Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all 2145 articles
Browse latest View live

በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ዘለፋ አዘል ግምገማ ተካሄደ

$
0
0

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት  ኢህአዴግ፣  ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው ተገምጋሚ

ራሳቸው ሆነዋል።

በጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የተደረገው ግምገማ አንድ ሙሉ ቀን የወሰደ ሲሆን፣ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ መጠናቀቁን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም ብዙዎችን የግምገማ ነጥቦች ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለግምገማው መራዘም ምክንያት

ሆኗል።

ሁሉም ባለስልጣናት  የሚገመገሙባቸው ነጥቦች ተመሳሳይነት አላቸው።  አስተያየቶች የሚሰጡትም በእነዚህ ነጥቦች ዙሪያ ነው።

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ  በቅድሚያ ራሳቸውን የሄሱ ሲሆን፣ እንዲህ ብለዋል ” ጥራት ያለው እቅድ አዘጋጅቶ በማከናወን ረገድ ፣ ራስን በንባብ ለማብቃት ጥረት በማድረግ ላይ እንዲሁም የለውጥ ትግበራ ላይ ችግሮች አሉብኝ” ። ነገር ግን “ስራን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በመፈጸም፣ ስራን በተሟላና ጥብቅ ስነምግባር በመፈጸም፣ ለስራ የተሰጠኝን መሳሪያዎች በእኔ ባይነት ስሜት በመጠቀምና በመጠበቅ እንዲሁም በፖሊሲ አፈጻጸም ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በኩል  ችግሮች የሉብኝም” ብለዋል። ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል በኩል በከፊል ችግሮች አሉብኝ ሲሉ አክለዋል።

ከቃለ ጉባኤው ለመረዳት እንደሚቻለው የመጀመሪያውን ሂስ ያቀረቡት ነባሩ የህወሃት ታጋይና የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ ናቸው። አቶ አርከበ ” የተጠራቀሙ ችግሮችን በመፍታት በኩል ችግሮች አሉብህ፣  ካቢኔህ ውስጥ ያለውን  የጥራት ችግርም በደንብ አላየኸውም፤ ለሃገሪቱ አመራር ቶሎ ምላሽ አትሰጥም፤ ‘እኔ የሚመስለኝ እንዲህ ነው’ ከማለት ውጭ፣ ቆፍጣና የሆነ አመራር አትሰጥም፤ ስራዎች ሁሉ ከሌላው አካል እንዲመጣልህም ትጠብቃለህ፣ ብዙውን ጊዜ በቅጻቅጾች ላይ አትኩረህ አይሃለሁ፤ ከብሄራዊ ደህንነት እና የቴክኖሎጂ ቁርኝት ጋር ያለውን ችግር ቁጭ ብለህ አለመፍታትህ ውዝግቡ እስካሁን እንዲቆይ አድርጎታል” ሲሉ ሂስ ሰንዝረዋል።

ሌላው የህወሃት አባል አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ ደግሞ  ” ስልጣንን ጠቅልሎ የመያዝ ነገር አለ፤ ስዎችን እርስ በርስ የማጋጨት ነገርም አለ፣ ለአማካሪዎችህ ‘እሱ ምን ሰርቶ ነው’ ትላለህ፣ በፖሊሲና እና ስትራቴጂ ላይ አዲስ የፈጠርኸው ቋንቋም የለም፣ ፓርላማው በአንተ

ጊዜ አዲስ ቃላትን እንኳ አለመደም፣ ይህም ከንባብ  የመጣ ችግር ነው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን በመደገፍ ፤ ሃሳብን በመቀበል ረገድ ችግር አለብህ፣ ገንቢ ሃሳብም በመስጠት ላይ ችግር ይታያል”” ብለዋል።

አቶ ሃይለማርያምን እጅግ ያበሳጫቸው የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል አሊሴሮ ያቀረቡት ትችት መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ።በቃለ ጉባኤው ላይ ሰፍሮ እንደሚታየው  አቶ አሊሴሮ ” ተግባብቶ መስራት ላይ ችግር አለ፣ ከክልሎች ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻሻል

የእሱ አስተዋጽኦ የለበትም፣ ያልተጻፉ ህጎች ይወጣሉ፤ ከክልሎች  ጋር ሳትነጋገር ከምክትሎች ጋር የኮሚኒኬሽንን ስልጣን በመጋፋት የህዝብ አስተያየት ትሰበስባለህ፤ ሰዎች ነጻ ሆነው እንዲሰሩ አለማድረግ፤ ገፍቶ ሄዶ ችግሮችን አለመፍታት፣ በአማራና አፋር፣ በትግራይና

አፋር ድንበሮች ያለውን ውዝግብ ተጋፍቶ ችግሮችን ለመፍታት አለመቻል፣ ጥሩነትን ወይም በጎነትን አለማበረታታት፣ አንዳንድ ሚኒስትሮች ቤተመንግስት እንዳይገቡ መከልከል፤ እቅድ ከማውጣት ጀምሮ በፖለቲካ ላይ ለውጥ ለማምጣት ስትጥር አለመታየት” የሚሉ

ትችቶችን በንባብ አሰምተዋል።

አቶ ሃይለማርያም ይህን ጽሁፍ ያዘጋጀውንና እንዲቀርብ ያደረገውን ሰው አውቀዋለሁ በማለታቸው ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር፣ እንደምንጮች መረጃ።

ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ባቀረቡት ሂስ ደግሞ ” በመንግስት በጀት እና ፋይናንስ እገዛ ማድረግ እና  ስራ እንዲሰራ መደገፍ ሲኖርብህ አትገድፍም፤ የመከላከያ ገንዘብ አወጣጥን በተመለከተ በከፊል በኦዲተር እንዲጣራ ከተስማማህ በሁዋላ ፣ በግልህ ሽረህ በእኔ ላይ ዛቻ እንዲደርስብኝ አስደርገሃል። ቤተመንግስቱን ኦዲት ለማድረግ በኦዲተርነት ሰርቶ የማያውቅ ሰው ተመድቧልና አይሆንም ስል፣ ‘ሂጂ ስራሽን ስሪ ዛሬ ችሎ ሊሆን ይችላል’ ተብያለሁ፣ ይሄ ስራ እንዲሰራ አለመፈለግ ነው። ለለውጥም ዝግጁ አይደለህም። በረከት ሰብስቦን

ሁሉም ስህተቱን ሲቀበል አንተ አልተቀበልህም፣ ይሄ ለለውጥ አለመዘጋጀትህን ያሳያል።” ብለዋል።

ወ/ሮ ሙፍሪያት  ” ከቢሮ ስነምግባር አንጻርም ችግሮች አሉ ይላሉ። ወደ ውጭ አገር በሚደረግ ጉዞ ላይ አድልዎ መኖሩን ራሳቸውን በምሳሌነት በማቅረብ ተናግረዋል። ” በግል ‘ አንቺ ተጽኖ ፈጣሪ አይደለሽም ፣ ደቡብ አንቺን ከሚወክል ቢቀር ይሻል ነበር’” ተብያለሁ

የሚሉት ወ/ሮ ሙፈሪያት፣  ወደ አውሮፓና ግብጽ ለሚደረገው የዲፕሎማሲ ጉዞ አስቀርቶኝ ወደ አዋሳ ልኮኛል ብለዋል። ዋናው ኦዲተር በአግባቡ እየሰራ አለመሆኑን ስናገርም ሙፈሪያት ስራ አትሰራም ብለኸኛል። ከካሱ ኢላላና ከሽፈራው ጋር ተጋጭቼ አንድም ቀን

ችግሩን ለመፍታት አልሞከርክም፤ የሰው ስም ታጠፋለህ፣ ትለማመናለህ”” ሲሉ የሰላ ትችት አቅርበዋል።

ወርቅነህ ገበየሁ ደግሞ ”   ቆራጥ አመራር በመስጠት በኩል መሰራታዊ ክፍተቶች አሉብህ” ያሉዋቸው ሲሆን፣  የፌደራል ፖሊስ ራሱ ተሟሙቶ ካልሰራ በስተቀር ሃይለማርያም አያግዘውም ሲሉ አክለዋል። “አፋጣኝ መልስ መስጠት ላይ ችግር አለ። የፌደራል ፖሊስ

ኮሚሽነር በነበርኩበት ዘመን፣ ህዳር 23 ሶማሊ በነብርኩበት ጊዜ በተደጋጋሚ ደውየ ‘ ስብሰባ ላይ ነኝ’ በሚል አልመለስክልኝም፤ ይዘነው የመጣነውን ፕሮግራም ጠፍቶብኝ ከደህንነቶች ጋር ስጨቃጨቅ ውዬ ፣ ተሰድቤ በበነጋታው ችግሩን ስነግርህ ልትፈታው አልቻልክም። የፌደራል ፖሊስ ከደህንነት ክፍሉ ጋር ያለው ግንኙነት የደከመ ነው። ጋምቤላ ላይ ያሉ ተዋጊዎችን እናጥፋቸው አሁንም ሶማሊና አማራ ክልል  ያሉ አማጽያንን እናጥፋ ስልህ የደህንነት ክፍሉና ጸጋየ በርሄ ይዘውታል ብለኸኛል። ጅጅጋ በተፈጠረው ነገር አራት ጊዜ ደውየ

ምላሽ ሳጣ ለሳሞራ ደወልኩ፣ እናም ‘ ለእኔ ከማሳወቅ ይልቅ ከጦሩ ጋ መንጠንጠል ይወዳል’ አልከኝ። ኢንሳ፣ ኢሳያስ ክፍል ስንሄድ ‘ሁሉንም ነገር እንዳታደርጉ ተብለናል’ እንባላለን። ከሁሉም የደህንነት ክፍሎች ጋር ፊትና ሁዋላ ሆነን እያለ በግዴለሽነት ችግሩን አልፈታሃውም” ሲሉ ጠንካራ ነቀፌታ አቅርበዋል።

ነባሩ የህወሃት ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ በበኩላቸው ” ሃይለማርያም ቸልተኝነት ያበዛል፣ በጣም ችላ ይላል፤ ስራዎችን ይገፋል። የሚያውቃቸውን ክህሎት፣ ካለው ሃላፊነት አንጻር ለሌሎች ላማካፈል አይጥርም፤ ያለመጋጨት ነገር አለ። ሚኒስትሮች ‘በፍላጎት እንዳንሰራ

ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱ ስልጠናዎችን ስናገኝ  ስለሚያሳልፍብን ነው’ እያሉ ስሞታ ያቀርባሉ። በስራ ስምሪት ወቅት በምትፈልጋቸው ስራዎች ላይ ራስህ ሰው ትመድባለህ። በረከት ላይ ትለጠፋለህ።” ብለዋል።

ሌላው ነባር ታጋይ አባይ ጸሃየ ደግሞ ” ሚኒስትሮች ሃላፊነት ተስምቷቸው የሚሰሩ አይመስለውም፤ ድጋፍ የማይሆን ክትትል ያበዛል፣ ሰራተኞችን በጣም ይንቃል። ከፍተኛ ሃላፊዎች ቢታመሙም የታመሙ አይመስልህም። ስራን ያላገናዘበ ሞራልን የሚነካ የሚያስፈራራ

ደብዳቤ ለአራት ሚኒስትሮች ሰጥተሃል።” ሲሉ ሂሰዋቸዋል።

የብአዴኑ ሊ/መንበርና ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ በፊናቸው ” ከህዝብ ወገንተኝነት ጋር በተያያዘ፣ አሁንም ቢሆን፣ ሁሉም እምነቶች በእኩል መስተናገድ ሲገባቸው ለፕሮቴስታንት ሃይማኖት ማዳለት እንዳለ ተገንዝቤአለሁ፤ ስራን በቁጭት ትሰራለህ ብየ አላስብም፣

የመሪነቱን እንዳልታማ እንጅ ለስራው ተቆርቁሮ የሚሰራ አይመስለኝም።  አስተያየት ሲሰጥ ተቀብሎ ለማሻሻል ከመጣር ይልቅ ሃሳቡ ጥሩ ነው ብሎ የመግፋት ነገር አለ፤ ከደህንነት ክፍሉና ከጠባቂዎችህ ጋር ያለህ ግንኙነትም የደከመነ ነው” ብለዋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ሮማን ገብረስላሴ ደግሞ ” ፈጣን ምላሽ መስጠት ላይ፣  ስብሰባ ከገባህ በምንም መንገድ መልስ አትሰጥም፣ ስራን ከፋፍሎ ያለመስጠት ነገር አለ። በሰው ላይ እምነት የማጣት ነገር አለ። ችግርን ወደ መድረክ አምጥቶ ከመፍታት ይልቅ ወደ ዝምታ ታመራለህ። ” ብለዋቸዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ የብአዴኑ አቶ አህመድ አብተው በበኩላቸው ” ታዳላለህ፣ የአቶ አዲሱ ለገሰን ስልጠና እንዳላገኝ ተከልክያለሁ፣ በአንተ አመራር ጥሩ ስራ መስራትና ጥሩ ስነምግባር ማሳየት የመብት መጣስን ያመጣል፣ በጣም ሃይለኛ ተንኮል አለብህ፤ በአንድ ስብሰባ

ላይ ‘አማራ አይቀበልህም’ ብለህ ከብሄሬ ጋር ልታጋጨኝ ሞከረሃል። በኢንዱስትሪ ዘርፍ ያሉ ሌሎች ስራዎችን ትተሃቸዋል ስልህ ‘ ስለሌሎች አያገባህም፤ እኔ ጠ/ሚኒስትር ነኝ’ አልከኝ። ለመማር እንኳ ዝግጁ አይደለህም። እኔ እየተማርኩ መሆኔን እያወቅ ከፈቃድ አሰጣት

ጋር አድልዎ ታደርጋለህ። ከጓደኞችህ ጋር በመሆን ‘አህመድ አገሪቱን በእንዱስትሪ ጭስ አፈናት ‘ ብለህ አፌዝክብኝ፤ ሰራተኛ ምንም አይመስልህም። ሞራል ትነካለህ፣ ሞራል አትጠብቅም፣ አስተካክል።” ብለዋል።

ሌላው ትችት አቅራቢ የደህዴኑ የኮምኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ናቸው። አቶ ሬድዋን ” ገንቢ አስተያየት መስጠትን በተመለከተ ፣ ብዙ ጊዜ አንድ ፕሮግራም አስቤ እጠይቅሃለሁ። ነገ ዛሬ እያልህ ሃሳብ አትሰጠኝም። አመራር ተቆራርጦ ይሰጣል። በወኔና በእልህ ሂ

ደቱን ለመለወጥ የሚደረገው ጥረት አናሳ ነው። ከእኔ ጋር በጥሩ ሁኔታ እያወራ ፣ ከሌላ ሰው ጋር ስለእኔ ሌላ ነገር ነው የሚናገረው፤ ለበረከት ‘እሱና ሽመልስ ልዩ ተልእኮ ያላቸው ሰዎች ናቸው፣ ልቆጣጠራቸው አልቻልኩም’ ብሎ ነግሮታል። ለእኔ አልነገርከኝም። የአመራር መስፈርቶችን ታሟላለህ አልልም።” የሚል ትችት አቅርበዋል።

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቀረቡባቸው ሂሶች ላይ መልስ ሰጥተዋል። “መሻሻል ያለባቸውን አሻሽላለሁ” ብለዋል። “ብዙውን ስራ እራሴ እሰራለሁ በሚል ለመስራት ስለምሞክር ነው ክፍተቶች የተፈጠሩት” የሚሉት አቶ ሃይለማርያም፣  “ስራውን ጠቅልሎ ይዟል

ለሚባለው ግን የሚገባኝን ይዣለሁ ብየ ነው የማስበው” ብለዋል።  ሰዎችን ማጋጨት ለተባለው  “እኔ ሰዎችን በማጋጨት ምን ላገኝ? ችግር ያለበትን ሰው ችግር አለበት ፣ ጥሩውንም ጥሩ ነው” እላለሁ። ሲሉ ተከራክርዋል።

“ሶማሊና አማራ፣ ትግራይ አፋር ላይ የተነሳው ችግር ከአሰራር ጋር በተያያዘ የመጣ ችግር መሆኑን የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፣ በሙፍሪያት ለተነሳው ቅሬታም ” ሙፈሪያትና ሽፈራውን ለማስማማት ሁለቱም ጋር ችግር አለ፤ አባይ እንዲፈታው ነግሬዋለሁ፡፡ ብለዋል””

“ስንሰራ ከፖለቲካ ጋር አስተሳስረን እንስራ ነው ያልኩት እንጅ ስራን አልከለከልኩም የሚሉት አቶ ሃይለማርያም በአቶ አህመድ  በአቶ አህመድ ለቀረበባቸው አስተያየት ደግሞ ” ፊት ለፊት ለራስህን ነው የነገርኩህ፣ ለሌላ ሰው በቀልድ መሃል ላወራ እችላለሁ።” ሲሉ በመካድና ባለመካድ መሃል ሆነው መልሰዋል።

“ለውጭ ጉዞ ታዳላለህ የተባለውን በአሰራራችን መሰረት ብናየው ጥሩ ነው ” ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ “እገሌ ከገሌ የሚባል ሳይሆን የስራውን አዋጭነት አይተን ነው  ሰዎችን የምንመድበው ሲሉ አክለዋል።

“ሰው ሲጋጭ ደስ ይልሃል የተባለውን አልቀበለውም” ብለዋል።   “ስራ ሲሰራ በግድ መሆን ባለበት ቀን ሊሰራ አይችልም፤ ችግሮች አሉ።  የደረሰንን ስልጠና አዳርሰናል፣ ማንንም የምነካ ሰው አይደለሁም፤ ማንንም አልንቅም” ሲሉ ራሳቸውን ለመከላከል ሞክረዋል።

“እምነትን በተመለከተም በእኔ እምነት ሁሉንም እኩል እያስኬዱ ነው ” አቶ ሃይለማርያም፣  የሙስሊሙንም የክርስቲያኑንም ችግሮች እኩል አያለሁ፣ ያለሁት ፖለቲካ ላይ ነው። ብለዋል።

በአቶ ስብሃት ለቀረበባቸው ሂስ ደግሞ ” ስብሃት በጣም ይጮሃል፣ እንዳሞራ ሁሉ ይዞረኛል፣ እዚህ ሳወያይ ሁሉ በጣም ይጮሃል፣ አለቃ መሆን ችግር ነው ብየ ዝም አልሁ። ንግግር ከመልክ ያምራል ይባላልና የተሳሳትኩት ነገር ካለ አርማለሁ።በአባባል ክፈተት ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በማለት በአቶ ስብሃት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል።

አቶ ሃይለማርያም የቀረበባቸውን ሂስ ቢቀበሉም ሌሎች አባሎቻቸው ግን በሂስ አቀባበላቸው ላይ የሰላ ትችት ከመሰንዘር አላገዳቸውም።

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ ዱሌ ” ሃይለማርያም አሁንም ለመማር አልተዘጋጀህም፣ ሰው ከሁለት ነገሮች አያመልጥም፣ ከፈጣሪና ከህሊናው።  ቀኑን ሙሉ በውይይት ፈጅተን የተሰጠን ምላሽ አልተመቸኝም”ያሉ ሲሆን፣  የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ በበኩላቸው “አብዛኛውን ገፍቶታል፣ ወደውስጡ አላስጠጋውም፣ ሁሉን ከተከላከለ በሁዋላ አስተካክላለሁ ብሎአል ” ብለዋል።

ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ደግሞ  ” ከፊሎችን አልነካሃቸውም ፣ መኮርኮምም አይቸብሃለሁ፤ ይሄ ከአንድ የአገር አመራር አይጠብቅም” ያሉ ሲሆን፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ  ደግሞ ” አቀባበሉ ላይ ዞሮ ዞሮ ላንተ ነው የሚጠቅምህ፣ እዚህ አገር ላይ የሆነ አሻራ ብታሳርፍ ያንተ ስም ነው የሚነሳው ፣ ፍቅርንና የመተባበር መንፈስን ብትዘራ ጥሩ ነው።” ብለው ምክር ለግሰዋቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ደግሞ ” ሁሉንም ጥያቄዎች ሳያቸው በወቅቱ መፈታት ይችሉ ነበር። ነገ የተሻለ አማራጭ እንዲኖረን እነዚህን ወስደህ ማረም አለብህ። የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ አመራር ማሰሩን በተመለከተ ትእዛዙ የመጣው ከላይ ነው። ባይሰራው ኖሮ ነበር የምጠይቀው” በማለት ውሳኔ የሚወስን ሌላ ሃይል እንዳለ ፍንጭ ሰጥተዋል።

አቶ ደሴ ዳልኬ ደግሞ ” በከፍተኛ አመራሩ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ችግር ምንድነው የሚለውን ለይቶ የመፍታት ነገር ቢጠናከር” የሚል ሃሳብ ሲሰነዝሩ፣  አቶ አረከበ እቁባይ  የአቶ ደሴን ሃሳብ በመደገፍ  ” ጠንካራ ጎኑ እንዳለ ሆኖ መስተካከል ካለበት ነገር አንዱ ነገሮችን

ጠቅልሎ መያዝ ላይ ነው። በአሰራራችን መሰረት ሚኒስትሩ የራሱን ስራ ፣ የክልል አመራሮችም ያራሳቸውን ስራ መስራት አለባቸው። ያንን ማስተካከል ያለብህ ይመስለኛል።” ብለዋል።

አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው “ቸልተኛ መሆንህና በችግሮች ልክ ቶሎ ምላሽ አለመስጠትህ በተለይ ከራሱ ጠባቂዎችና ከቤተመንግስት ደህንነቶች ጋር እንደፈለገ እንዲጨፈርብን አድርጎናል። እዚህ ላይ  ብታስተካክል ጥሩ ነው። ሌሎችን ጉዳዮች በተመለከተ ራሱ ባለቤቱ

ነው መሙላትና መጨነቅ ያለበት” ሲሉ የድጋፍ አይሉት የተቃውሞ አስተያየት ሰጥተዋል።

አቶ ሃይለማርያምም በመጨረሻ የቀረበባቸውን ሂስ እንደሚያስተካክሉ ተናግረው ግምገማው አብቅቷል።   አቶ ሃይለማርያም የ ቢ ደረጃ ማግኘታቸውን ከቃለጉባኤው ግምገማ  ውጤት ያሳያል።


የአሜሪካ መንግስት በደቡብ ሱዳን ላገረሸው ጦርነት የሳልቫኪርን መንግስት ተጠያቂ አደረገ

$
0
0

ጁባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ፣ በዩኒቲ ግዛት የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት ጥቃት በሲቪሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
ተቃዋሚዎች አጽፋዊ እርምጃ በመውሰድ ጦርነቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ መግለጫው ጠይቋል።
የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር እስካሁን ውጤት ሊያመጣ ባለመቻሉ የሚፈናቀሉ ደቡብ ሱዳናውያን ቁጥር ጨምሯል። እስካሁን ባለው መረጃ ከ300 ሺ ያላነሱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ተፈናቅለዋል።

በቡሩንዲ የተካሄደው መፈንቅለመንግስት ውጤት አሁንም አልለየለትም

$
0
0

ፕሬዚዳንት ኑኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ጊዜ ለመመረጥ መወሰናቸውን ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ መፈንቅለመንግስት ከተቀየረ በሁዋላ፣ አገሪቱ በምን ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም።
የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ዋና ዋና የሚባሉትን ተቋማት በተለይም የሬዲዮ ጣቢያ፣ አየር መንገዱንና ቤተመንግስቱን በመቆጣጠር መፈንቅለ መንግስቱ እንደከሸፈ ቢያስታውቁም፣ መፈንቅለመንግስቱን የሚደግፉ ሃኢሎች በበኩላቸው፣ ተቋማቱ በእነርሱ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ እየገለጹ ናቸው።
መፈንቅለመንግስቱ ያልተሳካ መሆኑን የሚያመላክቱ ፍንጮች በመታየት ላይ ቢሆኑም፣ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ለጉብኝት ከሄዱበት ታንዛኒያ ወደ አገራቸው ለመመለስ ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
በዋና ከተማዋ ውስጥ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነው። መፈንቅለመንግስቱን በመደገፍ በርካታ ዜጎች ወደ አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረትም ሆኑ ምእራባውያን ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ በመፈንቅለመንግስቱ ዙሪያ አስተያየት አልሰጡም።

”ወጣቱ ስርዓቱን እንደማይፈልገው በምርጫ እንቅስቃሴው ወቅት አሳይቷል”አሉ

$
0
0

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲዊ አንድነት መድረክ ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2007 ዓ.ም በጃንሜዳ የተጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ አስመልክቶ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በህዝቡ በኩል በተለይ ወጣቱ መንቀሳቀሱን ይሁን እንጅ ብዙ ቦታዎች ላይ የምርጫ ሜዳው መዘጋቱን ገልጸዋል። ህዝቡ በስሜት ስብሰባዎችን መሳተፉን የገለጹት ዶ/ር መረራ ፣ በምርጫው መቀመጫ ባይገኝ የህዝቡን ትግል ወደ አንድ እርምጃ ለመውሰድ በሚደረገው ሙከራ በብዙ ቦታዎች ላይ ይህን ለማድረግ የቻልን ይመስለኛል ብለዋል። ህዝቡ በተለይ ወጣቱ ” ኢህአዴግን በቃ፣ ኢትዮጵያን የስደተኞች አገር አታድርጋት” የሚሉና ሌሎችንም መልእክቶችን በጋለ ስሜት ማስተላለፉን ዶ/ር መረራ ተናግረዋል።
የፌታችን ቅደሜ በሚካሄደው የመድረክ ህዝባዊ ስብሰባ እስከ 50 ሺ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። መድረክ መስቀል አደባባይ ላይ ሰልፉን ለማድረግ ፈቃድ በማጣቱ ጃንሜዳ ለማድረግ ተገዷል። በዚህ ሰብሰባ ላይ ህዝቡ ድምጹን እንዳያሰርቅ መልክት እንደሚተላለፍ ዶ/ር መረራ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ዜና የአዲስ አበባ መስተዳድር በስራ ላይ የሚገኙ 200 መኪኖችን ለአዲስ አበባ ፖሊስ እንዲያስረክብ ታዟል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት 6 ወራት ልዩ በጀት ተመድቦለት ሲንቀሳቀስ ቢቆይም፣ ሰሞኑን ለፀጥታና ደህንነት አገልግሎት የሚውሉ ከ200 በላይ መኪኖችና ሹፌሮች እንዲዘጋጁለት ለመስተዳድሩ ጥያቄ አቅርቦ ፣ የከተማው አስተዳደርም በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ፣ መኪኖቹ ከነነዳጃቸውና የሹፌር አበል ጭምር በመሸፈን ለአዲስ አበባ ፖሊስ እንዲያቀርቡ ሰርኩላር ደብዳቤ ልኳል።
ከፖሊስ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር በየደረጃው ላሉ የፖሊስ የአመራር አካላት ባስተላለፉት ትእዛዝ በምርጫ 97 ወቅት አስጊ የነበሩ ቦታዎች፣ እንዲሁም ልዩ ክትትል የሚፈልጉ አዳዳስ ቦታዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት መኖሪያ አካባቢዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎችና ህዝብ የሚበዛባቸው ተቋማት፣ 4 ኪሎ፣ 6 ኪሎ፣ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን እንዲሁም ሌሎች ክ/ከተሞች፣ ወረዳዎችና መንደሮች እንዲለዩና ለተለዩትም አካባቢዎች ልዩ ታጣቂ ሃይል እንዲመደብላቸው እንዲሁም “እግር በእግር በአፋጣኝ መረጃ እንዲላክላቸው ጠይቀዋል።
ከምርጫው ዜና ሳንወጣ ኢህአዴግ በመላ ሃገሪቱ ለምርጫ ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገውን ወጪ ከመንግስት ባጀት/ካዝና/ በከፍተኛ መጠን እየተጠቀመ ሲሆን፣ የመንግስት ንብረት የሆኑና ለምርጫ ቅስቃሳ የሚያግዙ ባለድርብ ተግባር የመስክ ተሽከርካሪዎች ፣ ፒክ አፕ መኪና፣ሚኒባስ እና ሞተር ሳይክል፣ ከፍተኛ፣አነስተኛና መለስተኛ የህዝብ አውቶቢሶችን ፣ የመንግስት ሠራተኛውንና ህዝቡን በኢህአዴግ የለሙ መሰረተ ልማቶችን ለማስጎብኘት በሚል ለማጓጓዝ ተግባር እየዋሉ ነው። በመንግስት ወጪ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ያዘሉ የህትመት ውጤቶች፣ ኮፍያዎች ፣ባነሮችና ቲሸርቶች ና ፖስተሮች እንዲዘጋጁና ለኢህአዴግ ደጋፊ ለሆኑና ላልሆኑ የማህበረሰቡ ክፍል በሰፊው እንዲሰራጩ እየተደረገ ነው፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ የመንግስት ተሽከርካሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥራቸው ኮድ 4 የሆነውን ወደ ኮድ 2 እና 3 በመቀየር ገዢው ፓርቲ በሰፊው እየተጠቀመባቸው ነው፡፡
ከምርጫው ዘገባ ሳንወጣ በአዲስ አበባ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች መታሰራቸውን ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል።
ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መረጃ ግንቦት 5/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲና በወረዳ 19 የፓርቲው ዕጩ የሆኑት አቶ ኑሪ ሙደሲርን የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮች ሲለጥፉ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ በቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩት ምስጋናው ዘመነ፣ ምስረ ጣሂር፣ አብዩ ይታየው፣ ጥላሁን ኃ/ሚካኤል፣ መልካሙ አወቀና ተፈራ በውቄ ናቸው፡፡ ምስጋናው ዘመነና ምስረ ጣሂር የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሲሆኑ ሌሎቹ ደጋፊዎችና ቅስቀሳውን ሲያግዙ የነበሩ መሆናቸውን ፓርቲው ጠቅሷል።
“የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ምስጋናው ዘመነ እና ምስረ ጣሂር ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመናቸው ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በእስር ላይ ይገኛሉ” ሲል አክሏል።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መሪ የነበሩት አቶ ማሙሸት አማረ ግንቦት5 ረፋዱ ላይ በአዲስ አበባ ፖሊሶች ተይዘው መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
በትናንት ዘገባችን በጎንደር አቶ አዋጁ አቡሃይ አደመ እና አቶ አዳነ ባብል ታደሰ የተባሉት ሁለት ግለሰቦች በጸጥታ ሃይሎች መታሰራቸውን የዘገብን ቢሆንም ቶ አዳነ ባብል ታደሰ አለመታሰራቸውን ከቤተሰቦቻቸው ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን፣ አቶ አቡሃይ አደማ ግን አሁንም በእስር ላይ መገኘታቸውን አረጋግጠናል። አቶ አዳነ ባብል ታደሰ እንደታሰሩ ተደርጎ የቀረበው ዜና ስህተት በመሆኑ ይቅርታ እንጠይቃለን።
በመላ አገሪቱ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ ምርጫውን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የህዝብ አመጽ አስቀድሞ ለማምከን የወሰደው እርምጃ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከአዋሽ አርባ 3 ኪሎሜትር ርቆ በሚገኝ ገጠራማ ቦታ ላይ ታስረው ይገኛሉ።

በቴፒ 5 ሰዎች ተገደሉ

$
0
0

በጋምቤላና ደቡብ ክልል ድንበር አካባቢ የሪ በምትባል ቀበሌ 7 ሰዎች በተገደሉ ማግስት ሌሎች 5 ሰዎች ደግሞ በቴፒ ከተማ እንድሪስ ቀበሌ ውስጥ ከሌሊቱ 8 ሰአት ላይ በጥይት ተደብድበው መሞታቸውን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ከሟቾቹ መካከል አባትና ልጅ ይገኙበታል። ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ ገዳዮቹ ፖሊሶች ናቸው። ነዋሪዎች እንደሚሉት ሰዎቹ ይተገደሉት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን ያስጠጋሉ፣ ይደግፋሉ ተብለው ነው። ኢሳት ለከተማው ፖሊስ በመደወል ለማጣራት ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካም።
ኢሳት ከሶስት ቀናት በፊት “ከመስከረም ወር ጀምሮ በቴፒና አካባቢዋ ያለው ግጭት ተባብሶ በመቀጠሉ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ላይ መውደቃቸውንም፣ በእየለቱ በከተማዋ ውስጥ የጥይት ድምጽ እንደሚሰማና በርካታ ቁጥር ያላቸው የሸኮ መዠንገር ነዋሪዎች እየፈለሱ ወደ ቴፒ ከተማ በመግባት ላይ መሆናቸውን ” ዘግቦ ነበር።
ነዋሪዎች ጸጥታውን የሚያስከብርልን ሃይል አጥተናል በማለት በተደጋጋሚ አቤቱታ ያሰማሉ።

በሜሮን አለማየሁና ዳዊት አስራደ ላይ የ2 ሳምንት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ

$
0
0

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም የአይ ኤስ አይ ኤስን ድርጊት ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ
በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም ተይዛ የታሰረችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሜሮን አለማየሁ እንዲሁም በሰልፉ ወቅት ከተያዘ በኋላ በ25 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ እንደገና የታሰረው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት
አባል የነበረው ዳዊት አስራደ ግንቦት 7/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል።
ሜሮንና አቶ ዳዊት ሚያዝያ 5/2007 ዓ.ም ንፋስ ስልክ ላፍቶ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስት እንዲወጡ ተፈቅዶላቸው የነበር ቢሆንም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በማዛወር በእስር ላይ እንዲቆዩ
አድርጓል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል፡፡
ሁለቱም እስረኞች የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ አለኝ በማለቱ ፍርድ ቤቱ ለግንቦት21 ቀጠሮ ሰጥቷል።

ኢህአዴግ በዜጎች ላይ ፍርሃት በመልቀቅ እንዲመረጥ እያግባባ ነው ሲሉ የባህርዳር ነዋሪዎች ተናገሩ

$
0
0

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘጋቢያችን በላከችው ሪፖርት የገዢው መንግስት ካድሬዎች በየመንደሩ በመዞር የሚደርጉት የምርጫ እንቅስቃሴ የነዋሪዎችን ነጻነት ከማሳጣቱ በተጨማሪ፣ ኢህአዴግ በሚጠራው የመንደር ስብሰባዎች የሚቀር ሰው የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ተብሎ ይመዘገባል።

የገዢው ፓርቲ አባላትና የቀበሌ አመራሮች በየሰፈሩ በሚያደርጉት ስብሰባ በአካባቢው የሚኖሩ ባለሃብቶችን ያለ ፈቃዳቸው ለዕለቱ የሚስፈልገውን ለቡና፤ዳቦ እና ቆሎ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ በመቀበል በሰፈሩ በመዘዋወር እንዲሰባሰቡ የሚያደርጉ
ሲሆን፣ የሚዘገዩ ሰዎችን ስልክ በመደወል ‹‹ ለምን አልመጣችሁም?›› ፣ ‹‹ ጸረ ህዝብ ስራችሁን አቁሙ!›› በሚሉ ማስፈራሪያዎች ገዢውን መንግስት እንዲመርጡ ለማድረግ እየጣሩ ነው።

በየመንደሩ የሚካሄዱት ስብሰባዎች በየሶስት ቀኑ የሚቀጥሉ መሆኑን ያስታወቁት የገዢው መንግስት ካድሬዎች በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ጫና በመፍጠር ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና ደግሞ አምስቱ የኢህአዴግ አጋር ተብለው የሚታወቁ ክልሎች ማለትም ሶማሌ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሃረሪ ቅዳሜ በአዲስአበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማዕከል በመገኘት ለኢህአዴግ ያላቸውን አጋርነት ከማረጋገጥ አልፈው በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደሰማያዊ ፓርቲ ያሉትን ፓርቲዎች ያወግዛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ኢህአዴግ በወጣት ሊጉ አማካይነት በአዲስአበባ በየክፍለከተማው ወጣቱ ኢህአዴግን እንዲመርጥ የተለያዩ ቅስቀሳዎችን ሲያደርግ የሰነበተ ሲሆን፣ በብዙ አካባቢዎች ወጣቶች ኢህአዴግን እንደማይመርጡ ፊት ለፊት ከመናገር ጀምሮ ተቃውሞአቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ መሆናቸው ታውቆአል፡፡

ሰሞኑን በየካ ክፍለከተማ በተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ ወጣቶች «ኢህአዴግ ምን ስላደረገልን እንመርጠዋለን» በማለት ጥያቄ ከማቅረብ ጀምረው ሥራአጥነትና የኑሮ ውድነት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር የመሳሰሉ ችግሮችን በማንሳት እንደማይመርጡት በግልጽ ተናግረዋል።

5 በሃይል አማራጭ የሚያምኑ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ውይይት ጀመሩ

$
0
0

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማንኛውም አማራጭ ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች በጋራ ለመታገል የሚያስችላቸውን ውይይት መጀመራቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል።

ውይይቱን የጀመሩት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን)፣ የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ናቸው።

ድርጅቶቹ ” በሂደት ወደ አንድ የምንመጣበትን ሁኔታ እያመቻቸን፣ አሁን ግን አገርና ህዝብን የማዳኑን ስራ እንጀምር በሚል ውይይት እያደረግን መሆናችንን ለኢትዮጵያ ህዝብ መግለጽ እንወዳለን” ብለዋል።

የኢህአዴግን አገዛዝ በሃይል እናስወግዳለን በማለት የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጅቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሰው ሃይልና በሎጂስቲክ እየተጠናከሩ መምጣታቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ስርዓቱ በአገር ውስጥ በሚገኙ ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው አፈና ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር፣ ወጣቶች የትጥቅ ትግል አማራጭን የሚደግፉ ሃይሎችን እንዲቀላቀሉ እያደረጋቸው ነው።


የኢትዮጵያ ብሮድካሲቲንግ ኮርፖሬሽን ለቴሌቪዥን ስርጭቱ ገንዘብ ለመሰብሰብ በተንቀሰሳቀሰባቸው ከተሞች ህዝቡ የቴሌቪዥን ግብር አንከፈልም ሲል ተቃውሞውን እየገለጸ ነው

$
0
0

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተጠናክሮ በደረሰው ሪፖረት ህዝቡ “እኛ ኢቲቪን (ኢቢሲን) አይተን አናውቅም ፤ ለውሸት ጣቢያ ፈፅሞ ክፍያ አንፈፅምም ፤ በአይናችን ያየነውን ለሚክድ ሚዲያ
እኛ ምንም ድጋፍ አናደርግም፡፡ እንደዚህ የሚባል ጣቢያ አለ እንዴ ፤ ኢቲቪ የሚባል ጣቢያ መኖሩን አናውቅም ነበር ” የሚሉ አስተያየቶች ሲሰጡ፣ አንዳንዶች ደግሞ “እኛ ከኢሳት ውጭ ምንም ጣቢያ ሰምተንም አይተንም አናውቅም ፣
ሶሰት አመታት አለፈን” የሚሉ አሰተያየቶች ሰጥተዋል።
ኢቲቪ በሀገሪቱ ያለውን የቴሌቪዥን ቁጥር ወደ ግብር ሰንሰለት ለማሰገባት ያደረገው ጥረትም እንደከሸፈበት በሙሉ ሪፖርቱ ተካቷል፡
አየር ላይ ያለሰሚ እና ተመልካች ከሚባክኑ ጣቢያዎች መሃከል አንዱ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣ የኢሳትን መረጃ የሚጋፋ ሚዛን መያዝ እንደማይቻል ያትታል፡፡
ሀዝቡ ኢሳት ቴሌቪዥንን ለማገዝ ከፍተኛ መነሳሳት እንዳሳየ በዚሁ አጋጣሚ ከተሰበሰበው የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኢቲቪን ( ኢቢሲን) ግብር ለመሰብሰብ ከውሃ ፤ ከቴሌ እና ከመብራት ደረሰኝ ክፍያ ጋር ማቀናጀት እና አዲስ በሚገዙት ላይ የቴሌቪዥን ሽያጭ መደብሮች የውክልና ምዝገባ እንዲያ
ካሂዱ መስጠት እንደሚያስፈልግ የሚጠቁም የመፍትሄ ሀሳቦች በጥናቱ ተካተዋል ፡፡ የኢትዩጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ በጀት የሚተዳደር ሲሆን በአመት እስከ 123 ሚልዩን ብር ከማስታወቂያ የሚሰበሰብ ተቋም ነው፡፡

በሌላ ዜና ደግሞ ኢሳት ስርጭቱን እንደገና በአሞስ ሳተላይት ጀምሯል።ገዢው ፓርቲ አገሪቱን አንጡራ ሃብት በከፍተኛ መጠን በማፍሰስ ኢሳትን ከአየር ላይ ለማስቀረት የሚያደርገውን ጥረት በቀጠለበት በዚህ ወቅት ኢሳት እንደገና በአሞስ
ሳተላይት ወደ አየር መመለሱን የድርጅቱ ማኔጅመንት አስታውቋል፡፡

ኢሳት ለ24 ሰዓታት በSES 5 አማካኝነት ያለማቋረጥ ለሁለት ዓመታት ሲያቀርበው የቆየው ፕሮግራም ከሰኞ መጋቢት 14/2007 ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከተቋረጠ በሁዋላ ፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተደራሽነቱን በማስፋት
በአዲስ ሳተላይት ስርጭቱን ቢቀጥልም፣ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ገጥሞት ከአየር ላይ ወርዷል።

ምንም እንኳ ድርጅቱ አፈናውን ለማስቀረት የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ቢሆንም ፣ በውጭ አገር ታላላቅ መንግስታት በሚደረግ ግፊት ፣ ለሳተላይት ኩባንያዎች በሚቀርብ የገንዘብ ስጦታና እና ከፍተኛ ጥቅም በሚያስገኙ ፕሮጀክቶች
በመደለል፣ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ኢሳት በኢትዮጵያ ምድር እንዳይታይ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።

ማኔጅመንቱ “እነሱ ለአፈና ካላቸው ቁርጠኝነት በላይ እኛም የኢትዮጵያ ሕዝብ የነጻነት ርሃብ ይሰማናል እና ማናችውንም መስዋዕትነት በመክፈል ኢሳት በኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያውያን ድምጽ ሆኖ እንዲቀጥል እንደምንሰራ እያረጋገጥን በአዲስ ሳተላይት እንደገና ስርጭታችን ” መቀጠሉን እናስታውቃለን ብሎአል፡፡

አዲሱ ሳተላይት የሳህን አቅጣጫ በከፊል ማስተካከል የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ሕዝቡ የችግሩን ስፋት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህንኑ እንዲፈጽም እንዲሁም በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ነጻነት ወዳዶች ሁሉ ኢሳት በተጨማሪ ሳተላይቶች ጭምር ስርጭቱን ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ማኔጅመንቱ አቅርቧል።

አዲሱ የሳተላይት ስርጭት
Amos,
Frequency 12335 vertical,
symbol rate 27500 (27.5) , FEC 3/4
17 degree east
ሲሆን ኢትዮጵያውያን መረጃውን በማሰራጨት ከኢሳት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

ኢሳት በAB 7 ሳተላይት ላይ የ 24 ሰዓታት የራዲዮ ዝግጅት በማቅረብ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያዉያን የፀሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት ተካሄደ

$
0
0

በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ እና አካባቢዋ ያሉ አብያተ ክርስቲያንናት እንዲሁም የተለያዩ የሲቪል ድርጅቶች በቅርቡ በየመን፥ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመዘከር እሁድ እለት በዚህ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ የመታሰቢያ ዝግጅቶችን አካሄዱ።

ነዋሪነታቸው በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ በርካታ ኢትዮጵያዊን በታደሙበት በዚህ ዝግጅት፥ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ሟች ኢትዮጵያዊያንን አስመልክቶ ያስተላለፉት የሀዘን መልክት ተነቧል። ልዪ የጸሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት በተከናወነበት በዚሁ ዝግጅት፥ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፥ ከኢትዮጲያ የሙስሊም እምነት ተወካዮች፥ ከመካነ-እየሱስ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን፥ እንዲሁም ከአለምአቀፍ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የተወከሉ የሀይማኖት አባቶች የሃዘን መግለጫ መልክት ማስተላለፋቸውን ከስፍራው የደረስን መረጃ አመልክቷል ።

ለግማሽ ቀን ያህል በተከናወነው በዚሁ የመታሰቢያ ዝግጅት ወቅት ከዋልድባ ገዳም ማህበር ፤ ከዲሲ ሜትሮ ግብረ-ሀይል እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያዊንን በማስመልከት የተሰማቸውን ሀዘን እንደገለጹ ታዉቋል።

በእለቱም ለሟች ቤተሰቦች ድጋፍ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሂዶ ከ ፬ ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ታውቋል።

በቅርቡ በሊቢያ፥ የመንና፥ ደቡብ አፍሪካ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን በማስመልከት ነዋሪነታቸው በዚሁ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶችና የተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያከናውኑ መቆየታቸው ይታወሳል።

በጋምቤላ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዉ ህይወት ጠፋ

$
0
0

በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ አካባቢ ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት አምስት ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል ።

በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ማጣታቸውን የሚናገሩት የወረዳው ነዋሪዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ጥያቄዎችን ባነሱ ነዋሪዎች ላይ የሚወስዱት እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል ።

በተለይ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከሚካሄድውን ምርጫ ጋር በተያያዘ ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት እማኞች፥ ከተገደሉት አምስት ሰዎች በተጨማሪ ሁለት ነዋሪዎች ከባድ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ለህክምና ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል።

በወረዳው የሚገኙ የእርሻ መሬቶች ኢንቨስተሮችን ለመሳብ በሚል ሰበብ ነዋሪዉን በማፈናቀል ለባለሀብቶች የሚሰጠው ውሳኔ በነዋሪዎች ዘንድ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያሥነሳ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በቅርቡ መሬታቸውን ለፖለቲከኛ ሹመኞች መሰጠቱን በተቃወሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ መንግስት የተቀነባበረ ጭፍጨፋን ማከናወኑን ነዋሪውች ይገልጻሉ ።

በአዲስ መልክ በጎደሬ ወረዳ ሜጢ አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት አስመልክቶ ከክልሉም ሆነ ከፌደራል መንግስት የተስጠ ምላሽ የለም።

የምርጫ ገጠመኝ

$
0
0

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እየተዋከቡ፣ እየታሰሩና ደብደባም እየተፈጸመባቸው መሆኑን በየጊዜው የሚደርሱን መረጃዎች
ያሳያሉ።
የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች አንድ ጊዜ የቡና ሌላ ጊዜ የእድር እያሉ በተለይም እናቶችን እየሰበሰቡ ኢህአዴግን እንዲመርጡ፣ ልጆቻቸውንም አመጽ እንዳያስነሱ እንዲመክሩ ለማግባባት ይጥራሉ።
መራጮች በኢህአዴግ ካድሬዎች የቅስቀሳ መንገድ መማረራቸውን ከመግለጽ ውጭ ፣ ይህ ነው የሚባል እርምጃ ሲወስዱ አይሰማም። ሰሞኑን አንድ የአዲስ አበባ ወጣት የወሰደው እርምጃ ጥላቸው የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ነው።
አንድ የኢህአዴግ ካድሬ የኢህአዴግ ምልክት የሆነውን የንብ ቲሽርት ለብሳ በየመንደሩ እየዞረች፣ ቤት ለቤት እያንኳኳች ኢህአዴግን ምረጡ ትላለች። ካድሬዋ አንድ ወጣት ቤት ስትደርስ፣ ወጣቱ “ምን ልታደርጊ መጣሽ?” ይላታል።
እሷም በድፍረት መለሰችለት። በመልሷ የተበሳጨው ወጣት ” ድርጅትሽ ቆሻሻ! አሁንስ በጣም ጠገባችሁ!” የሚሉና ሌሎችንም ስድቦች ከሰደባት በሁዋላ፣ በንዴት አንገቷ አካባቢ ሲመታት ወጣቷም መሬት ላይ ወደቀች። ካድሬዋም
ከሰአታት በሁዋላ ነፍስ ዘርቶባት ከመቶት ተርፋለች። እንዴት ተደፈርን ያሉት የኢህአዴግ ካድሬዎች፣ ወጣቱን ለመያዝ አሰሳውን አጠናክረውታል። ዘጋቢያችን ይህን ዜና እስካጠናከረበት ሰአት ድረስ ወጣቱ አልተያዘም።

ወጣት እስማኤል ዳውድን ጨምሮ 18 ተከሳሾች ላይ ክስ ተመሰረተ

$
0
0

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት አይኤስን ለማውገዝ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል የተባሉትና በወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት ተከሳሾች ላይ መደበኛ
ክስ ተከፈተ።
በዚህም መሰረት የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ አምደኛና የአንድነት አባል የነበረው ወጣት እስማኤል ዳውድን ጨምሮ በሌሎች 18 ተከሳሾች ላይ የፌደራል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።
በወንጀል ዝርዝሩ ላይ ተከሳሾቹ ‹‹ቤተ መንግስት አካባቢ በቡድን በመሆን መፈክር በመያዝና በቃል በመናገር “ተነስ! በለው!”ጊዜው ዛሬ ነው አትነሳም ወይ፣ የሞተው ሬሳ ያንተ አይደለም ወይ? መንግስቱ ሀይለማርያም ይምጣልን!
ከኢህአዴግ አይ ኤስ ይሻለናል!፣ ወያኔ ሌባ!፣ ውሸት ሰለቸን!፣ ዝምታ ይብቃ!፣ እናት ኢትዮጵያ ያደፈረሰሽ ይውደም!” በማለት ሁከትና ብጥብጥ ፈጥረዋል ተብሏል።
እንዲሁም መፈክሮችን በመያዝ እና ወደ ፀጥታ ሀይሎች ድንጋይ በመወርወር ሰልፉን አውከዋል ያለው አቃቤ ህግ፤ “በዋና ወንጀል አድራጊነትና ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ወንጀል- በቡድን ስብሰባን በማወክ ወንጀል›› መከሠሳቸውን
አስረድቷል።
ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ያሉት ተከሳሾች ስድስት ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን፤ በሌሎቹ 14 ተከሳሾች ላይ ሁለት ክስ እንደቀረበባቸው የክስ ቻርጁ ያትታል።
ዐቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ 21 የሰው ምስክር 6 የሰነድ ማስረጃና ሁለት ኤግዚቢቶችንም አቅርቧል።
ከተከሳሾቹ ውስጥ ከ1ኛ ተከሳሽ፣ 2ኛ ተከሳሽ፣ 3ኛ ተከሳሽ፣ 6ኛ ተከሳሽ፣ 11ኛ ተከሳሽ 12ኛ ተከሳሽ የሰጡት የእምነት ቃል በሰነድ ማስረጃነት ቀርቧል።
በኤግዚበትነት “ከአባይ በፊት የህዝብ እንባ ይገደብ” እና “ዝምታ ይብቃ” የሚሉ መፈክሮችን የያዙ ሳምፕሎችም በ ኤግዚቢትነት ተያይዘው ቀርበዋል።
ይሁንና ከሚያዚያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የሚገኘው ወጣት እስማኤል ዳውድ፣ ከትላንት በስቲያ ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ
ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ዐቃቤ ህግ በሰነድ ማስጃነት ያቀረበው ቃል የእሱ አለመሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡
‹‹የሰጠሁት ቃል የኔ አለመሆኑን በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ 3 መርማሪዎች ከማረፊያ ቤት ሌሊት 7፡30 አካባቢ ጠርተውኝ እዚህ ወረቀት ላይ ባትፈርም እየተፈራረቅን እናድርብሃለን በማለት በከዘራ እየመቱ ያስረሙኝ መሆኑን
ፍርድ ቤቱ እንዲገነዝብልኝ›› ሲል እስማኤል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታውን አቅርቧል።
ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአንድ መዝገብ ውስጥ ከሚገኙት 19 ተከሳሾች ውስጥ ወጣት እስማኤልን ዳውድን ጨምሮ ሌሎች አራት ተከሳሾች በድምሩ አምስት ተከሳሾች የዋስትና መብት ተነፍጓል።
እንዲሁም አስራ አራቱ ተከሳሾች የተጠየቀባቸውና የዋስትና ገንዘብ ብር 10000 በሲፒኦ አሰርተው ገቢ ቢያደርጉም አቃቤ ህግ በጠየቀው ይግባኝ የተነሳ ተከሳሾቹ ገንዘቡን አስይዘው ወደ ማረፊያ ቤት እንደተመለሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የስኳር ፕሮጀክቶች በፋይናንስ ችግር ምክንያት ሳይሳኩ ቀሩ

$
0
0

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች መካከል የስኳር ፕሮጀክቶች በዋነኛነት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እንዳልተሳኩ ከስኳር ኮርፖሬሽን
የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡
በሰኔ ወር 2007 መጨረሻ የሚጠናቀቀው የአምስት ዓመት መርሃግብሩ ከተያዙት ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ለፕሮጀክቶቹ ተስፋ ተጥሎባቸው የነበሩት አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ ሊሰጡ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ዕቅዱ
ሙሉ በሙሉ ማሳካት ሳይቻል መቅረቱን አመልክቷል፡፡

ከተያዙት ፕሮጀክቶች መካከል ኩራዝ፣ ተንዳሆ፣ በለስ፣ ወልቃይት፣ አርጆ ደዴሳ፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ የፊንጫአ፣ ወንጂ/ሸዋ እና መተሃራ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙበት የሚታወቅ ነው፡፡
ምንጮች እንደሚሉት ፕሮጀክቶቹ ብድር ባይገኝላቸውም በአብዛኛው በሀገር ውስጥ ከሚገኝ ባንኮች ብድር በጀት ስራቸው የተጀመረ ሲሆን አብዛኛውን የፕሮጀክቶቹን ሥራዎች ልምድ የሌለው በመከላከያ ወታደሮች የሚመራው የብረታብረት
ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ያለአንዳች ውድድር እንዲይዘው ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ፕሮጀክቶቹ በወቅቱና በተያዘላቸው በጀት የመጠናቀቃቸው ጉዳይ በባለሙያዎች ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል።

በሜቴክ ስር እየተሰሩ ላሉ ፕሮጀክቶች የ2007 በጀት ዓመት ከስኳር ልማት ፈንድ እና ከሀገር ውስጥ ብድር ለበለስ አንድ እና ሁለት 4 ነጥብ 26 ቢሊየን ብር፣ ለኩራዝ አንድ 2 ነጥብ 34 ቢሊየን ብር በድምሩ 6 ነጥብ 56
ቢሊየን ብር እንዲሁም ለተንዳሆ ምዕራፍ ሁለት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ 290 ነጥብ 76 ሚሊየን ብር፣ ለከሰም ብር 562 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ፣ ለወንጂ ማስፋፊ ፕሮጀክት ቀሪ ክፍያ 608 ነጥብ 33 ሚሊየን ብር በውለታ
የሚከፈል፣ ለመለዋወጫ የሚከፈል 175 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በጠቅላላው 7 ነጥብ 26 ቢሊየን ብር የተጠየቀ ሲሆን፣ በያዝነው በጀት ዓመት 1 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር እንደተከፈላቸው መረጃው ያመለክታል።

በሶማሊ ክልል በደረሰው ድርቅ ከ2 ሺ በላይ የቤት እንስሳት አለቁ

$
0
0

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች የመስክ ጉብኝት በማድረግ ባወጡት ሪፖርት በሲቲ ዞን ባለፈው ወር ብቻ በተከሰተው ድርቅ ከ2 ሺ በላይ በጎችና ፍየሎች ሲያልቁ ነዋሪዎችም እየተሰደዱ ነው።

በረሃቡ ምክንያት በሃዲጋላ ወረዳ ጉርጉር ቀበሌ በጎች የሌሎችን በጎች ቆዳ ሲበሉ መታየታቸውን በስእል የተደገፈው ሪፖርት ያሳያል።

አይሺያ፣ ሃድሃጋላ፣ ከፊል ሽንሌ፣ ከፊል ደምበል፣ ሰሜን ኤረር፣ ከፊል አፍዴም እና መኢሶ በድርቅ የተጠቁ አካባቢዎች ተብለው ተለይተዋል።
በሽንሌ፣ ሃዲጋላና አይሺያ ወረዳዎች እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቤት እንስሳት ያለቁ ሲሆን፣ ነዋሪዎችም ድርቁን በመሸሽ የተሻለ ምግብ ወደ ሚያገኙበት ቦታ ፈልሰዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።

አለማቀፍ ማህበረሰቡ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር በመሆን እርዳታ ለማድረስ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል።


የኢሳት የአሞስ ስርጭት እንደገና ታፈነ

$
0
0

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት በናይል ሳት ሲያስተላልፈው የነበረው ስርጭቱ በ2 ሳምንታት ውስጥ የኢህአዴግ አገዛዝ ባሳደረው የዲፕሎማሲ ጫና ከአየር ላይ እንዲወርድ ከተደረገ በሁዋላ፣ በአሞስ ስርጭቱን
ቢጀምርም፣ ከአገሪቱ በሚለቀቀው ሞገድ እንደገና በመታፈኑ ከአየር ላይ እንዲወርድ ተደርጓል።

ኢሳት ባለፉት 5 አማታት 8 የሳተላይት ጣቢያዎችን እየቀያየረ ስርጭቱን ሲያቀርብ ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢሳትን ለማፈን የሚታየው የዲፕሎማሲ ዘመቻ፣ አገዛዙ በኢሳት ስርጭት ክፉኛ መደናገጡን እንደሚያሳይ አስተዳደሩ ገልጿል።

የኢሳት አስተዳደር ሌሎች የሳተላይት ጣቢያዎችን በማፈላለግ ላይ ሲሆን፣ እንደተሳካ ለውድ ተመልካቾች ያስታውቋል። በኢሳት ሬዲዮ ላይም የአፈና ሙከራ እየተደረገ በመሆኑ ስርችቱ አልፎ አልፎ እየተቋረጠ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች
ያሳያሉ።

አንድ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ተገደለ

$
0
0

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖረው የ25 ዓመቱ ሲሳይ ተሾመ በቅጽል ስሙ ገብሬ ያለፉትን 8 ዓመታት በቃሊቲና በዝዋይ እስር ቤቶች እየተመላለሰ አሳልፏል።
በተለይ ወደ ዝዋይ እስር ቤት ከተላለፈ በሁዋላ ፣ ሃጎስ የተባለው የእስር ቤቱ ሃላፊ ” አንተ የነፍጠኛ ልጅ እንበቀለሃለን፣ በእኔ እጅ ነው የምትሞተው” እያሉ ይደበድቡትና ይዝቱበት ነበር። ባለፈው ቅዳሜ እናቱ ሊጠይቁት ሲሄዱ፣ ታሞ
ሚኒሊክ መወሰዱን ይነግሩዋቸዋል። ወደ ሚኒሊክ ሲሄዱ፣ በአንድ አምቡላንስ ውስጥ ጎንና ጎኑ በኤሌክትሪክ ተጠብሶ፣ ኩላሊቱ አካባቢ ተረጋግጦና በልዞ፣ አናቱ አካባቢ ያረፈበት ድብደባ ፊቱን ለማየት በማይቻል ሁኔታ በደም እንዲሸፈን
አድርጎታል።
የደረሰበትን ጉዳት ለመግለጽ ይዘገንናል የሚሉት ቤተሰቦቹ፣ ፖሊሶች አንዴ ታሟል፣ ሌላ ጊዜ ጉዳዩ በአቃቢህግ ተይዟል በማለት ለመደናገር እየሞከሩ ነው። የ22 አካባቢ ወጣቶች የሟቹ ቲሸርት ያለበትን ፎቶ እያሳተሙ ነው። ፖሊሶችና ደህንነቶች በድንካኑ አካባቢ እየተዘዋወሩ በመቆጣጠር ላይ ናቸው። የሟች የቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደን እያሉ ነው ። ከቤተሰብ አባላት ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል

በትጥቅ ትግል ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ድርጅቶች የጥምረት ስምምነት ተፈራረሙ

$
0
0

በገዢው የኢህአዴግ መንግስት ላይ የትጥቅ ትግልን እያካሄዱ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ወደ ጥምረት እና ውህደት የሚወስዳቸውን ውይይት መጀመራቸውን ባለፈዉ አርብ ይፋ አደረጉ ።

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፥ የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፥ የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፥ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ነቅናቄ፥ እና የአርበኞች ግንቦት ፯ ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ የጥምረት ብሎም የውህደት ዉይይቶችን መጀመራቸውን አስታወቁ ።

“ሀገርን እና ህዝብን ለማዳን የጋራ ግብ አድርጎ ለመስራት” በሚል መርህ የተዘጋጀውን ውይይት በማካሄድ ላይ መሆኑን ንቅናቄዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል ።

በቅርቡ በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኘው አርበኞች ግንባር፥ ከግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ጋር ውህደት ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አምስቱ ንቅናቄዎች በማካሄድ ላይ ያሉትን ውይይት አስመልክቶ ውጤቱን በቀጣይ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከድርጅቶቹ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ንቅናቄዎቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ከመቼውም ግዜ በላይ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና መከራ ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት ድርጅቶቹ፥ አንድነትን በማጠናከር ሀገርንና ህዝብን ነጻ ማውጣት የሚገባበት ወቅት አሁን ነው ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ አክለው አስታቀዋል።

በ97 ምርጫ የካርተር ማእከል የምርጫ ታዛቢ ዋና አማካሪ የኢትዮጵአን ምርጫ ሂደት አጣጣሉት

$
0
0

ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቴሬንሴ ሊዮንስ በዋሽንግተን ፖስት ላይ “ነጻና ፍትሀዊ ምርጫን ከኢትዮጵያ ጋር ምን አገናኘው?”በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሁፍ በመጪው ግንቦት 16 በ ኢትዮጵያ የሚካሄደው ምርጫ የመርሀግብር ማሟያ እንጂ ትርጉም ያለው እንዳልኾነ ገልጸዋል።
ሂደቱ ከቅድመ-ምርጫ ጀምሮ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዳልነበር በስፋት ያብራሩት ጸሃፊው ”ዜጎች አዲስ መንግስት የማይመርጡበት ትርጉም የለሽ ምርጫ”ሲል አጣጥለውታል።
የአሜሪካ ምክትል የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ወንዲ ሸርማን ኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ሀገር ማለታቸውና በመጪው ሳምንት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀውንም ምርጫ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ብለው ማሞካሸታቸውን ተችተዋል።
ጸሃፊው እንደሚሉት ምርጫው ለውጭ አገር ህጋዊ ተቀባይነት ማስገኛ ተብሎ በየጊዜው ከሚደረግ ይልቅ፣ በአገር ውስጥ ያለውን ህዝብ ለመቆጣጠርና አፈና ጉልበትን ለማሳየት ተብሎ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በጆርጅ ማሶን ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ፀጻፊው ፣ ገዢው ፓርቲ በ2002 ምርጫ ካገኘው ውጤት ያልተናነሰ እንደሚያገኝም ገልጸዋል።

በእስራኤል የሚገኙ የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

$
0
0

ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤተእስራኤላውያን ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ በአገሪቱ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍንና ዘረና የሆነው ፖሊስ እንዲያዝ ጠይቀዋል።
ከሳምንታት በፊት የተካሄደው ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ደም አፋሳሽ ሆኖ ቢጠናቀቅም ፣ የአሁኑ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል።
ከ185 ሺ በላይ ቤተእስራኤላውያን በእስራኤል ምድር የሚኖሩ ሲሆን ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አድሎዎች ይፈጸሙባቸዋል።
ከዚህ ቀደም እናቶች ያለፈቃዳቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ መርፌ እንዲወጉ መደረጋቸው ፣ ኢትዮጵያውያን የለገሱት ደም እንዲደፋ መደረጉ እንዲሁም በቅርቡ ደማስ ፈቃደ በተባለ ወታደር ላይ አንድ ፖሊስ የፈጸመው ድብደባ ኢትዮጵያውያን
በስርአቱ ላይ ተቃውሞ እንዲያነሱ ካደረጉዋቸው ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ ።

Viewing all 2145 articles
Browse latest View live