብለው የነበሩትን መንግስታት በማንኳሰስ የራሳቸውን ስራ ማሞገስ በየመድረኩ ተጠናክሮ መቀጠሉ...
ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ በአዳማ ከተማ ለጋዜጠኞች ባዘጋጀው ሴሚናር ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ተወክለው በስብሰባው በመገኘት ንግግር ያደረጉት አቶ ናስር ለገሰ ባቀረቡት የኢትዮጵያ ሰፖርት ታሪክ ንግግራቸው የቀደሙት መንግስታትን ስራ በማጣጣል...
View Articleየህዝብ ግንኙነት ካድሬዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ሊዘምቱ ነው
ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አሰልጥኖ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት በህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት ለመደባቸው ካድሬዎች የሁለት ቀናት የማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ስልጠና በመስጠት በተለይ በግንቦት ወር ከሚካሄደው ሀገር...
View Articleበአፋር የፌደራል ፖሊሶች አንድ ሰው ገድለው ሌላ ሰው አቆሰሉ
ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአሚባራ በአፋርና በኢሳ መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው ገድለው ሌላ የአፋር ተወላጅን ደግሞ አቁስለዋል። በአካባቢው ውጥረቱ አሁንም መቀጠሉን ገልጸዋል። በሌላ በኩል...
View Articleየፌደራል ኦዲተር ባለፉት ሶስት አመታት እርምጃ ያልተወሰደባቸውን መስሪያ ቤቶችን ስም ለተወካዮች ምክር ቤት አቀረበ
ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የመንግስት ሃብትና ንብረትን ላለፉት ሶስት አመታት የህዝብን ሃብት በህገወጥ መንገድ በማባከን ሪኮርድ የሰበሩ መንግስታዊ ተቋማት እርምጃ እንዳልተወሰደባቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ያዘጋጀው ሪፖርት ያመለክታል። የተወካዮች ምክር ቤት...
View Articleበኦሮሚያ ና በአማራ ከልሎች የግሪሳ ወፍ መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግሪሳ ወፍ በሰብል ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከልና ብሎም ለማጥፋት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ዛሬ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት በፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ...
View Articleበላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ላይ እተከሰተ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የቤተ ክርስቲያኗ አመራሮች...
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅዱስ ላሊበላ ገዳም የሰው ሃይል አስተዳደር የሆኑት ቀኝ ጌታ በላይ አናውጥ ከልዩ ልዩ አካባቢ ለመጡ ጋዜጠኞችና ጎብኝዎች እንደ ገለጹት ገዳሙ በዝናብና ጸሃይ እየደረሰበት ያለው ጉዳት ቅርሶቹን በአስከፊ ደረጃ እያፈረሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቅርሶቹን...
View Articleየኢትዮጵያ መንግስት በወንጀልና በሽብር የሚጠረጥራቸውን ሰዎች በሱዳን ግዛት ውስጥ በቀላሉ ለመያዝና ንብረቶቻቸውን ለመውረስ...
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቂቅ አዋጁ ሁለቱ ሀገራት በወንጀል የጠረጠሩትን ዜጎች በመያዝ ለፈላጊው ሀገር አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችላቸው ነው፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተመለከተው በዚህ ትብብር መሰረት መረጃው በሚፈለገው ሀገር አግባብነት ባለው ተቋም ህጋዊ መጠየቂያ ደብዳቤ መሰረት...
View Articleበአዲስ አበባ ውስጥ የሚታየውን የሃይል እጥረት ለመቅርፍ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎች ገለጹ
ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንደይጠቀስ የፈለጉ በኢትዮጵያ መብራት ሃይል ስር የሚሰሩ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በአዲስ አበባ የሚታየው የመብራት ሃይል መቆራረጥና መጥፋት ነዋሪውን ለስቃይ እየዳረገው ነው። እናቶች የአቦኩትን ሊጥ ለመጋገር ሲዘጋጁ መብራት ይጠፋና ሊጡ...
View Articleከ50 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊጓዙ ሲሉ መያዛቸውን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ መንገድ መግባታቸውን የገለጸው የኬንያ ፖሊስ፣ 54ቱ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቤት ውስጥ ታጭቀው ተገኝተዋል ብሎአል። ሰዎቹን ወደ ኬንያ ያመታው ግለሰብ መጥፋቱንም ፖሊስ ገልጿል። ኢትዮጵያውያንን ወደ ደቡብ አፍሪካ ማሻገር ትልቁ የገቢ...
View Articleበኢትዮጵያ ፖሊዮ አሁንም ህዝቡን እያጠቃ ነው ሲል ዩኒሴፍ አስታወቀ
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2013 በነበረው ጊዜ ከፖሊዮ ነጻ አገር ተብላ የተወደሰች ቢሆንም፣ ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ በሽታው እንደገና መታየቱን ዩኒሴፍ አስታውቋል። ባለፈው አመት 10 የፖሊዮ ተጠቂዎች መታየታቸውን የገለጸው ዩኒሴፍ፣...
View Articleበአዲስ አበባ በሚካሄደው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ሰልጣኞች ለምናነሳቸው ጥያቄዎች መልስ አላገኘንም አሉ
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና መድረክ ከወረዳ ጽ/ቤት እስከ ማዕከል ቢሮዎች የሚገኙ ሰራተኞች እና የፌደራል መ/ቤት ሰራተኞች ከማክሰኞ ጥቅምት 3 ቀን እስከ ቅዳሜ ጥቅምት 14/2007 ዓ.ም ለተከታታይ 11 ቀን የፖለቲካ ስልጠና የተሰጠ...
View Articleበቦሌ አካባቢ የሚደረገው ፍተሻ እንዳስመረራቸው ነዋሪዎች ገለጹ
ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ አባላት አሸባሪዎች ገብተዋል በማለት የሚያደርጉት ተደጋጋሚ ፍተሻ እንዳስመረራቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የተጠናከረ ፍተሻ ሰኞ እለት ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት በቦሌ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች፣...
View Articleጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስራት ተቀጣ
ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት፣ ግዙፍ ባልሆነ ማሰናዳትና የመንግስትን ስም በማጥፋት ወንጀል ተከሶ ሲከራከር ከቆየ በሁዋላ፣ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 9ኛ ወንጀል ችሎት በ3 አመት ጽኑ...
View Articleበጋምቤላ የሚታየው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጨምሯል
ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላና በደቡብ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በሚኖሩ በመዠንገርና በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ፣ ቁጥራቸው 50 የሚጠጋ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያና የአካባቢው ሚሊሺያዎች ከተገደሉ በሁዋላ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት...
View Articleበስብሰባ ምክንያት በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር የሚገኙ መ/ቤቶች ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ አይደለም ተባለ
ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመስተዳድሩ ኃላፊዎች በፖለቲካ ስልጠና እና በግምገማ መወጠራቸው ውሳኔ በወቅቱና በአግባቡ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ ነዋሪዎች አገልግሎት ለማግኘት ተቸግረዋል። በእያንዳንዱ የሴክተር መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙጥ ኃላፊዎች የሉም ያለው ዘጋቢያችን፣ ውሳኔዎችን...
View Articleየአለም ባንክ መሪ ለዶክተሮች ጥሪ አቀረቡ
ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ የሚገኙት የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጂም ዮንግ ኪም በምእራብ አፍሪካ የሚታየውን የኢቦላ ወረርሽን ለመዋጋት ቢያንስ 5 ሺ ዶክተሮች የሚያስፈልጉ በመሆኑ ፣ ዶክተሮች ና የጤና ባለሙያዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃዳቸውን እንዲገልጹ ተማጽነዋል።...
View Articleበቦሌ የድምጻችን ይሰማ መፈክሮች በሌሊት ተጽፈው አደሩ
ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊሶች ሰኞ እለት አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል በማለት በቦሌ አካባቢ ፍትሻ ባደረጉ ምሽት መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳውን ጥያቄ እንዲመልስ የሚጠይቁ መፍክሮች በቦሌ ወሎ ሰፈርና በደንበል አካባቢዎች ተጽፈው አደረዋል። መብትን መጠየቅ ሽብር...
View Articleበርካታ ቁጥር ያላቸው ኦሮሞዎች እየታሰሩ እየተገደሉና እየተዋከቡ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ
ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2011 እስካሁን ያለውን ሁኔታ አጥንቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ፣ ከ5 ሺ ያላነሱ ኦሮሞች በእስር ላይ ይገኛሉ። ጥናቱን ያጠኑት የአምነስቲ የኢትዮጵያ ክፍል ሃላፊ ክሌር ቤስተን መንግስት አገሪቱን...
View Articleየወ/ሮ አዜብ መስፍን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መዳከሙ ተሰማ
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለቤታቸውን በድንገተኛ ሞት ከማጣታቸው በፊት የፓርላማ አባል የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በራሳቸው ፍቃድ ፓርላማውን ከመልቀቃቸውም በተጨማሪ በድርጅታዊ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እየተዳከመ መምጣቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ ባለፈው አንድ...
View Articleአዲስ አበባ ውስጥ ሌሊት የሚለጠፉ ወረቀቶችን ተከትሎ ውጥረት መንገሱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ፖሉ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን ነገረ...
View Article