Quantcast
Channel: Amharic
Browsing all 2145 articles
Browse latest View live

በሀረር ለ2ኛ ጊዜ የተነሳውን የእሳት አደጋ መንስኤ በተመለከተ የክልሉ መንግስትና ህዝቡ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጠ ነው

መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሀረር በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ህዝቡ መንግስትን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ መንግስት በበኩሉ ድብቅ የፖለቲካ አላማ ያላቸው ሀይሎችን ያደረሱት ቃጠሎ ነው ይላል። ቅዳሜ ምሽት ሲጋራ ተራ እተባለ በሚጠራው የንግድ ማእከል ላይ በተነሳው...

View Article


የአባይ ግድብ መዋጮ መቀዝቀዙ መንግስትን ስጋት ላይ ጥሎታል

መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በያዝነው ወር የሶስተኛ ዓመት የምስረታ ልደቱ የሚከበርለት የአባይ ግድብ ግንባታ እስካሁን ከወጣው ወጪ በሕዝብ መዋጮ መሸፈን የተቻለው 26 በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑና ሕዝቡ ለግድቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ መቀዛቀዝ ማሳየቱ ታውቋል። ግድቡ በመጋቢት 24 ቀን 2003...

View Article


አርሶ አደሩ ከግብር ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉ ተገለጸ

መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮሚዩኒኬሺን ጽ/ቤት  ከህዝብ ባሰባሰበው መረጃ እና ከክልሎች የተላከው የጽሁፍ ሰነድ እንዳመለከተው ፤ የኦሮምያ ፤ የአማራ እና የደቡብ ክልል አርሶ አደሮች ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ወስዳችሁ ግብር እና የማዳበሪያና የምርጥ ዘር እዳችሁን አንክፍልም...

View Article

በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጉዳይ በድጋሜ ተቀጠረ

መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ ሩጫ ላይ ተቃውሞ አሰምታችሁዋል በሚል ከአስር በላይ ቀናትን በእስር ያሳለፉት የሰማያዊ ፓርቲ 7 ሴት እና 3 ወንድ አመራሮች መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓም ጉዳያቸው ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚታይና ለዛሬ መጋቢት 9 ውሳኔ...

View Article

በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ውስጥና በዙሪያዋ ዋና መግቢያ በሮች በሚገኙ ከተሞች በየቀኑ የሚከሰተውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የትራፊክ አደጋ ተከትሎ በአንድ ክፍለ ከተማ ብቻ  3 ሰዎች በየቀኑ እንደሚሞቱ ለማዎቅ ተችሏል፡፡ በረ/ኢ/ር አሰፋ መዝገቡ በኩል ከመንግስት ሚዲያዎች በየቀኑ...

View Article


ነጋዴዎች በግብር ስርአቱ መማረራቸውን ተናገሩ

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነጋዴዎች ምሬታቸውን የገለጹት ሰሞኑን በግብር አከፋፈል ዙሪያ ላይ በባህር ዳር ከተማ የኢፌዴሪ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በስብሰባው ላይ በአማራ ከልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት አማካኝነት የተካሄደ ጥናት የቀረበ ሲሆን፣ በጥናቱምው...

View Article

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በዋስ ተፈቱ

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 10 የፓርቲው ሴት እና ወንድ አመራሮች ያለፉትን 11 ቀናት በእስር ቤት ካሳለፉ በሁዋላ ፖሊስ እያንዳንዳቸውን በ3 ሺ ብር ዋስ ለቋቸዋል። ምንም እንኳ አቃቢ ህግ ክስ ለመመስረት የሚያስችል በቂ ማስረጃ የለኝም ቢልም፣ ፖሊስ እስረኞችን በነጻ ከመልቀቅ በዋስ...

View Article

በኩዌይት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ናቸው

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ውጥረቱ የተጀመረው አንዲት ኢትዮጵያዊት አንድ የአገሪቱን ባለስልጣን ልጅ መግደሉዋን ተከትሎ ነው። ኢትዮጵያዊቷ ግድያውን የፈጸመችበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅ ባይቻልም፣ ገዳዩዋን በቅርብ እናውቃለን ከሚሉ ወገኖች የተገኘው መረጃ በቂም በቀል ተብሎ የተደረገ...

View Article


የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሽቆልቆል አሳሳቢ ሆኗል

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስአበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በታሪኩ አይቶ የማያውቀው የአገልግሎት አሰጣጥ መጨናነቅ እንዳጋጠመውና በዚህም ምክንያት ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አንጻር የአገልግሎት ጥራቱ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱን አንድ ከድርጅቱ የተገኘ ጥናታዊ...

View Article


አንድነት ፓርቲ የእሪታ ቀን በሚል በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ ነው

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው የተቃውሞ ሰልፉን የሚጠራው በዋና ከተማዋ የሚታዩትን የማህበራዊ አገልግሎቶችን ችግሮች ለመቃወም ነው። “በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት መፍረሳቸው፣ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው...

View Article

በሀረር በህዝቡና በአስተዳደሩ መካከል ያለው አለመተማመን መስፋት ወደ ብሄር ግጭት እንዳያመራ ተስግቷል

መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር በአንድ ሳምንት  ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የንግድ ቤቶች መቃጠላቸውን ተከትሎ፣ በህዝቡና ክልሉን በሚመራው የሃረሪ ሊግ መካከል የተፈጠረው ከፍተት እየሰፋ መሄድ የብሄር ግጭት ሊያስነሳ ይችላል በማለት ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸው...

View Article

በኬንያ ወንዶች ተጨማሪ ሚስቶች እንዲኖራቸው የሚያዘው ህግ በፓርላማው ጸደቀ

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአመታት ሲያወዛግብ የነበረው ወንዶች ባለ ብዙ ሚስቶች የሚያደርጋቸው ህግ ትናንት በፓርላማ አባላት ሲጸድቅ፣ 30 የሚሆኑ ሴት የፓርላማ አባላት ክርክሩን ረግጠው ወጥተዋል። አንድ የፓርላማ አባል ” ይህ አፍሪካ ነው፣ በአፍሪካ ባህል የአፍሪካ ሴት ስታገባ ፣...

View Article

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ አሁንም በእስር ላይ ነው

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ችግር ለጀርመን ሬዲዮ በመዘገብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በውል ባልታወቀ ምክንያት  ሳምንታትን በእስር ለማሳለፍ መገደዱ ታውቋል። ነብዩ በተለይም ከወራት በፊት ከሳውድ አረቢያ በሚፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ...

View Article


ከሳውዲ አረቢያ የተመሰሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተመልሰው እየተሰደዱ ነው

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በአስከፊ ሁኔታ ከሳውድ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ዜጎች ተመልሰው እየተሰደዱ እንደሆን መረጃዎች አመለከቱ። ኢትዮጵያውያውያኑ ስደትን እንደ አማራጭ የሚጠቀሙበት በአገራቸው ለመስራት ሁኔታዎች እንዳልተመቻቹላቸው በመግልጽ ነው። በተለይ ወደ...

View Article

በሻኪሶ ተነስቶ ለነበረበው ብጥብጥ ህዝቡ መንግስትን ተጠያቂ እያደረገ ነው

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአስር ቀናት በፊት በሻኪሶ ከተማ ጎሳን ማእከል አድርጎ በተማሪዎች መካከል በተነሳው ብጥብጥ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ አለበት ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማው ባለስልጣናት በግጭቱ ዙሪያ ህዝቡን በማወያየት ላይ ሲሆኑ፣ የከተማው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ...

View Article


በጅጅጋ አንድ የልዩ ሃይል አባል የዩኒቨርስቲ ተማሪ ገጭቶ በመግደል አመለጠ

መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነውና ስሙ ለጊዜው ያልታወቀው ወጣት የተገደለው ጧት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አስቀድሶ ሲመለስ ነው። የልዩ ሃይል ንብረት የሆነችውን መኪና የሚያሽከረክረው ሰው ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ በፍጥነት በማሽከርከር ተሰውሯል። ልዩ...

View Article

ኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃን በማዳረስ በኩል የሚሊኒየም ግቦችን ብታሳካም በንጽህና በኩል ወደ ሁዋላ መቅረቷን ዩኒሴፍ ገለጸ

መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ አመታዊውን የውሃ ቀን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ በሚሊኒየም የልማት ግቦች የተቀመጠውን ለ62 በመቶ የሚሆነው ህዝብ እስከሚቀጥለው አመት የንጹህ የመጠጥ ውሃ  ተጠቃሚ የማድረጉን እቅድ ተሳካለች። ይሁን እንጅ ይላል ድርጅቱ ህዝቡ ንጹህ...

View Article


ኢትዮጵያ አሰብን ለማለፍ ስትል ከመቀሌ ታጁራ ለሚሰራው የባቡር መስመር ተጨማሪ 6 ቢሊዮን ብር እንደምታወጣ ታወቀ

መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መቀሌ/ ወልድያ፣ ሰመራ ታጁራ የሚባለውን የባቡር ሃዲድ ፕሮጀክት ግንባታን ለመስራት ኢትዮጵያ 34 ቢሊዮን ብር የሚሆን ገንዘብ የመደበች ሲሆን ፣ መስመሩ አሰብን ለማለፍ ሲባል ተጨማሪ 6 ቢሊዮን ብር ወይም 300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣት ለኢሳት...

View Article

የኢትዮጵያ መንግስት በውጭና በአገር ውስጥ የሚገኙ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ይሰልላል ተባለ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ይሰልላል ብሎአል። ድርጅቱ ባወጣው ባለ 100 ገጽ ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለስርአቱ አደገኛ ናቸው...

View Article

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ልማት ሕዝብን ተጠቃሚ የማድረጉ ጉዳይ በሕዝብ ጥያቄ እንደተነሳበት አንድ ጥናት አመለከተ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በአዋጅ በፈረሰ ስያሜ የሚጠቀመው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት አዲስአበባን ጨምሮ በ20 ከተሞች አደረግነው ባሉት ጥናት በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው ልማት አብዛኛውን ሕዝብ ተጠቃሚ የማድረጉ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ እምነት አለኝ...

View Article
Browsing all 2145 articles
Browse latest View live