በመቶዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ
ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ተይዘው በወረዳ 5 ቀበሌ 08/09 በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ የተደረጉ ወጣቶች ዛሬ ጧት ላይ በሶስት አይሲዙ መኪኖች ተጭነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወጣቶቹ በቅርቡ በአዲስ አበባ...
View Articleአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዙበት ሁኔታ ለህይወታቸው አስጊ ነው ተባለ
ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በከፍተኛ ህመም በመሰቃየት ላይ ሲሆኑ እስካሁን በዶክተሮች ለመጎብኘት አልቻሉም። አያያያዛቸው የከፋ መሆኑን በማስመልከት የእንግሊዝ መንግስት አስቸኳይ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ...
View Articleኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች የሚረገጡባት ዜጎች የሚሰደዱባት አስከፊ አገር ሆናለች ተባለ
በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በማካሄድ ላይ ባለው 56ኛው አፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና ህዝቦች መብቶች መደበኛ ጉባኤ ላይ ፣ አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት የተባለው ተቋም ባቀረበው ጽሁፍ ፣ ነጻነትን በማፈን የአለም ሻምፒዮን ከሆኑ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዳ መሆኗን ገልጿል። በኢትዮጵያ የሚባለውና የሚደረገው...
View Articleሼክ አላሙዲን ጋዜጠኞችን ወቀሱ
በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሳውድ አረቢያዊ የሆኑት ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን በሸራተን አዲስ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ በስፍራው የተገኙትን የመንግስት ጋዜጠኞችና አንዳንድ የግል ሚዲያ ሃላፊዎችን ወቅሰዋል። ሼክ አላሙዲን በአሜሪካና በአውሮፓ የደሀ መሬት እየወሰዱ ነው እያሉ ስማችንን የሚያጠፉ ስራፈት...
View Articleበድሬዳዋ በጣለው ድንገተኛ ዝናብ የሰዎች ህይወት አለፈ
ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ በጣለው ድንገተኛ ዝናብ፣ እስካሁን ባለው መረጃ 9 ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል። ሟቾቹ ለገሃሪ እንደገበሬ በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። የ9 ሰዎች አስከሬን ተፈልጎ መገኘቱን ምንጮች ገልጸዋል። ድሬዳዋ ከዚህ ቀደም በደረሰ ጎርፍ በርካታ ነዋሪዎቿን ማጣቷ...
View Articleበአምቦ ተማሪዎች ታሰሩ
በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ፣ አምና በሚያዚያ ወር ከ79 በላይ የኦሮሞ ወጣቶች በአምቦና አካባቢዋ ከተገደሉ በሁዋላ፣ ባለፉት 10 ቀናት ደግሞ 50 የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መያዛቸውን ገልጿል፤፡ ከ20 በላይ ወጣቶች በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸው በአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል...
View Articleየመጪው ምርጫ ተውኔት አስቂኝ ነው ሲል ዘጋቢያችን ገለጸ
በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የኢህአዴግ ካድሬዎች እያደረጉት ያለውን የምርጫ ቅስቀሳና የካርድ እደላ የታዘበው ዘጋቢያችን የምርጫው ሂደት አስቂኝ ሆኗል ብሎአል። በከምሴ፣ ደብረብርሃን፣ ደብደረማርቆስና ሌሎችም ቦታዎች ካርድ ያለወጡ ሰዎች ኢህአዴግን እንደሚመርጡ ካርድ እየተሰጣቸው ነው። በአንድ ለአምስት፣ በአንድ...
View Articleየሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የውሳኔ ቀጠሮ ተራዘመ
በተራዘመ የፍርድ ሄደት የሚሰቃዩት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ፣ የመጨረሻ ብይን ሚያዚያ 30 እንደሚሰጥ አስቀድሞ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ የብይኑ ቀን እንደገና ተራዝሟል። የመራዘሙ ዜና አስቀድሞ በኢሳትና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተዘገበ በመሆኑ፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስገራሚ...
View Articleአስመጪና ላኪዎች በዶላር እጥረት ተማረሩ
በሃገሪቱ የሚታየው ከፍተኛ የዶላር እጥረት አስመጪና ላኪዎችን ማማረሩን ዘጋቢያችን ምንጮቹች ዋቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ የላከው ዜና ያመለክታል። የቡና ኤክስፖርት ከቆመ ወራት ተቆጥረዋል፣ በሃገሪቱ ያሉ ባንኮች ዶላር ሽያጭ አቁመዋል የሚለው ዘጋቢያችን፣ ከዲያስፖራው የሚገኘውን የውጭ ዶላር ገቢ ለማሳደግ ልዩ ልዩ...
View Articleየብሄራዊ ደህንነት መረጃ ሃላፊዎች ጥብቅ ፍተሻ እንዲካሄድ አዘዙ
ሰሞኑን በአዲስ አበባ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ነን ያሉ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣነው በማለት በየክፍለከተማዎችና ወረዳዎች እየዞሩ፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ ለግል ተቋማት ሃላፊዎች፣ ” ማንም ሰው ፣ የመንግስት ባለስልጣናም ሆነ መለዮ ለባሽ ወታደር፣ ፖሊስ ወይም...
View Articleበአማራ ክልል በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የሲሚንቶ እጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ በሲሚንቶ እጥረት ግንባታዎች እንዲቋረጡ መደረጉን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችና በግንባታ ላይ የሚገኙ የህብረተሰቡ ክፍሎች ለዘጋቢያችን አስታውቀዋል፡፡ ችግሩ የህወሃቱ ንብረት በሆነው መሰቦ ስሚንቶና የሼክ አላሙዲን ንብረት በሆነው ደርባን...
View Articleከሰሞኑ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የታሰረ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ተፈረደበት
ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም በተጠራ ሰልፍ ላይ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ስድስትወርእንደተፈረደበት ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ጋዜጣው እንደሚለው ግንቦት 3/2007...
View Articleየተረጋጋ የትምህርት ፖሊሲ አለመኖር ወጣቱን ተስፋአልባ እንዲሆን አድርጎታል ተባለ፡፡
ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅማ ዩኒቨርስቲ ሰሞኑ በተደረገ አውደጥናት ላይ ፣ በየዓመቱ በየጊዜው የሚቀያየረው የትምህርት ፖሊሲ ርእይ ያለው ወጣት እንዳይፈጠር ማድረጉ ተገልጿል ፡፡ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የትምህርት ፖሊሲ ይዛ ባለመማራቷ ችግሩ መፈጠሩንም ምሁራን ተናግረዋል። በሁለተኛ ደረጃ...
View Articleበጋምቤላ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሰዎች ተገደሉ
ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላ እና በደቡብ ክልል አዋሳኝ ከተሞች የሚታየው የጸጥታ ሁኔታ እየተበላሸ መሄዱን ተከትሎ ዜጎች እየተፈናቀሉና እየተገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከሁለት ቀን በፊት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በጎደሬ ወረዳ በየሪ ቀበሌ በፈጸሙት ጥቃት 6...
View Articleለመብራት መቆራረጡ ሰራተኞች ተጣያቂ ተደረጉ
ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ ሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ መብራት እየተቆራረጠ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በህዝቡ ጥያቄ የተወጠሩት የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ሃላፊ ሠራተኞቻቸውን ተጠያቂ አድርገዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የውጭ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ገብረእግዚአብሔር ታፈረ...
View Articleበታሰሩ የፌደራል ፖሊስ ስልኮች ላይ የተገኙት የአቶ አንዳርጋቸውና የመንግስቱ ሃይለማርያም ፎቶዎች መሆናቸው ታወቀ
ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በተወሰኑ የፊደራል ፖሊስ አባላትና እና በማረሚያ ቤቶች ጠባቂዎች ላይ በተካሄደ ድንገተኛ ማጣራት፣ በ18 የፀጥታ አባላት ስልኮች ላይ በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም ፎቶዎች መገኝታቸውን...
View Articleከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አዋሽ አርባ በሚባል ቦታ መታሰራቸው ታወቀ
ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ሳምንታት በውዴታና በግዴታ ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ ወጣቶች አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸውን አምለጠው የመጡ ወጣቶች ለኢሳት ተናግረዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ወጣት “በመጀመሪያ የወረዳው ባለስልጣናት ለስብሰባ...
View Articleሰመጉ በሃመር ወረዳ የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ ያጣራውን ሪፖርት ይፋ አደረገ
ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)፣ በደቡብ ኦሞ ዞን በሐመር ወረዳ ዲመካ ከተማና አካባቢው ከጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ ግጭት በ7 ሰዎች የሞትና በ9 ሰዎች የመቁሰል አደጋ መድረሱን በጥናቱ...
View Articleጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በመጨረሻው የኢህአዴግ ዙር ግምገማ መተቸታቸው
ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችንና የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በሙሉ ሲያስገመግሙ ከከረሙ በሁዋላ በመጨረሻ ራሳቸው 15 ሰአታት በፈጀ ግምገማ ተገምግመዋል። አብዛኞቹ በአቶ ሃይለማርያም የስራ ችሎታና አመራር ላይ ዘለፋ ቀረሽ ሂስ አቅርበውባቸዋል። አቶ ሃይለማሪያም...
View Articleየዜጎች መታፈን ተባብሶ ቀጥሎአል
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ አገዛዙን ይቃወሙ ይሆናል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በገፍ እየተያዙ በመታሰር ላይ ሲሆኑ፣ በርካታ ወጣቶችም ከእስር ለማምለጥ መሸሸጋቸውን ለኢሳት እየገለጹ ነው። በተለያዩ ክልሎች የገዢው ፓርቲ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ ወጣቶች...
View Article