Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

በሰሜን ወሎ በመርሳ ከተማ በህዝብና በፖሊስ መካከል በተደረገ ግጭት ሁለት ሰዎች ተጎዱ

$
0
0

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግጭቱ የተነሳው በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ የመዘጋጃ ሰራተኞች እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተከትሎ ነው። ህዝቡ ድንጋይና ዱላ በመያዝ ፖሊሶችን ደብድቦ ያባረረ ሲሆን፣ ፖሊሶቹ ተደራጅተው በመምጣት ሁለት ሰዎችን በጥይት መትተው የተወሰኑትን ደብድበው አስረዋል። ፍጥጫው ዛሬም ደረስ የቀጠለ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪ ቤቶቻችን አይፈርሱም በማለት በአቋሙ እንደጸና ነው።

የቆሰሉት ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ለኢሳት የደረሰው ዜና ያመለክታል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles