Quantcast
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሚፈጸመው እስር እንዳሳሰበው ገለጸ

ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ተጠናክሮ የቀጠለው እስር በአገሪቱ ውስጥ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይኖር ያደረገ ነው ብሎአል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበት ሁኔታ አለመታወቁንና ለከፍተኛ ስቃይ ሊዳረጉ እንደሚችሉ መግለጹንና አለማቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰቡን ያስታወሰው አምነስቲ፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ደንኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሽዋስ አሰፋና ሀብታሙ አያሌው የተባሉ ታዋቂ ፖለቲከኖች መታሰራቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይኖር ለማድረግ የታሰበ መሆኑን ገልጿል።

የፖለቲካ ድርጅት መሪዎቹ በማእከላዊ ስቃይ ሊፈጸምባቸው እንደሚችልም አስጠንቅቋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles