Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

3 እስራኤላዊ ወጣቶች መገደላቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ጨምሯል።

$
0
0

ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሶስት የእስራኤል ወጣቶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ መገደላቸው እንደታወቀ የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን በፈጸመው በሃማስ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ማስታወቁዋን ተከትሎ በአካባቢው ያለው ውጥረት አይሏል።

የአገሪቱ መሪ ጠ/ሚ ናትኒያሁ ” ወጣቶቹ በሰው እንስሶች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ” ተገድለዋል ያሉ ሲሆን፣ በሃማስ ላይ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ዝተዋል። ይህን ተከትሎም ማምሻውን እስራኤል በሃማስ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ከ30 ላላነሰ ጊዜ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።

ሃማስ በበኩሉ እስራኤል ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ የገሃነም በሮች ይከፈቱላታል ብለአል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles