አቶ አንዳርጋቸው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የሚያሰሙት ቁጣ እንደቀጠለ ነው
ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፈው በሰብአዊ መብት ጥሰትና ህዝብን በማሰቃየት በአለም የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ዘወትር ለሚወገዘው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው መስጠታቸው ያበሳጫቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ...
View Articleአንድነት ፓርቲ የታሰሩት የአመራር አካሎች በአስቸኳይ እንዲለቀቅ ጠየቀ
ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች የአንድነት ፓርቲን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነውን ወጣት ሃብታሙ አያሌውን ፣ የፓርቲውን የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን የሽዋስ አሰፋን እንዲሁም...
View Articleየአቶ አንዳርጋቸውን እስር ተከትሎ ከአገር ቤት በስልክ የሚሰጠው አስተያየት እንደቀጠለ ነው
ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአገር ቤት በተከታታይ የሚደወሉ ስልኮችን ለማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት እየገለጸ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች አቶ ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውን ከበሬታ የሚገልጹና ኢህአዴግን በሃይል ለማንበርከክ የሚታገሉትን ቡድኖች ለመቀላቀል እንዴት እንደሚቻል የሚጠይቁ...
View Articleኢህአዴግ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በቴሌቪዥን ማቅረቡን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው
ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገር ውስጥ እና በውጭ ከፍተኛ ጫና የተፈጠረበት የኢህአዴግ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ምስል በቴሌቪዥን ካቀረበ በሁዋላ የተለያዩ አስተያየቶች በማህበራዊ የመገናኛ መንገዶችና በስልክ እየተሰጡ ነው።አብዛኛው አስተያየት ሰጪ በቴሌቪዥን የቀረበው ምስልና ድምጽ መቆራረጡን...
View Articleየህወሃቱ የስለላ ሃለፊ ታሰረ
ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት አባል የሆነውና በሶማሊ ክልል የደህንነት ሃለፊ በመሆን ሲሰራ የነበረው መቶ አለቃ አወጣሃኝ በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ እንዲታሰር ተደርጓል። ግለሰቡ በምን ምክንያት እንደታሰረ ለማወቅ ባይቻልም፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት እና በህወሃት የጸጥታ ሰራተኞች መካከል...
View Articleታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች በማእከላዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታወቀ
ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌደራል ፖሊሶች እየተደበደበ ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስዶ የነበረው ታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ ማእከላዊ እስር ቤት መታሰሩ ታውቋል። የአብረሃ መኖረያ ቤት በፖሊሶች እንደተፈተሸም ለማወቅ ተችሎአል። የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ...
View Articleአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን መግለጽ ቀጥለዋል
ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ሰሞኑን ከአገር ቤት በሚደወሉ ስለኮች የተጨናነቀ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች የኢህአዴግን ስርአት በሃይል ለመፋለም መቁረጣቸውን የሚገልጹ ናቸው። እንደሰሞኑ ሁሉ ” መንገዱን አሳዩን እና አቶ አንዳርጋቸው ይዘውት የተነሱትን ራእይ እውን እናድርገው ” የሚሉ ወጣቶች...
View Articleአምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሚፈጸመው እስር እንዳሳሰበው ገለጸ
ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ተጠናክሮ የቀጠለው እስር በአገሪቱ ውስጥ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይኖር ያደረገ ነው ብሎአል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበት ሁኔታ አለመታወቁንና ለከፍተኛ ስቃይ ሊዳረጉ እንደሚችሉ መግለጹንና አለማቀፉ ማህበረሰብ...
View Articleሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አሰሙ
ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በረመዳን ጾም ተጠናክሮ የቀጠለው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ፣ ዛሬም በበኒ መስጂድ እጅግ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ” የእምነት ነጻነታችን ይከበር፣ ለከፈልነው መስዋትነት ተመጣጣኝ ውጤት እናመጣለን” የሚሉ መፈክሮችን ጽፈው...
View Articleየአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና የሌሎችም ፖለቲከኞች መታሰር የፈጠረው ህዝባዊ ቁጣ እንደቀጠለ ነው
ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ህገወጥ በሆነ መልኩ አሳልፈው ከሰጡዋቸው በሁዋላ ኢትዮጵያውያን አሁንም ቁጣቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች ” የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ልብን የሚሰብር ቢሆንም፣ ወሳኙ ነገር ማዘን ሳይሆን...
View Articleአቶ ሽመልስ ከማል የሚመሩት ፕሬስ ድርጅት ደካማ ነው ተባለ
ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርላማ : ባህል ፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ቋሚ ኮምቴ ስብሳቢ 73ኛ የምስረታ ዓመቱን በቅርቡ ያከበረውን የኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅት በቁሙ እየሞተ መሆኑን በመጠቆም በራሱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይትችትአቀረቡ፡፡ የቋሚ ኮምቴው ስብሳቢ ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ ከአዲስ ዘመን...
View Articleበአማራ ክልል አርሶ አደሮችን ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱ ውጤታማ አይደለም ተባለ፡፡
ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደር ፀጥታ እና የፖሊስ ኮሚሺን በጋራ የ2006 ዓ.ምየ11 ወራት አፃፀም በገመገሙበት ውይይት የጎጃም ፤የጎንደር ፤የሺዋ እና የኦሮሞ አርሶ አደሮች ዛሬምበድብቅመሳሪያዎችንበነፍስወከፍበየቤቱይዘው እንደሚገኙያወሱሲሆን፣ አርሶ አደሩ የጦር መሳሪያውን...
View Article“ግንቦት ሰባትን ለማዳከም የተወሰዱ እርምጃዎች ከፍተኛ ውጤት አስገኝተዋል”ሲል የፀረ ሺብር ግብረሃይል አስታወቀ፡፡
ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ እና እሁድ በጠቅላይ ሚኒስትር አዳራሽ የጸረ ሽብር ግብረሃይሉና የኢህአዴግ ባለስልጣናት በጋራ የመከሩ ሲሆን፣ስኬታማ ስራዎችን ለመስራት 3 ሚልየን 400 ሺ ዶላር ወጭ ማድረጉን ገልጿል፡፡ “ኢሳያስ ቢያስፈልገን እርሱን የመያዝ አቅም ላይነን” በማለትራሱን...
View Articleበኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና ሌሎችም የታሰሩት ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ጠየቁ
ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በኖርዌይ የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የአቶ አንዳርጋቸውን ተላልፎ መሰጠት በእጅጉ አውግዘዋል። ከፍተኛ ቁጣ ባስተናገደው ተቃውሞ እንግሊዝ እየወሰደችው ያለው እርምጃ እንዲብራራላቸው ጠይቀዋል። በኖርዌይ የውጭ ጉዳይ መስሪያ...
View Articleእስራኤል በጋዛ ላይ ያቋረጠችውን ድብደባ እንደገና ጀመረች
ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃማስና በእስራኤል መካከል የተጀመረው ጦርነት ፣ በግብጽ አደራዳሪነት ለሰአታት ጋብ ብሎ የቆየ ቢሆንም፣ እስራኤል ድብደባውን እንደገና መጀመሯን ቢቢሲ ዘግቧል። በግብጽ የቀረበውን የሰላም ስምምነት እስራኤል ብትቀበለውም፣ ሃማስ ግን ስምምነቱ ሽንፈትን እንደመቀበል...
View Articleየአዲስ አበባ ቴልኮም ማስፋፊያ ስራ በተያዘለት የጊዜ ገድብ ሊፈጸም አልቻለም
ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮ ቴሌኮም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ፈሶበት በሥራ ላይ የነበረውን የኖኪያ ኔትወርክ ነቅሎ በመጣል በቀላሉ ለስለላሥራ በሚመች መልኩ በአዲስ መልክ ለመትከል በቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ እየተከናወነ ያለው የአዲስ አበባ የቴሌኮም ማስፋፊያ ሥራ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ...
View Articleየደብረ ታቦር ህዝብ በባለስልጣናት መማረራቸውን ገለጹ
ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የከተማው እና የዞኑ አመራር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ኗሪዎች በመሰረተ ልማት ፤ በመልካም አሰተዳደር ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ አለም ደጉ የተባሉ የደብረ ታቦር ኗሪ ” የጋማ ከብት እና ሰዎች በአንድ ላይ...
View Articleየውጭ ጉዳይ ሚ/ር “የሚመለከታቸው አካላት ካልፈቀዱ በስተቀር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመጎብኘት እንደማይቻል”ገለጸ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለእንግሊዝ የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ በጻፈው ደብዳቤ፣ አቶ አንዳርጋቸው የህግና የማማከር አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ” የሚመለከታቸው አካላት” መፍቀድ አለባቸው ብሎአል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ” የሚመለከታቸው አካላት” ያላቸውን አካላት በስም ከመጥቀስ ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ...
View Articleየኤድስ ስርጭትን እኤአ እስከ 2030 ማቆም እንደሚቻል ተመድ ገለጸ
ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ኤጀንሲ እንደገለጸው ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ አገሮች የኤደስ ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነ ሲሆን ፣ ስርጭቱንም ከ14 አመታት በሁዋላ ማቆም እንደሚቻል ገልጿል። አሁንም በርካታ ዜጎች መድሃኒት አጥተው በመሰቃየት ላይ...
View Articleየድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት እንደገና ተራዘመ
ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ሰበቦች እየቀረቡበት የሚራዘመው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ሂደት ዛሬም በችሎት አዳራሽ ለውጥ ምክንያት እንዲራዘም ተደርጓል። በአቶ አቡበክር ምዝገብ የተከሰሱት ኮሚቴዎች፣ የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ ማስደመጥ እንደጀመሩ ነበር የችሎት...
View Article