Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኤርትራ በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም ወንጀል ሳትፈጽም እንደማትቀር ገለጸ

$
0
0

ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጀቱ ለአንድ አመት ሲያካሂድ የነበረውን ጥናት በሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ውስጥ ይፋ የሚያደርግ ሲሆን፣ በሪፖርቱ የኤርትራ መንግስትን ይወቀሳል። የኤርትራ ህዝብ ከህግ ይልቅ በፍርሃት ነው
የሚገዛው የሚለው ድርጅቱ፣ ከፍርድ ቤቶች እውቅና ውጭ ሰዎች በዘፈቀደ ይገደላሉ ብሎአል። ወጣቶች አገራቸውን ጥለው እንደሚሰደዱና ገደብ ለሌለው ብሄራዊ ውትድርና አግልግሎት እንደሚሰጡ ሪፖርቱን ዋቢ በማድረግ የተለያዩ አለማቀፍ
ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ድርጅቱ ከኤርትራ መንግስት እውቅና ውጭ ጥናቱን ማድረጉን ገልጿል። የኤርትራ መንግስት በጥናቱ ለመካፈል ለምን እንዳልፈለገ ግን የገለጸው ነገር የለም ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ካውንስል በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ምርምራ እንዲያድርግ በተለያዩ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ቢጠየቅም እስካሁን ፈቃደኛ አልሆነም። ድርጅቱ በቅርቡ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አያያዝ
ዙሪያ ምርመራ እያደረገ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከኤርትራ የሚሰደዱ ወጣቶች ቁጥር መጨመሩን ገልጾ፣ መንግስታትም ስደተኞችን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርቧል። የኤርትራ መንግስት ስደተኞች ስራ ፍለጋ ከአገር እንደሚወጡ ይገልጻል።
የኤርትራ መንግስት በሪፖርቱ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles