Quantcast
Channel: Amharic
Browsing all 2145 articles
Browse latest View live

በአዊ ዞን  የኢህአዴግን የአባልነት ፎርም አንሞላም ያሉ ተማሪዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

ኀዳር ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዊ ዞን አንከሻ ወረዳ ውስጥ የሚማሩ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የኢህአዴግን የአባልነት መሙያ ፎርም ወስደው እንዲመዘገቡ በርእሰ መምህራቸው አማካኝነት ቢጠየቁም፣ ከ700 ያላነሱ ተማሪዎች ድርጊቱን ተቃውመዋል። ተማሪዎቹ የአባልነት ቅጹን በሁለት ቀናት ውስጥ...

View Article


በኮምቦልቻ ከተማ በመጠጥ ውሃ ታሪፍ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ሊደረግ ነው

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ካቢኔ የከተማዋ ነዋሪዎች ጭማሪው እንዲከፍሉ የወሰነው ለከተማው ውሃ ለመዘርጋት ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቱን በመግለጽ ነው። የክልሉ የውሃ ሀብት ም/ል ሃላፊ ለክልሉ ካቢኔ እንደገለጹት ለከተማዋ የውሃ መስመር ዝርግታ 6 ሚሊዮን 300 መቶ ሺ ብር ለማስፋፊያ...

View Article


130 የግል ትምህርት ቤቶች ክስ ተመሰረተባቸው

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የተጋነነ የትምህርት ቤት ክፍያ ዋጋ በመጨመር ህብረተሰቡን ለአላስፈላጊ ወጪ ዳርገዋል በተባሉ 130 የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ክስ መመስረቱን የአዲስአበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን እና የግል...

View Article

የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በተቀናጀ የከተማ ፕላን ላይ የመስተዳድሩን ሰራተኞች ሊያሰለጥን ነው

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከላከው ቅጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ፓርቲው በአዲስ አበባና ኦሮምያ የተቀናጀ የከተማ እቅድ ዙሪያ በመንግስት ሰራተኛው ውስጥ ያለውን የአመለካከት ክፍተት ለመሙላት ስልጠና ይዘጋጃል። ፓርቲው የተለያዩ ቅጾችን...

View Article

ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ የገንዘብ ገበያ ለመበደር ድርድር ጀመረች

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት የጀመራቸውን የሃይል፣ የመንገድ፣ የባቡርና የስኳር ፋብሪካዎችን ለመጨረስ የሚያስችለውን ገንዘብ ከአለማቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር የሚያስችለውን ድርድር ከሁለት የአውሮፓ እና ከአንድ የአሜሪካ ባንክ ጋር ጀምሯል። መንግስት ገንዘቡን ለመበደር...

View Article


ሰማያዊ ፓርቲን ያቀፈው የ9 ፓርቲዎች ትብብር በመንግስት አፈና ትግሉን እንደማያቆም አስታወቀ

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ባወጣው መግለጫ ህዳር 21 ለሚደረገው ስብሰባ ለመስተዳድሩ የሰለማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ቢላክለትም ለመቀበል ፈቃደኛ ካለመሆኑም በተጨማሪ፣ ስብሰባውን የሚያስተባብሩት የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ የሆኑት አቶ ኑሪ...

View Article

በምእራብ አርማጭሆ ወጣቶች የጸረሰላም ሃይሎች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተነገራቸው

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብአዴን አመራሮች ሰሞኑን በዞኑ ባካሄዱት የወጣቶችና ሴቶች ጉባኤ ላይ ፣ የአካባቢው ወጣቶች የጸረ ሰላም ሃይሎች መሳሪያ ከመሆን እን  ዲቆጠቡ ጠይቀዋል። ወጣቶቹ በግፍ የታሰሩ የአካባቢው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አንጋው ተገኝ፣ አባይ ዘውዱና...

View Article

አንድ የአርበኞች ግንባር አባል በእስር መቀጣቱ

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኛ ጋሻው ሽባባው በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ጋር ለ4 ወራት ሲፋለም በቁጥጥር ስር መዋሉን ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም ድርጊቱ የ4 አመት ከ8 ወር እስራት እንደፈረደበት ገልጿል።...

View Article


የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለአዳር የሚቆይ ተቃውሞ በመስቀል አደባባይ ለማካሄድ የእውቅና ጥያቄ አቀረበ

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ህዳር 18 ለመስተዳድሩ ባስገባው የእውቅና ጥያቄ ፣ የተቃውሞ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ከህዳር 27 እስከ ህዳር 28፣ 2007 ዓም ለማካሄድ ማቀዱን ገልጿል። የእውቅና ደብዳቤውን ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣...

View Article


በሚሰሩት መንገዶች ደስተኞች አይደለንም ሲሉ የባህርዳር ነዋሪዎች ገለጹ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገዢው መንግስት በምርጫ 2007 ያለውን ተቀባይነት ለማጠናከር በማሰብ የተለያዩ የህብረተሰቡን ክፍሎች በየክፍለ ከተማው በማሰባሰብ የተሰሩ ስራዎችን በማቅረብ ለመመስገን ሙከራ ቢያደርግም፤ተሰብሳቢዎች ግን ምንም እንዳልተሰራና ተሰራ የተባለውም ችግር ያለበት...

View Article

በሃረር የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች የሚያመልኩበት አንድ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ ተደረገ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ሰማያዊ ብርሃን ቤተክርስቲያን በመሄድ ማፍረሳቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን አንድ ፓስተር እስከባለቤታቸውና ሌላ አገልጋይ ታስረዋል። የሃረር አብያተ ቤተከርስቲያናት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዮሴፍ አምደማርያም ታስረው...

View Article

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአቶ አንዳርጋቸውን  መታሰር በመቃወም ሰልፍ አደረጉ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ኦስሎ በሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ገዢው ሃይል የወሰደውን እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ የኢንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስላሉበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የተቃውሞ...

View Article

በአብዛኛው በቀድሞ ባለስልጣናት የተመሰረተው ራያ ቢራ ፋብሪካ በቅርቡ ወደምርት ሊገባ መሆኑ ተሰማ፡፡

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞው የመከላከያ ኢታማጆር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳይ የቦርድ ሰብሳቢነት የሚመራው ራያ ቢራ በቀድሞ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህወሃትን ተጠግተው በሚነግዱ ነጋዴዎች ከፍተኛ አክስዮን የተመሰረተ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። ማይጨው ከተማ...

View Article


መንግስት ከጸጥታ ችግሮች መካከል የተወሰኑትን መቅረፉን አስታወቀ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ከፌደራልና ከክልሎች ለተውጣጡ የጸጥታና ደህንነት ሃላፊዎች እንደተናገሩት መንግስት አራት የጸጥታ ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ የመጀመሪያው የሽምቅ ውጊያ የሚያደርጉ ሃይሎች የፈጠሩት ስጋት ነው ያሉት ዶ/ር ሽፈራው...

View Article

በድቡብ ሱዳን አራት  ኢትዮጵያውያን በጥይት ተመቱ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንዳለው በዋና ከተማዋ ጁባ አንድ ወንድና አንድ ሴት ሲገደሉ ሁለት ሴቶች ግን በጠና ቆስለው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደዋል። የሁለቱም ሟቾች አስከሬንም በኢትዮጵያውያን እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱ ታውቆል:: ሰዎቹ በምን ሁኔታ እንደተገደሉና እንደቆሰሉ...

View Article


የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን አስገራሚ የደሞዝ ጭማሪ አደረገ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት 111 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል በተከታታይ ተገቢ የሆነ የደሞዝ ማስተካካያ አላደረገም በሚል ጥያቄ ሲቀርብብት ቆይቷል። ሰሞኑን የካቢኔ አባላት ተሰብስበው   የአማራ ክልል...

View Article

ዘጠኙ ፓርቲዎች የህዳር 27 እና 28 የተቃውሞ ሰልፉን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ...

View Article


ህጋዊ ተቃዋሚዎችን በአክራሪነት ሰበብ ለመምታት የሚያስችሉ ሃሳቦች ቀረቡ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቃስቃሴ የሚያደርጉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በሽብርተኝነት እና ጽንፈኝነት በመፈረጅ የጥቃት ኢላማ ለማድረግ መታሰቡን ኢሳት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ጉዳዮች ሰሞኑን ከመንግስት...

View Article

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ጀርመን አቀኑ

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ አገሪቱ ከግል የገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋን ተከትሎ የኢትዮጵያን ብድር በበላይነት በሚያስተባብረው በጀርመን ትልቁ ባንክ አማካኝነት በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ተብሎአል። ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ ገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋ ብዙ...

View Article

በአማራ ክልል ባለፉት 5 አመታት ከ6ሺ በላይ ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን አጡ

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 ዓ.ም ወዲህ በተከሰተ አደጋ በክልሉ 18ሺ 994 የመኪና አደጋዎች ተከሰተዋል፡፡ በትራፊክ ሳምንት ውይይት ላይ እንደተገለፀው በአጠቃላይ በአምስት አመታት በተከሰተው አደጋ 6ሺ 668 ሰዎች ህይዋታቸውን አጠዋል፡፡ 6ሺህ 581 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ፤...

View Article
Browsing all 2145 articles
Browse latest View live