ኢትዮጵያና ግብጽ የቃላት ጦርነት ጀምረዋል
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሁለቱ አገሮች መካከል መተነኳኮሱ እየባሰ የመጣው ዘንድሮ ግንቦት 20 ቀን የተከበረውን የገዥውን ፓርቲ በኣል ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ ፦” የ አባይ ወንዝን የተፋሰስ አቅጣጫ አስቀየስኩ” ብላ ማወጇን ተከትሎ ነው። ይህን ተከትሎ በተለይ የግብጽ መንግስት...
View Articleኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የወጣን ጅብ ለማስወጣት 5 ጥይቶች ሲተኮሱ አንድ ወጣት ቆሰለ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው ሰሞኑን ከምሽቱ አራት ሰዓት በአንድ የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት ሶስተኛ ፎቅ ላይ የተኛውን ጅብ ለማስወጣት አምስት ጥይቶች ተተኩሰው ጅቡ የተገደለ ሲሆን፤ በአካባቢው የነበረ አንድ ወጣት ሆዱ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ገብቷል። ጅቡ በህንጻው...
View Articleበሻሸመኔ ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተፈጸመ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቁጥራቸው 13 የሚጠጋ የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት አቶ በየነ ሞርሲ፣ ሳምሶን ራቦ፣ አበራ መቲቦ እንዲሁም በማዘጋጃ ቤት ውስጥ ሀላፊ የሆነ አቶ ዳዊት ደጮ የተባሉት ግለሰቦች ” አብዲ ሁንዳ” እና ሀምሌት የተባሉ የቤትና የንግድ ማህበሮችን መስርተናል...
View Articleየአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ እና ግብጽ እንዲነጋገሩ ጠየቀ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህብረቱ ጥያቄውን ያቀረበው በኮሚሽነሩዋ በዳላሚነ ዙማ አማካኝነት ነው። ሁለቱ አገሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለመፈለግ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር መዘጋጀት አለባቸው በማለት ኮሚሽነሩዋ ተናግረዋል። ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እወስዳለው ማለቷን ተከትሎ አቶ...
View Articleወደሶማሌ ክልል ተጉዞ የነበረው የአርቲስቶችና የጋዜጠኞች ቡድን በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዳለ ምስክርነቱን በመስጠት...
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቡድኑ ከጎዴ ተነስቶ በቀብሪደህር፣ በደገሃቡር፣ በቀብሪበይህ፣ በጂጂጋ አድርጎ ወደሐረር በመግባት የሳምንት ጉዞውን በድሬዳዋ ከተማ ባለፈው እሁድ አጠናቋል፡፡ በጉዞው ወቅት በአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት የተጓዘው የዚሁ ቡድን አባላት ከሆኑት...
View Articleየፊታችን እሁድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካው ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስአበባ ስታዲየም የሚያካሂደው የዓለም...
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፊታችን እሁድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካው ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስአበባ ስታዲየም የሚያካሂደው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ ግጥሚያን በመሃል ዳኝነት የሚመሩት ግብጻዊ ዳኛ በመሆናቸው ጨዋታው በሰላም የመጠናቀቁ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ስጋት አሳድሯል።...
View Articleየደሴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ከስራ ተባረሩ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል የአሰተዳደር እና ጸጥታ ዘርፍ ቢሮ በተለያዩ ዞኖች በሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች ላይ ግምገማ ሲያደርግ መቆየቱን ተከትሎ የደሴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ደረጀ እንዲባረሩ ተደርጓል። በቅርቡ ኢሳት ይፋ ባደረገው የድምጽ ማስረጃ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች...
View Articleበደቡብ ጎንደር ዞን መምህራን በደህንነት ሀይሎች ታፍነው ተወሰዱ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደብረ ታቦር ከተማ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ መምህራን ትናንት ማታ እና ዛሬ ጠዋት በደህንነት ሐይሎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።...
View Articleፍርድ ቤት የባንክ ሂሳባቸውን ያገደባቸው የመንግስት ባለስልጣናትና ባለሀብቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቁጥር የኮ/መ/ቁ 134048 ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 429 የመንግሥት ኃላፊዎችና ባለሃብቶች በመንግሥትና በግል ባንኮች ያላቸው ገንዘብ የታገደባቸው መሆኑን ፣ የአንዳንዶች ደግሞ የድርጅታቸው የባንክ ሂሳብና...
View Articleየተምች ወረርሺኝ በመላ ሃገሪቱ ቡቃያዎችን እያጠቃ ነው፡፡
ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፀረ ሰብል ተባይ ወይም ተምች ወረርሽኝ በአማራ በኦሮሚያ ዞን፣ በምስራቅ ጎጃም፣ በደቡብ ጎንደር፣በሰሜንና በደቡብ ወሎ፣ በትግራይ ደቡባዊ ዞን በአላማጣና ራያ አዘቦ ወረዳዎች ቡቃያዎችን እያጠፋ ነው፡፡ በባህላዊ ዘዴዎችና በኬሚካል ርጭት ለመከላከል ሙከራ ቢደረግም...
View Articleከ 30 በላይ አረጋውያን ያለምንም ጥያቄ ታስረው ይገኛሉ ሲሉ ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ
ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮምያ ክልል በጎሬ ወረዳ በንግድ ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ከ30 በላይ አረጋውያን ካለፉት 8 ወራት ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ገልጸው፣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር እውነቱ በቀለ አረጋውያኑ መታሰራቸውን አምነዋል። አብዛኞቹ እስረኞች እድሜያቸው...
View Articleአንድነት ፓርቲ ግብጽና ኢትዮጵያ ከጸብ አጫሪነት ድርጊት እንዲቆጠቡ ጠየቀ
ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ” ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የቆረጠ ፓርቲ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” የግብጽና የኢትዮጵያ መንግሥት ከፀብ አጫሪ ድርጊት እንዲቆጠቡ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ከሚያበላሹ ፕሮፓጋንዳዎችን...
View Articleየአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ አስተያየቶችን ሊሰማ ነው
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ከታዋቂ የውጭ አገር ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አስተያየቶችን እኤአ ሰኔ 20 ይሰማል። ከኢትዮጵያ የግንቦት7 ሊቀመንበር እና በበክኔል ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ...
View Articleኢሳትን ሲመለከቱ የነበሩ 60 ሰዎች መታሰራቸው ተሰማ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በባሌ ሮቤ እና በጎባ ከተማ በቅርቡ ኢሳትን ሲመለከቱ የተገኙ ሰዎች ገናሌ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት ውስጥ መታሰራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ግለሰቦቹ የተያዙት በተለያዩ ሰበቦች ቢሆንም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚቀርብባቸው ክስ ግን የተቃዋሚ ጣቢያ የሆነውን...
View Articleሰማያዊ ፓርቲ አለ።
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ ፦<<እነሱ ከ አባቶቻቸው አይበልጡም፤ እኛም ከ አባቶቻችን አናንስም>> በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ወረራና ደባ መፈፀም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ከመነሳቷ እጅግ በርካታ አመታት በፊት...
View Articleበአባይ ግድብ ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ማድረግ ተጀመረ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው የደህንነት መረጃ እንዳመለከተው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ቻይና እና ሩሲያ ሰራሽ ራዳሮች ሰሞኑን በአካባቢው ተተክለዋል። መንግስት ማንኛውንም አይነት ድንገተኛ የአየር ወይም የሰርጎ ገቦች ጥቃት ለመከላከል ዘመናዊ ራዳሮችን ከመትከል በተጨማሪ የተወሰኑ...
View Articleየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የሰላማዊ ሰልፍለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ በአዲስ አበባ መስተዳድር ጽህፈት...
ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ-ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ- መድረክ ለእሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚቆይና ከስድስት ኪሎ ተነስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጎዳና በማድረግ መዳረሻው ድላችን ሐውልት የሚያደርግ ሰላማዊ ሰልፍ...
View Articleገዢው ፓርቲ በደሴና ጎንደር የሚካሄዱትን ሰላማዊ ሰልፎች ለማደናቀፍ እየሞከረ ነው የፓርቲው ሰዎች በአቋማቸው ጸንተዋል
ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀምሌ 7፣ 2005 ዓ/ም በደሴና ጎንደር ከተሞች አንድነት ፓርቲ የጠራቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች በታቀደላቸው ጊዜ እንደሚካሄዱ ከመንግስት እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ባለስልጣናት የቅስቀሳ ወረቀቶችን የሚበትኑትን ሰዎች ከማሰር እና...
View Articleታዋቂው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆኖ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሊመረጥ እንደሚችል ተጠቆመ
ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሻለቃ ኃይሌ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለው ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጹን ተከትሎ ኢህአዴግ መራሹ ራዲዮ ፋና ባልተለመደ መልክ ዜናውን ደጋግሞ እንዳራገበው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቅሰው ፣ ሀይሌ የሰጠውም መግለጫ ሆነ የሬዲዮ ፋና ዘገባ በድንገት የሆነ...
View Articleበ1976 ዓ.ም የተቋቋመው አንጋፋው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ማኔጅመንት ከሠራተኛው ጋር እሰጣ አገባ ውስጥ ገባ
ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በሀላፊነት ላይ የሚገኙ የድርጅቱ ሠራተኛ እንደተናገሩት በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር በቦርድ ሰብሳቢነት ወደመድን ድርጅት ከመጡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ዘረኝነትና ግልጽ የሆነ ዘረፋ...
View Article