Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ መንግስት ሰበቦችን እየፈለገ ነው

$
0
0

ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማደናቀፍ በተለያዩ ክፍለከተሞች ስብሰባ መጥራቱ ታውቋል።

የተለያዩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት መስተዳድሩ በሰልፉ ላይ ብዙ ህዝብ እንዳይገኝ ለማድረግ ከቤት ጋር የተያያዙ አጀንዳዎችን በማንሳት ህዝቡ ወደ ተቃውሞ ሰልፉ እንዳይሄድ ለማድረግ እየጣረ ነው።

“ኢህአዴግ ድህነትን ለፖለቲካ ድጋፍ ማስገኛ እየተጠቀመበት መሆኑን፣ በከተማው ያሉ የቤት እና ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት የማየፈልገውም ህዝቡ መሰረታዊ ነገሮች ከተማሉለት ድጋፍ አይሰጠኝም ብሎ በማሰብ የህዝቡን ድህነት የፖለቲካ ድጋፍ መግዢያ ማድረጉን የሚያሳይ ነው” በማለት ዘገባውን የላከልን ሪፖርተራችን ከአዲስ አበባ ገልጿል።

ግንቦት25 እሁድ ሰልፉ በታቀደለት መሰረት ከተካሄደ ከምርጫ 97 በሁዋላ የመጀመሪያው የተቃውሞ ሰልፍ ይሆናል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles