Quantcast
Channel: Amharic
Browsing all 2145 articles
Browse latest View live

ኢህዴድ በሐረርጌ በጨለንቆ ከተማ ያስገነባው የሰማዕታት ሐውልት የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ባልተገኙበት   መመረቁን...

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅዳሜው የሐውልት ምረቃው ላይ ያልተገኙት ጠ/ሚኒስትሩ፣  በማግስቱ በጅማ ከተማ በተካሄደው የስታዲየም ሰልፍ ላይ ተገኝተው ኦህዴድን የሚያወድስ ንግግር ቢያደርጉም እርሳቸውም ሆኑ የህወሃት ባለስልጣናት በሃውልቱ ምርቃት ላይ አልተገኙም። የህወሃት ከፍተኛ...

View Article


በኮንሶ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት 8 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው። ሰዎቹ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንና ዘመዶቻቸው ለፖሊስ አባላት ሄደው በሚያመለክቱበት ወቅት የእነሱ ጉዳይ ከባድ ነው ጠብቁ የሚል መልስ እንደተሰጣቸው...

View Article


የፌደራል ፖሊሶች በግምገማ ተወጥረዋል

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በአዲስ አበባ በተወሰኑ ክፍሎች የሚገኙ የፌደራል ፖሊሶች ተቃዋሚዎችን ይደግፋሉ በሚል መነሻ ጠንካራ ግምገማ እየተካሄደባቸው ነው። የፌደራል ፖሊሶች ፌስ ቡክ እና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ በተለይ በውጭ ከሚኖሩ...

View Article

ኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ግንባታን በየደረጃው የሚቆጣጠረውን ስምምነት ፈረመች

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በጋራ የፈረሙት አዲሱ ስምምነት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ በሙሉ ነጻነት የምትሰራውን ስራ እንደሚገድብ ከአረብኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው  ሰነድ አመልክቷል። ሰነዱ ኢትዮጵያ ግድቡን ለመገንባት በምታደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴና...

View Article

“ኢህአዴግ የህዝቡ ብሶት አደጋ እንደሚያስከትል አውቋል”ስትል የአዲስ አበባ የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ ም/ል ሊቀመንበር ተናገረች

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሊጉ ም/ል ሊቀመንበር በመሆን ለአመታት ያገለገለችው ወ/ት እየሩሳሌም  አበረ  ከኢሳት ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ “የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሚገነፍል ድስት እፍ እፍ እየተባለ  ቢያዝም፣ አሁንም በርካታ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እያነሳ...

View Article


የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክቶች በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፉ እየተደረገ ነው

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መጋቢት 16/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ፣ ከተላኩት የቅስቀሳ መልክቶች መካከል ” የመከላከያ ሰራዊቱ ሌሎችም የአገሪቱ ቁልፍ ተቋማት ከገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ውጪ አልሆነም፣ በተለይም በገዛ ሃገራቸው ከስራ ይባረራሉ ፣...

View Article

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የካሳ ክፍያ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚዘረፍ ኦዲት መስሪያ ቤት አስታወቀ

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባለሰልጣኑ የኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየው በአማራ ክልል የባህርዳር ከተማ፣በምዕራብ ጎጃም ዞን የባህርዳር ዙሪያና የይልማና ዴንሳ ወረዳዎች የጣና- በለስ-ባህርዳር 400 ኪሎቮልት እና የባህርዳር- ደብረማርቆስ 400 ኪ.ቮ. የኃይልማስተላለፊያ...

View Article

ድምጻችን ይሰማ ሳንቲም የመሰብሰብ  ተቃውሞ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ ባለፉት 3 ዓመታት የተካሄደው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ወደ ማእቀብ እና ትብብር የመንፈግ  ሂደት መሸጋገሩን ካስታወቀ በሁዋላ፣  ከመጋቢት 18፣2007 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ላልተወሰነ ጊዜ...

View Article


በኦሮሚያ እና ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ ችግር ት/ቤቶችን ከማዘጋት አልፎ ለስደት እየዳረገ ነው

መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በመቶ ሚሊየን በሚገመት ወጪ በታላቅ ፌሽታ እያከበረ የሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰውን የመጠጥ ውሃ ችግር ሊታደግ ያልቻለ...

View Article


9 ፓርቲዎች የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ በመጪው እሁድ ሊካሄድ ነው

መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት የተሰባሰቡትና ምርጫ ቦርድ ዕውቅና አልሰጠሁም በሚል ትብብራቸውን እንዲያቆሙ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ዘጠኝ ፓርቲዎች በትብብር የጠሩት ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድ የአዲስአበባ እና የድሬዳዋ ከተሞችን ጨምሮ...

View Article

በኦሮምያ ዋና ከተማ የውሃ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከማሃል ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ አካባቢዎች ውሃ ካጡ ረጅም ጊዜ አስቆጥረዋል። ውሃ ጀሪካን በጋሪ ላይ ጭኖ መሄድ ወይም ለውሃ ወረፋ ረጃጅም ሰልፎችን መጠበቅ የእለት ተእለት ክስተት መሆኑን ነዋሪዎች...

View Article

65 ኢትዮጵያውያን በኬንያ ፍርድ ቤት ቀረቡ

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኬንያው  ዘ ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ ወደ አገሪቱ በህገወጥ መንገድ በመግባታቸው እያንዳንዳቸው 2 መቶ ሺ ሽልንግ እንዲከፍሉ የኢሲዮሎ ፍርድ ቤት ወስኖባቸዋል። ሁሉ ም ስደተኞች ባለፈው ሰኞ ሳምቡሩ በተባለው ስፍራ ላይ የተያዙ ሲሆን፣...

View Article

ድምጻችን ይሰማ የጠራው የሳንቲም መሰብሰብ ተቃውሞ  ተጀመረ

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ወደ ማእቀብ እና ትብብር የመንፈግ  ሂደት መሸጋገሩን ድምጻችን ይሰማ ካስታወቀ በሁዋላ፣ አርብ መጋቢት 20 የሳንቲም መሰብሰቡ ሂደት ተጀምሯል። ምን ያክል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ እያደረጉት መሆኑን...

View Article


የፊታችን እሁድ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ  በአዲስ አበባ በጥሩ ሁኔታ ሲካሄድ በክልሎች እንቅፋት እየጋጠመው ነው

መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ9 የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር መጋቢት 20 በአዲስ አበባና በ15 የክልል ከተሞች የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የትብብሩና የሰማያዊ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ለኢሳት ተናግረዋል። ኢ/ር ይልቃል በግብርናና ገጠር ልማት ዙሪያ...

View Article

የበርገን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ የሳውል ፍሬዎች የሚል ፊልም አስመረቀ

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በርገን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ አማካኝነት የተሰራው የሳውል ፍሬዎች በፈረንጆች አቆጣጠር ማርች 28 በበርገን ኖርዌይ ከተማ ተመርቋል። በአይንሸት ገበያው  ተደርሶ በጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን አርታኢነትና አዘጋጅነት...

View Article


እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ፍርድ ቤት ቀረቡ

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቁጥጥር ስር የዋሉትእና በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ...

View Article

ኦብነግ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ምርትን ወደ ውጭ መላክ የማይታሰብ ነው አለ

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር -ኦብነግ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር በበሁለት አመት ውስጥ ኦጋዴን  ያለውን የተፈጥሮ ጋዝ ለውጭ ገበያ እናቀርባለን በማለት የሰጡት መግለጫ፣  ያልተጨበጠና የማይሆን ነው ብሎአል። መንግስት በኦጋዴን ውሰጥ...

View Article


በጋምቤላ ሌላ ዙር የጎሳ ግጭት አንዣቧል ሲሉ የጋምቤላ ኒሎትስ አንድነት ንቅናቄ አደራጅ ተናገሩ

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው መስራችና አደራጅ   ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት የህዝባዊ ወያን ሃርነት ትግራይ መንግስት በአካባቢው ያለውን መሬት ሙሉ በሙሉ ጠቅልሎ ለመውሰድ ባለው ፍላጎት በአኝዋኮችና በኑወር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ነው።...

View Article

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዋጋ ቤትፈላጊዎችን አስመርሯል

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመጪውን ምርጫ መቃረብ ተከትሎ በአዲስአበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ 32ሺ ያህል ብዛት ያለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከሳምንት በፊት ቢወጣም ቅድሚያ ክፍያው የዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም በላይ ሆኗል። የኮንዶሚኒየም  ቤቶች ዋጋ...

View Article

ፖሊሶች በግድግዳ ላይ የሚጻፉ ጽሁፎችን ተከታትለው እንዲያጠፉ ታዘዙ

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በግድግዳዎች ላይ ተጽፈው የሚገኙ የተለያዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች በአስቸኳይ እንዲጠፉ  የደህንነትና ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ትእዛዝ ሰጥቷል። ፖሊሶቹ በግድግዳ ላይ የተጻፉ የነፃነትና የፍትህ ጥያቄዎችን...

View Article
Browsing all 2145 articles
Browse latest View live