Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

የመከላከያ  ቀንን  ለማክበር  ፈቃደኛ ያልሆኑ  የባጃጅ  ሹፌር  አሽከርካሪዎች  እየተቀጡ ነው

$
0
0

የካቲት ፭ (አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በባህርዳር የሚከበረውን የመከላከያ ሰራዊት ቀን የሰልፍ ትርኢት እንዲያጅቡ ተጠይቀው ፈቃደኛ ያልሆኑ የባህርዳር ባጃጅ አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃዳቸውን እየተነጠቁ ቅጣት እንደተጣለባቸው፣ አንዳንዶችም በፖሊስ መዋከባቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ሹፌሮች ለኢሳት ተናግረዋል።

ሹፌሮቹ መብታችን ተገፏል በማለት ባቀረቡት አቤቱታ፣ ያለፍላጎታቸው ስራ አቁመው ሰልፍ እንዲያጅቡ መጠየቃቸው አግባብ ባለመሆኑ አንዳንዶች መኪኖቻቸውን አቁመው ስራ ፈተው ለመዋል ተገደዋል።

መንግስት የመከላከያ ቀን የሚል በአል ማክበር መጀመሩ ይታወቃል፡፡  የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአንድ ብሄር ሰዎች የእዝ ቁጥጥር ስር መውደቁን ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ይገልጻሉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles