Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all 2145 articles
Browse latest View live

ቴሌ ኮሚኒኬሽን ከቻይናው ዜድ ቲ ኢ ጋር የ 800 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመ

$
0
0

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  ስምምነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሞባይል ስርጭት ተጠቃሚ ወደ 50 ሚሊዮን ለማሳደግ የተደረገ ነው ተብሎአል።

መንግስት ለዘርፉ ከመደበው 1 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ከፊሉን ለሌላው የቻይና ኩባንያ ሀዋይ መስጠቱ ታውቋል።

ሁለቱም የቻይና ኩባንያዎች የመንግስትን የስልክና የሌሎች የመገናኛ መንገዶች ጠለፋ አቅም እንደሚያዳብሩለት ኢሳት ምንጮችን በመግለጽ መዘገቡ ይታወሳል።

የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ዋልታ በሰራው ዜና ለ80 ሚሊዮን ህዝብ አንድ ብቻ የስልክ አገልግሎት የሚጠጥ ኩባንያ መኖሩን እንዲሁም በአፍሪካ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎትን በመንግስት ቁጥጥር ስር ካደረጉ ጥቂት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኑን ዘግቧል።


በቁጫ ወረዳ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሮአል

$
0
0

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በወረዳው የተነሳውን ከማንነት ጋር የተያያዘ ጥያቄ ለማፈን መንግስት የጀመረውን ዘመቻ በማጧጧፍ ለውጭ አገር ሚዲያ መረጃ ይሰጣሉ የተባሉትን የቁጫን ህዝብ በመወከል ሲከራከሩ የነበሩት መቶ አለቃ ማሴቢ ማዳልቾ፣ ባለፈው ቀድሜ ተይዘው ዛሬ ወደ አርባምንጭ ተልከዋል።

በአጠቃላይ እየታደኑ ካሉት መካከል 12 አንጋፋና ታዋቂ ሰዎች ሲታሰሩ፣ 9ኙ የገቡበት  አልታወቀም።

በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው እንዲሰማራ መደረጉ ይታወሳል።

ለአቶ መለስ ሙት አመት መታሰቢያ የመንግስት ሰራተኞች በግድ እንዲገኙ ታዘዙ

$
0
0

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል በልዩ ልዩ
ፕሮግራም ታስቦ እንደሚውል ለማወቅ የታቸለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ደግሞ  የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ምሽትና ነገ  ሻማ በማብራት እንዲዘክሩት ታዘዋል።

አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች  ኢቲቪ አቶ መለስ ዜናዊ ከተናገራቸው ንግግሮች መካከል እያለ ሲያቀርብ መሰንበቱ እንዳሰለቻቸው ተናግረው፣ የፓርቲው ካድሬዎች በየመስሪያ ቤቱ የሚገኙ ሰራተኞች በግድ ተገኝተው እንዲዘክራቸው ማስፈራሪያ አዘል ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ነሃሴ 7 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ የመለስ ዜናዊ የአረንገዴ ልማት ማዕከል የመሰረት ድንጋይ  በአድዋ
ፓርክ የተጣለ ሲሆን የዚህን ፕሮጀክት ወጪ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳዳር ለመሸፈን ቃል መግባቱን መዘገባችን ይታወቃል።

ከሃያት ሆስፒታል ፊት ለፊት ማረፊያውን የሚያደርገው ማዕከሉ ከ100 ሄክታር በላይ ስፋት ሲኖረው ፥  በተለያዩ
የአረንጓዴ ዕፅዋት በመሸፈን በውስጥ ትላልቅ የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካትታል ተብሏል።

ባለፉት 15 ቀናት የአዲስአበባና የክልል ከተሞች ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች ዕለቱን ለማሰብ የችግኝ
ተከላ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን መንግስትም በዚህ አጋጣሚ የመለስን ሌጋሲ ለማስቀጠል የገባውን ቃል ዳግም
ያደሰበት አጋጣሚ መሆኑን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሲናገር ከርሟል።

አቶ መለስ ዜናዊ ታምመው በሕክምና ሲረዱ መቆየታቸው በከፍተኛ ሚስጢር ተይዞ ከቆየ በኃላ ነሃሴ 14 ቀን 2004
ዓ.ም መሞታቸውን መንግስት በይፋ ማመኑ የሚታወስ ነው፡፡

ገዢው ፓርቲ የአቶ መለስን ሞት ለፖለቲካ ድጋፍ ማስገኛ እየተጠቀመበት ነው በሚል ሲተች ቆይቷል። አቶ መለስ በኢኮኖሚው ዘርፍ መጠነኛ ለውጥ እንዳመጡ ቢነገርላቸውም፣ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት በማዳከም፣ አገሪቱን ወደብ አልባ በማድረግና የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ይወቀሳሉ። በህይወት በነበሩበት ጊዜ በተለይም ኢፈርት የተባለ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ተቆጣጥሮ ዬያዘ የንግድ ኩባንያ እንዲቋቋም በማድረግ አንድን ብሄር ብቻ ለመጥቀም ተንቀሳቅሰዋል እየተባሉ በተቃዋሚዎቻቸው ይተቹ ነበር።

ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመለስን ፋውንዴሽን በበላይነት እየመሩ ይገኛሉ።

የተወዳጁ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ የእዮብ መኮንን የቀብር ሥነ-ስርዓት ነገ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ 9 ፡00 ሰዓት ላይ ይፈጸማል።

$
0
0

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  የኢሳት ወኪል ከስፍራው ባደረሰን መረጃ  አስከሬኑ ዛሬ ንጋት ላይ ተኝቶ ሲታከምበት ከነበረው ከናይሮቢ -ወደ አዲስ አበባ ገብቷል።

እዮብ ከሳምንት በፊት ልጁን በብሽክሊሊት ትምህርት ቤት አድርሶ ከተመለሰ በሁዋላ ቤቱ መግቢያ በር ላይ ሲደርስ ድንገት ሰውነቱ አልታዘዝ ብሎት መዝለፍለፉን የገለጸችው ባለቤቱ ቲና፤ከዚያ እንደምንም የበሩን ደወል ተጭኖ መጥሪያ ካሰማ በሁዋላ መቆም አቅቶት በተደገፈው በር ሸርተት እያለ ወደ መሬት ሲወርድ ደርሰውበት መደንገጣቸውንና በአስቸኳይ በቅርብ ወደሚገኘው ሀያት ሆስፒታል እንደወሰዱት ተናግራለች።

የሀያት ሆስፒአል ሐኪሞች እዮብን ለመርዳት የተሻለ ህክምና ያለው በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል እንደሆነ በነገሯቸው መሰረት በፍጥነት ወደዚያው ቢወስዱትም፤ እዚያም በደም ግፊት ወይም በስትሮክ ክፉኛ የተመታው እዮብ በውጪ አገር የተሻለ ህክምና እንደሚያስፈልገው በተነገራቸው መሰረት  ለህክምና ከተጠየቀው 25ሺህ ዶላር ውስጥ ቅድሚያ 22 ሺህ ዶላር ተከፍሎ በቅርብ ውደሚገኘው ወደናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ሆስፒታል ወስደውታል።

ይሁንና ለቀናት ራሱን የሳተው የ37 ዓመቱ አርቲስት እዮብ ፤ናይሮቢ ሆስፒታል በገባ በማግስቱ እስከወዲያኛው አሸልቧል።

የኢሳት ወኪል ባደረሰን መረጃ መሰረት የእዮብ አስከሬን ዛሬ ጧት 1፡00 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን፤ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ነገ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

ተወዳጁ አርቲስት እዮብ መኮንን የአንዲት የ13 ዓመት ሴት ልጅ አባት ነበር።

የኢሳት ባልደረቦች ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለአድናቂዎቹና በእዮብ ሞት መሪር ሀዘን ለደረሰባቸው ሁሉ መጽናናት ይሆንላቸው ዘንድ ልባዊ ምኞታቸውን በድጋሚ ይገልጻሉ።

 

የቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጠየቀ።

$
0
0

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው የቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ እንጠይቃለን” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ፓርቲያችን አንድነት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከሚታገልላቸውና ገዥው ፓርቲ ከወረቀት አልፎ ያልተገበራቸው ሀገራዊ ቁምነገሮች ውስጥ ዜጎች ሳይሸማቀቁ በነፃነት ሃሳባቸውንና አመለካከታቸውን የመግለፅ፣ በነጻነት የመደራጀት፣ በገዛ ሀገራቸው በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ በፈለጉበት አከባቢ የመኖር፣  የመደገፍ፣ የመቃወም እና  ስለመብታቸው ሳይሸማቀቁ የመጠየቅ  መብቶች እንደሚገኙበት  አመልክቷል።

እንዲሁም በአጠቃላይ የሕግ በላይነት መስፈን፣ የሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቶች መከበር፤ ከዚህም ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ  እና የዜጎችን ዋስትና ማረጋገጥ፤ ፓርቲው ከሚታገልላቸው የዲሞክራሲ ምሰሶዎች ዋነኞቹ መሆናቸውን ገልጿል።

የቁጫ ሕዝብም ያነሳቸው የማንነት፣ የቋንቋ፣ የባህልና የአስተዳደር ጥያቄዎች ከዚህ ተነጥሎ እንደማይታይ የገለጸው አንድነት ፓርቲ፤  የአካባቢው ነዋሪዎች በሠላማዊ መንገድ፣ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ጥያቄያቸውን ለመንግሥት ቢያቀርቡም የተሰጣቸው ምላሽ እስርና ማስፈራሪያ መሆኑ ፓርቲያችንን አሳዝኖታል ብሏል።

ከግንቦት 28 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ የሆነው ነገር የዜጎችን ህጋዊ ጥያቄ በሕገ-ወጥነት መቀልበስ መሆኑን መካድ አይቻልም  ብሏል አንድነት።

በጅምላ የታሰሩትና አሁንም እስር ላይ የሚገኙት ህጋዊና ሰላማዊ ዜጎች መሆናቸውን ያመለከተው አንድነት፤  ፓርቲያችን ጉዳዩን በቅርበት ተከታትሎ እንዳጣራው በርካቶች በጅምላ የታሰሩበት ምክንያት፦” ልጆቻችን አፋቸውን በፈቱበት ቋንቋ ይማሩ፣ በስማችን ልንጠራ ይገባናል፣ የማንነት ጥያቄያችን ምላሽ ያግኝ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ይረጋገጥ፣ የልማት ጥያቄያችን ምላሽ ያግኝ የሚሉና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን የመብት ጥያቄዎች በማንሳታቸው  እንደሆነ ገልጿል፡፡

እነዚህን የዜጎች ተፈጥሯዊና ህጋዊ መብቶች ስርዓቱ “አረጋግጫቸዋለሁ” በሚላቸውና በቁጥጥር ስር ባደረጋቸው ሚዲያዎቹ የሚለፍፋቸው ቢሆኑም፤ ለቁጫዎች የተሰጣቸው ምላሽ ግን ሰብዓዊ ክብራቸውን መጣስና ማሰር ነው ያለው አንድነት፤” ፓርቲያችን ይህንን ሕገ-ወጥ ተግባር አጥብቆ ይቃወማል፡፡”ብላል።

የፓርቲው መግለጫ  በመጨረሻም ፦”መንግስት የመብትና ማንነት ጥያቄ ስላነሱ ያሰራቸውን በአስቸኳይ እንዲፈታ፤ ቁጫዎች ያነሷቸውን ጥያቄዎች አግባብ ባለው መንገድ በፍጥነት እንዲመልስ እንጠይቃለን!!!” በማለት ጥሪ አቅርቧል።

ወ/ት ሐዲያ ሙሀመድ ከሳምንታት የእስር ቤት ስቃይ በሁዋላ ተፈታች

$
0
0

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራር የሆነቸው ወ/ት አዲያ አህመድ ከሀምሌ 22 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ  ስቃይ እስር ቤት ውስጥ ከደረሰባት በሁዋላ በዛሬው እለት በዋስ ተፈታለች።

ወ/ት ሐዲያ እንዳለችው መርማሪ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ያዋሉዋት አንድነት ፓርቲ ሀምሌ 28 በሶዶ ከተማ ሊያደርገው የነበረውን ህዝባዊ ስብሰባ በተመለከተ የቅስቀሳ ወረቀቶችን መበተኑዋን ተከትሎ ነው።

ፖሊሶቹ በሀድያ ጉዳይ አንድነትን ከድምጻችን ይሰማ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ ለመወንጀል ቢፈልጉም፣ ሀድያ ባሳየችው ያቋም ጽናት ሳይሳካለቸው ቀርቷል።

መርማሪ ፖሊሶች ” ገልብጠን እንገርፍሻለን፣ አንገትንሽን ጠምዝዘን ገደል እንወረውረዋለን፣ ቀደም ሲል የታሰሩ እስረኞች እንዳወቁበት እወቂ” የሚሉና ሌሎችንም የማስፈራሪያ ቃላት በመጠቀም እነሱ አዘጋጅተው ባመጡት ወረቀት ላይ እንድትፈርም ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ሀድያ ለማስፈራሪያው ልትንበረከክ አለመቻሉን ተናግራለች ( )

በታሰረችበት እስር ቤት መጸዳጃ ቤቱ ሞልቶ በምኝታቸው ላይ ይፈስ እንደነበር የምትለው ሐድያ፣ የወላይታ እስር ቤት የምድር ሲኦል ነው በማለት በእስር ቤቱ ውስጥ ያየችውን በዝርዝር ለኢሳት ተናግራለች። ከወ/ት ሀድያ ሙሀመድ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ ሰሞኑን እናቀርባለን ።

በዚህ አጋጣሚ ወ/ት ሀድያ ወደ ፍርድ ቤት ስትሄድ በመቆያነት ታስራበት የነበረውን ጊዜያዊ እስር ቤት ከፊል ገጽታ በፎቶ በማንሳት ላካፈለን የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽበሺ ከፍተኛ ምስጋናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

በዛሬው ዕለት ታስቦ ከዋለው የመለስ ሙት ዓመት በዓል ጋር በተያያዘ አብዛኛው አገልግሎት ሰጪ የመንግስት መ/ቤቶች ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ዝግ ሆነው ዋሉ፡፡

$
0
0

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በዓሉን አስመልክቶም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሶአል፡፡ የአቶ መለስ ሙት ዓመት ጉለሌ በሚገኘው የዕጽዋት ማዕከል የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣የጎረቤት አገር መሪዎች፣ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብርዋል፡፡ በተለይ የመንግስት ሠራተኞች በግዳጅ   በመስቀል አደባባይ የሻማ ማብራት ስነስርዓት እንዲያካሂዱ መታዘዛቸው ታውቋል፡፡

ይህን ተከትሎም በርካታ ሠራተኞች ዕለቱን እንደዕረፍት በመቁጠር በስራ ገበታቸው ላይ እንዳልተገኙ፣ የተገኙትም መደበኛ ስራቸውን ማከናወን ሳይችሉ እንደቀሩ የጠቆመው ዘጋቢያችን ኃላፊዎችም በዓሉን እያከበሩ በመሆኑ ስራ የሚከታተል ሀላፊ እንዳልነበርም አክሏል፡፡

በተለይ በአዲስአበባ ማዘጋጃ ቤት በሚገኙ የተለያዩ ቢሮዎች በመንግስት ወጪ ከፍተኛ መጠን ያለው ጧፍ ተገዝቶ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሠራተኞቹ ተገኝተው የቀድሞ መሪያቸውን ሙት ዓመት እንዲያስታውሱ መመሪያ ተሰጥቶአቸዋል።

የመንግስት ሐብትና የስራ ሰዓት እየባከነ መሆኑ ገዥዎቻችን ልብ አላሉትም የሚለው አንድ አስተያየት ሰጪ  በአሁኑ ወቅት በመለስ ስም የተለያዩ ንብረቶች እየተገዙ እግረመንገድም  በየቢሮው ምዝበራው እየተጧጧፈ መሆኑ አሳዛኝ ነው ብሎአል።

የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች እና የተለያዩ ህጻናት ሳይቀር በመኪኖች እየተጫኑ ለመለስ ሙት አመት እንዲገኙ መደረጉን  ዘጋቢያችን ከላከው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።

የፌስቡክ መስራች በታዳጊ አገሮች የሚገኙ 5 ቢሊዮን ሰዎችን ለመድረስ አዲስ እቅድ ነደፈ

$
0
0

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣቱ ዙከርበርግ እንደገለጸው ድርጅቱ ከኤሪክሰን፣ ኖክያ፣ ኦፔራ፣ ኳልኮም እና ሳምሰንግ ጋር በመተባበር በሞባይል መረጃ ላይ የሚጠየቀው ክፍያ እንዲቀነስ ያደርጋል።

በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የኢንተርኔት አግልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሚሰራ ዙከርበርግ ተናግሯል።

አንዳንድ ባለሙያዎች በበኩላቸው የአፍሪካውያን ችግር የኔትወርክ እና የሀይል አቅርቦት ችግር መሆኑን በመጥቀስ በዚህ በኩል ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ይመክራሉ።


የሆስኒ ሙባረክ መፈታት ግብጽን እንደገና ሊከፍላት ይችላል ተባለ

$
0
0

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሲኤን ኤን፣ ቢቢሲ እና ሌሎችም ታዋቂ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞችን በማነጋገር እንደዘገቡት የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር መፈታት ግብጽን በድጋሜ ከሁለት ሊከፍላት ይችላል።

አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ሙባረክን ለማውረድ የታገሉ ወጣቶች ምናልባትም ራሳቸውን ከሙስሊም ብራዘርሁድ ጋር በማቀናጀት በስልጣን ላይ ባለው መንግስት ላይ ሊዘምቱ ይችላል። ይሁን እንጅ የሙርሲን መንግስት ከስልጣን በማውረድ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ታምሩድ የሚባለው የወጣቶች ስብስብ፣ ለሆስኒ ሙባረክ መፈታት ተጠያቂው የሙርሲ መንግስት ነው ብሎአል። የሙርሲ መንግስት በሙባረክ ላይ በቂ ማስረጃዎችን ቢያቀርብ ኖሮ ሙባረክ ሊለቀቁ አይችሉም ነበር በማለት የሙባረክን መፈታት ብልጠት በተሞላበት መንገድ ተቀብሎታል።

ሌሎች ተንታኞች በበኩላቸው የግብጽ ወጣቶች አብዮቱ መቀልበሱን በማስታወስ ምናልባትም ለተቃውሞ ወደ አደባባይ ሊወጡ ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የሙባረክ ደጋፊዎች ምናልባትም ለቀድሞው መሪ ያላቸውን ድጋፍ በማሳየት ወደ አደባባይ ሊወጡ ይችላሉ።

ሙባረክ ከእስር የሚፈቱት አገሪቱ ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሳይነሳ ነው።

ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ቢለቀቁም፣ ከአገር መውጣት አይችሉም፡፡   ከሁለት አመት በፊት በተገደሉ ወጣቶች ዙሪያ የቀረበባቸውን ክስ በውጭ ሆነው እንደሚከራከሩ ይጠበቃል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞች የፓርቲ ስራ እንደሰሩ መታዘዛቸውን ተቃወሙ

$
0
0

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንዳንድ ሰራተኞች የኢህአዴግ የ2006 እቅድ መስሪያ ቤቱ ካለበት መደበኛ ስራ ውጪ የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስራ በልዩ ሁኔታ እንዲያስፈፅም ማስገደዱን እየተቃወሙ ነው።አብዛኛዎቹ ሰራተኞች ሚኒስቴሩ በ2006 ዓ.ም ድርጅታዊ ስራን ትኩረት ሰጥቶ እንዲተገብር መድረጉ ሰራተኛው ያለፍላጎቱ የመንግስትንና የድርጅትን ስራ ቀይጦ እንዲሰራ የሚያስገድድ ነው ብለዋል።

ለጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ቅሬታ ያቀረቡት እነዚሁ ሰራተኞች እቅዱን ያለፍላጎታቸው እንዲተገብሩ፤ ካልሆነም የደመወዝ እድገትም ሆነ የደረጃ እድገት የሚያገኙበት ዕድል ዝግ የሚያደርግ መሆኑ ተነግሯቸዋል። ሚኒስቴሩ በሐምሌ ወር 2005 ዓ.ም “የዝግጅት ምዕራፍ ዝክረ ተግባር” በሚል ባለ ስምንት ገፅ እቅድ ላይ በሚኒስቴሩ የድርጅት ስራ ማጠናከር ተገቢ መሆኑን አመልክቷል። በዚሁ እቅድ ውስጥ “ከዚህ ቀደም በነበሩን የሴክተራችን እንቅስቃሴዎች የድርጅት እንቅስቃሴ ጎልቶ የሚታይ ያልነበረ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ በጀት ዘመን ይህ አካሄድ መቀጠል አይኖርበትም። ሴክተራችን የሚመራው መሪ ድርጅታችን ባስቀመጣቸው ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መሆኑ ግልጽ ነው። ሆኖም የነዚህ ተግባራት ተፈፃሚነት ዕውን የሚሆነው ልዩ ልዩ ዘርፎቻችን በውስጣቸው ያለውን የድርጅት እንቅስቃሴ ማጠናከር ሲችሉና አባላትም የሴክተሩን ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማስፈፀም ግንባር ቀደም ሚና መጫወት ሲችሉ ነው። በዚህ በጀት ዘመን በሴክተራችን ይህን ማረጋገጥ ካልተቻለ መሪው ድርጅት በተቋማችን ውስጥ ያለው የመሪነት ሚና እና ውጤታማነቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ ሆኗል። በመሆኑም በዝግጅት ምዕራፍ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ማከናወን እንደ ወሳኝ አቅጣጫ ሊወሰድና ወደ ተግባር ሊለወጥ ይገባል” የሚል ማሳሰቢያ መጨመሩ ታውቋል። የወረዳ አደረጃጀቱን እንደገና ፈትሾ ማጠናከር፣ በተዋረድ የመሰረታዊ ድርጅትና የህዋስ አደረጃጀቶችን ፈትሾ ማጠናከር፣ በሴክተራችን የድርጅት ዘርፍ የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን በጥንቃቄ በጥናት መለየት፣ ክፍተትን ማዕከል ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና ዝግጅት ማከናወን፣ በየደረጃው ለሚገኙ አመራርና የመሪ ድርጅት አባላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት፣ የድርጅት ዘርፍ የጠራ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ ዕቅዱን ማዕከል በማድረግ ለእያንዳንዱ አመራርና አባላት በተዘረዘረ እቅድ የተደገፈ ግልፅ ተልዕኮ መስጠት፣ የአባልነት መለኪያው በዋነኝነት በዘርፉ እቅድ ሁሉም ምዕራፎች ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ ሆኖ መገኘት መሆኑን ማስረፅ፣ ተግባራዊ ማድረግና የክትትልና ድጋፍ አግባብ ዘርግቶ ሂደቱን መከታተልና መደገፍና የመሳሰሉ ተግባራት ለባህልና ቱሪዝም ሰራተኞች የቀረበው ሰነድ ያስረዳል ሲል ሰንደቅ ዘግቧል። ኢህአዴግ በበህርዳር ባደረገው 9ኛ ጉባኤ ላይ የኢህአዴግ አባላት የትግል ቁርጠኝነት እየላላ መምጣቱን በማውሳት የግንባሩን አላማዎች ወደ ተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች ለማውረድ እና ጠንካራ የ5 ለአንድ አደረጃጀት ለመገንባት መወሰኑ ይታወቃል። የመንግስት ሰራተኞች የኢህአዴግ አባላት ካልሆኑ የትምህርት እድል፣ የደሞዝ ጭማሪ ወይም ሌሎች እድገቶችን እንደማያገኙ አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ሳይቀር ሲገልጹ ቆይተዋል።

በኢትዮጵያ የሚታየው የመብራት መጥፋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ

$
0
0

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሳምንታት መብራት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች በማስመልከት ዘገባውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን እንደሚለው በየጊዜው እየሄደ ሳይታሰብ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ሀይል፣ መንግስት ላለፉት 21 ዓመታት ገነባሁት የሚላቸው የሀይል ማመንጫዎች የት እንደደረሱ ጥያቄ የሚፈጥር ነው።

ያለምንም መብራት መቋረጥ አንድ ሳምንት መድፈን ብርቅ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ በተለይ የህክምና መስጫ ተቋማት ከመብራት መጥፋት ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ችግር በአገልግሎት አሰጣጣቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው።

የተለያዩ የኢንዱስትሪ ባለንብረቶች ስራቸውን እስከማቆም መድረሳቸውን የስሚንቶ ፋብሪካዎችን በዋቢነት በመጥቀስ ዘግቧል።

በበጋ ውሀ እጥረት አለ በሚል ሰበብ መብራት ይጠፋል፣ በክረምት ደግሞ የማስተላለፊያ መስመሮች ጉዳት ይደረስባቸዋል በሚል ሰበብ መብራት ይጠፋል፣ በየትኛው ወር መብራት እንደማይጠፋ ለማወቅ አልቻልንም ሲል አንድ የግል ኮሌጅ  ተማሪ ገልጿል።

ኑሮዋን የኮምፒተር ቤት በመክፈት የምትመራ ወጣትም በመብራት መጥፋት የተነሳ ብዙ ጉዳት እንደደረሰባት ገልጻ፣ በአሁኑ ጊዜ የቤት ኪራይ ለመክፈል የማትችልበት ደረጃ ላይ መድረሷን አክላለች።

መንግስት የአገር ውስጥ የሀይል ፍጆታን ሳያሟላ ለጎረቤት አገሮች ሀይል በመሸጥና ለመሸጥም በመደራደር ላይ ነው።

በቡሬ ግንባር በሰራዊቱ የሚደፈሩ ሴቶች ቁጥር ጨምሯል

$
0
0

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሬ ግንባር የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተለያዩ ጊዜያት የአፋር ሴቶችን አስገድደው እንደሚደፍሩ ከስፍራው ደረሰን መረጃ አመለከተ።

የሰራዊቱ አባላት ለቅኝት ወይም ለተለያዩ ስራዎች በሚወጡበት ጊዜ ግመል እና ፍየል የሚጠብቁ ሴቶች ሲያገኙ በሀይል ይድፍራሉ።

ነሀሴ 3 ቀን 2005 ዓም አንዳባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሀሊማ አህመድ የሱፍ የተባለች እድሜዋ ከ45 እስከ 50 የሚጠጋ ሴት በሰራዊቱ አባላት ከተደፈረች በሁዋላ ተገድላ በማግስቱ ተገኝታለች። ዳፋሪዎቹ ወታደሮች ስትጠብቃቸው የነበሩትን 20 ፍየሎች መውሰዳቸውም ታውቋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የመከላከያ ሰራዊቱ እንስሶችን ከመዝረፍ አልፎ ሴቶቻቸውን በሀይል እየደፈሩ መሆናቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአፋር ተወላጆች ላይ የመንግስት ታጣቂዎች እያደረሱ ያለው ስቃይ እየተጠናከረ መምጣቱን የሚያመለክት ነው።

በጉዳዩ ዙሪያ የቡሬን ግንባር አዛዦች ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

በቁጫ የተነሳውን ተቃውሞ አስተባብረዋል የተባሉ 32 ሰዎች ከስራ ተባረሩ

$
0
0

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት የወረዳው ምንጮች እንደገለጹት ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል 2 አቃቢ ህጎች፣ 2 ዳኞች ፣ 1 ፍርድ ቤት ሬስጅስትራርና አንድ ፖሊስ ይገኙበታል። 8 ሰዎች ደግሞ ከስራ ገበታቸው ላይ ለቅቀው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተሰደዋል። የሚታሰሩ ሰዎች እየተበራከቱ መምጣቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ 16 ሰዎች ሰሞኑን ተይዘው ታስረዋል።

ካለፈው ወር ጀምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉት 40 ሰዎች ደግሞ በዛሬው እለት ወላይታ ሶዶ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ፣ ለነሀሴ 22 የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶአቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል።

የወረዳው ችግር እየተባባሰ መምጣቱ ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል በሚል ሰጉ 60 ወረዳው ሽማግሌዎች  ለፌደራል መንግስት አቤት ለማለት በዛሬው እለት ወደ አዲስ አበባ ተጉዘዋል። ባለፉት ወራት ወደ ፌደራል መንግስቱ በመሄድ አቤቱታቸውን ካቀረቡት አገር ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑት ተይዘው መታሰራቸው ይታወቃል። ታዋቂው ባለሀብትና አገር ሽማግሌ ሆኑት መቶ አለቃ ማሴቦ ማዳልጮ፣ ከሶስት ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ከቀበሌ ቀበሌ መረጃዎችን ያስተላልፋሉ ተብለው የተጠረጠሩ 160 ባጃጅ መኪኖችም እስካሁን ከእስር አልተለቀቁም።

ወደ አዲስ አበባ የተጋዙት የአገር ሽማግሌዎች መንግስት ሰራተኞችንና ማፈናቀል፣ ነዋሪዎች ማሰሩን ካላቆመ፣ የወረዳው ህዝብ የራሱን እርምጃ የሚወስድ መሆኑንና በሚፈጠረው ችግር መንግስት ሀላፊነት የሚወስድ መሆኑን ለማሳወቅ ማቀዳቸውን ከምንጮች ለመረዳት ተችሎአል።

አንድነት ፓርቲ ”መንግስት የመብትና ማንነት ጥያቄ ስላነሱ ያሰራቸውን በአስቸኳይ እንዲፈታ፤ ቁጫዎች ያነሷቸውን ጥያቄዎች አግባብ ባለው መንገድ በፍጥነት እንዲመልስ” መጠየቁ ይታወቃል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ሆስኒ ሙባረክ ተፈቱ

$
0
0

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተፈተው በሄሊኮፕተር ወደ ጦሩ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስደዋል፣ ጊዚያዊው መንግስት ከቤታቸው እንደማይወጡ አስታውቋል።

ፕሬዚዳንቱ ከቀረረበባቸው የሙስና ክስ ነጻ በመሆናቸው መፈታታቸው ተገልጿል። ይሁን እንጅ ከሁለት አመት በፊት በግብጽ ከተካሄደው አብዮት ጋር በተያያዘ አሁንም ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል።

ደጋፊዎቸቻቸው ደስታቸውን ቢገልጹም፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ደግሞ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ግብጽ አሁንም በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ብዙ የፖለቲከኛ ተንታኞች ይናገራሉ።

በአማራ ክልል በአንድ ሰምንት ጊዜ ውስጥ በጎርፍ ከ45 ሰዎች በላይ ሞቱ

$
0
0

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው በሚጥለው ከባድ ዝናም የተነሳ በክልሉ በሚገኘው ኦሮሚያ ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 ያላነሱ ሰዎች የተገደሉበትን ክስተት ጨምሮ ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ አንዲት ሚኒ ባስ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት በተደረገ ጥረት የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

በክልሉ እየጣለ ያለው ሀይለኛ ዝናብ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መሆኑን ከክልሉ የሚደረሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በአንዳንድ አካባቢዎች ትራንስፎርመሮች በመቃጠላቸው መብራት ለሳምንታት መቋረጡም ታውቋል።


ሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች -ሰማያዊ ፓርቲን ከፓርቲዎች የትብብር መድረክ አሰናበቱ።

$
0
0

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ33ቱ ፓርቲዎች የትብብር መድረክ -ሰማያዊ ፓርቲን ያሰናበተው፤የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሰሞኑን ለ ሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት ቃለምልልስ የሌሎች ፓርቲዎችን ክብር የነፈገ ነው በሚል ነው።

በዚህም መሰረት ፓርቲዎቹ ባደረጉት ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ ከስብስቡ እንዲወጣ መወሰናቸውን የቪኦኤ ዘገባ ያስረዳል።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው እሁድ በተካሄደ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሆነ  ገልጸዋል።

አቶ ይልቃል ለሰንደቅ በሰጡት ቃለ ምልልስ በዚህች አገር ከሰማያዊ ፓርቲ ውጪ ሌላ ተቃዋሚ ፓርቲ አለ ብለው እንደማያምኑ መገለፃቸው ይታወሳል።

“ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ የሰጡንን ዕውቅና ሳይቀር አቶ ይልቃል ነስተውናል”ያሉት የመኢአድ ፀሀፊ፤ህዝቡ በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ እምነት እንዳያድርበት ደባ ስለፈጸሙ፤ ድርጊታቸውን እንዲያርም ጊዜ ቢሰጣቸውም ሊያርሙ ስላለረቻሉ፤ ይባስ ብለውም ያንኑ ሃሳባቸውን ፡”የኛ ፕሬስ”በተሰኘ ጋዜጣ ላይ በማንፀባረቃቸው እና አቋሙ የ እርሳቸው ብቻ ሳይሆን የፓርቲያቸው ጭምር እንደሆነ በመረጋገጡ ከስብስቡ እንዲሰናበቱ ወስነናል ብለዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል በበኩላቸው “የሰጠሁት አስተያየትና ያንፀባረቅኩት ሃሳብ አዲስ አይደለም፤ እውነትም    ነው”ብለዋል።

እስካሁን ሌሎች ፓርቲዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት እርሳቸውና ፓርቲያቸው እንደሚያደንቁ ለቪኦኤ የተናገሩት አቶ ይልቃል፤ይሁንና ተቃዋሚዎች በአሁኑ ጊዜ የህዝብን የለውጥ ጥያቄ ለመመለስ በሚያስችል ጥንካሬና አቋም ላይ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

“እኔ ስህተተኛ ብሆን ደስታዬ ነበር”ያሉት አቶ ይልቃል፤”እነዚህ ፓርቲዎች ነን እንደሚሉት ቢሆኑ እኔና ጓደኞቼ ሰማያዊ ፓርቲን አፍርሰን ወደየሌሎች ፓርቲዎች እንገባለን፤ወይም ወደየቤታችን እንሄዳለን”ብለዋል።

“ግን እውነቱ ሌላ ነው። የኢትዮጵያን ችግር መጋፈጥ አለብን ካልን እውነቱን ማድበስበስ የለብንም” በማለት ቀደም ሲል በሰጡት አስተያዬት እንደሚያምኑ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን ቤት ለማዳረስ ከ20 ዓመታት በላይ እንደሚፈጅ አንድ ሰነድ አመለከተ

$
0
0

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ረቂቅ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የኮንዶሚየም ቤት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ እንደሚወስድ ጠቆሟል።

አስተዳደሩ ለኮንዶሚየም ቤቶች ብቻ ከ800ሺ በላይ ዜጎችን ቢመዘግብም በቀጣይ አምስት ዓመት ለመስራት ያቀደው 178 ሺ ቤቶችን ብቻ ነው፡፡

አስተዳደሩ ከ2006 እስከ 2010 ዓ.ም ሥራ ላይ አውለዋለሁ ባለው የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የቤቶች ልማትን በተመለከተ የያዘው ዕቅድ እጅግ አነስተኛ ሆኖ መገኘት በየደረጃው ያሉ አባላትና ካድሬዎችን ጭምር አስደንግጦአል፡፡

በአሁኑ ወቅት 20 በ80 በሚባለው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለቤት ለመሆን ከ800ሺ በላይ
ነዋሪዎች ተመዝግበው እየተጠባበቁ ባሉበት ሁኔታ በአምስት ዓመት 178ሺ ቤቶችን ብቻ እገነባለሁ በሚለው ስሌት ሲታሰብ 800ሺ ተመዝጋቢውን ለማዳረስ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ የሚፈጅ መሆኑ ሕዝቡን በከፍተኛ ደረጃ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው ተብሎ ተሰግቶአል፡፡

የቤቶች ልማት ቢሮው ይህን ዕቅድ የያዘው የአስተዳደሩን አቅምና የእስካሁኑን የግንባታ ልምድ ግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡ የኩማ አስተዳደር በአምስት ዓመት ቆይታው 36ሺ700 ከባለአደራ አስተዳደር የተረከበውን ቤቶች ጨምሮ በጠቅላላው በሰልጣን ጊዜው መገንባት የቻለው 175ሺ246 ያህል ቤቶችን ብቻ ነው፡፡

ፕሮግራሙ ከተጀመረ ባለፉት ስምንት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለተጠቃሚዎች የተላለፉ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ብዛት 100 ሺ 559 ያህል ነው፡፡ አዲሱ ዕቅድም ሲሰራም ይህን የመገንባት አቅም ታሳቢ አድርጎ መሆኑን ታውቋል፡፡

ይህ ረቂቅ ዕቅድ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ሰሞኑን በየደረጃው ላሉ
የአስተዳደር አካላት ለውይይት በቀረበበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ አንዳንድ ተሰብሳቢዎች በዚሁ መድረክ ላይ ይህን ዕቅድ ሕዝቡ አይቀበለንም፣ ማሳመንም አንችልም በሚል ተሻሽሎ እንዲቀርብ ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም በአዲሱና አወዛጋቢ በነበረው የሊዝ አዋጅ መሠረት በቀጣይ አምስት ዓመታት በአዲስአበባ ብቻ ካሉ ነባር ባለይዞታዎች ግማሽ ያህሉን ወደሊዝ ሥርዓት ለማስገባት የተያዘው ዕቅድም በተመሳሳይ ሁኔታ በራሱ አመራር አባላት ተቃውሞ ገጥሞታል።

የሊዝ አዋጁ ነባር ይዞታን በተመለከተ ይዞታዎች ሲሸጡ ወደአዲሱ የሊዝ ሥርዓት እየገቡ እንደሚሄዱ ቢደነግግም  አስተዳደሩ በምን መልኩ 50 በመቶ ያህል ነባር ይዞታዎችን ወደሊዝ ሥርዓት
ለማስገባት እንዳቀደ ግልጽ አይደለም ፡፡

የስብሰባው ተካፋዮችም ይህ የሊዝ ጉዳይ አገር አቀፍ ሕግ ሆኖ ሳለ በአዲስአበባ ይጀመር የመባሉ ጉዳይ እና የአፈጻጸሙ ሁኔታ የህዝብን ድጋፍ ያሳጣል በሚል ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡ ይህ የአምስት ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ በቀጣይ ህብረተሰቡ ተወያይቶበት ስራ ላይ ይውላል ተብሎአል፡፡

የቁጫ የአገር ሽማግሌዎች በጠቅላይ ሚ/ሩ ጽህፈት ቤት ተገኙ

$
0
0

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 60 የሚጠጉ የወረዳዋ ሽማግሌዎች በዛሬው እለት ለ7ኛ ጊዜ በጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽሀፈት ቤት ቢገኙም ጠ/ሚኒስትሩን ሊያገኙዋቸው እንዳልቻሉና በተወካያቸው በአቶ ወርቁ በኩል መንግስት ጉዳዩን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳውቃል የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ለኢሳት ገልጸዋል።

በመንግስት መልስ ደስተኞች ያለሆኑት የአገር ሽማግሌዎች፣ እንደገና ተመልሰው ወደ ክልሉ ዋና ከተማ አዋሳ ማቅናታቸው ታውቋል። ሽማግሌዎቹ ለጠ/ሚንስትር ሀይለማርያም ተወካይ ፣ ወደ ቦታችን ስንመለስ እንደማንታሰር ዋስትና ይሰጠን በማለት ቢጠይቁም፣ ተወካዩ የሚያስሩዋችሁ ከሆነ በቀጥታ ደውሉልኝ ብለው ስልካቸውን እንደሰጡዋቸው ገልጸዋል።

የአገር ሽማግሌዎች ወደ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽ/ት ቤት ለመሄድ ያስገደዳቸው በወረዳው የሚታሰረው ሰው ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱና ይህን ተከትሎም ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ አስቀድሞ ለማሳወቅ ነው ብለዋል።

በአካባቢው እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት ፣ በአገሪቱ መንግስት አለ ወይ የሚያስብል መሆኑን ከሽማግሌዎቹ አንዱ ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም ከ90 እስከ 100 የሚደርሱ ሰዎች መታሰራቸውን ሽምግሌዎቹ ይናገራሉ።

መረጃውን ከቀበሌ ቀበሌ በማመላለስ ግጭት እንዲፈጠር ያደርጋሉ የተባሉ 160 ባጃጅ የሚባሉ ተሽከርካሪዎች አሁንም ፖሊስ ጣቢያ ቆመዋል። ከ30 በላይ ሰራተኞችም ተባረዋል።

የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች በቋንቋችን እንጠቀም፣ ሌሎች መብቶቻችን ይከበሩልን የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ይታወቃል።

በሱዳን ከ300 ሺ ህዝብ በላይ በጎርፍ ተጠቃ

$
0
0

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው በያዝነው ወር በጣለው ዝናብ ከ50 በላይ ሰዎች ሞተው፣ ከ300 ሺ ያላነሱት ደግሞ ተፈናቅለዋል።

በተለይ በዋና ከተማዋ ካርቱም ላለፉት 25 አመታት ያልታየ ጎርፍ መታየቱን ድርጅቱ አስታውቋል።

በአገሪቱ ካሉ 18 ግዛቶች መካከል በ14 ላይ ከፍተኛ የንብረት መውደምም ተከስታል።

በባህርዳር የኢህአዴግ አባል ያልሆነና በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ያልተደራጀ ስኳዐር አያገኘም ተባለ

$
0
0

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከባህርዳር የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ ለከተማው ነዋሪዎች አዲስ የአባልነትና አንድ ለአምስት አባልነት መለያ ወረቀት ያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህንን ወረቀት ያላሳየ ሰው በመንግስት የሚከፋፈለውን ስኳር አያገኝም። አንዳንድ ነዋሪዎች ችግራቸውን በኤፍ ኤም ራዲዮ ላይ ቢናገሩም ምንም መፍትሄ እንደሌለው እንዳወቁ ለኢሳት ተናግረዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ህዝብ ግንኙነት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ኢህአዴግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገር ውስጥ ባሉ ተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ እየተደናገጠ መምጣቱ ይነገራል።

Viewing all 2145 articles
Browse latest View live