Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

ፍርድ ቤቱ የእነ ደብሬ አሸናፊን ጉዳይ አላይም አለ

$
0
0

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመናገሻ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ሀምሌ 3/2007 ዓ.ም በደህንነትና ፖሊሶች ተይዞ የታሰረውን የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ደብሬ አሸናፊንና በወቅቱ ከእሱ ጋር ተይዘው የታሰሩትን ወጣቶች ጉዳይ እንደማያይ አስታውቋል፡፡
ዛሬ ሀምሌ 6/2007 ዓ.ም ደብሬ አሸናፊ፣ ቴዎድሮስ ሻንካና ኤፍሬም የተባሉት ታሳሪዎች አምስት ኪሎ በሚገኘው የመናገሻ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ዳኛው ‹‹ይህን ጉዳይ አናይም፡፡›› በማለታቸው እነ ደብሬ ወደ ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ዳኛው ጉዳዩን አላይም ያሉበት ምክንያት አለመታወቁን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles