የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ጸደቀ
ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ከተሞች ሥር የሰደደውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል የተባለ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ፡፡ አዋጁ በተበታተነና በልማዊ መንገድ ሲካሄድ የነበረውን የመሬት ባለቤትነት ይዞታ አሰራርን በዘመናዊ መልኩ እንዲካሄድ...
View Articleበሶማሊያ ክልል 47 ሰዎች መገደላቸውን የአገር ሽማግሌዎች ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በላኩት ደብዳቤ ገለጹ
ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀላፎ አካባቢ የሚኖሩ የየረር ባሬ ጎሳ የአገር ሽማግሌዎች ለጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ያስገቡትና መረጃው ለኢሳት እንዲደርስ በሚል በላኩት መረጃ ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር እና ጄኔራል አብርሀም በቅጽል ስማቸው ኳታር የሚመራው ልዩ...
View Articleየደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር እስካሁን ውጤት አላሳየም
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት እና በአማጽያን መካከል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው ድርድር እንደቀጠለ ቢሆንም፣ ሁለቱም ሀይሎች በሚያቀርቡዋቸው ቅድመ ሁኔታዎች እስካሁን ውጤት አለመገኘቱ ታወቀ። አማጽያኑ የታሰሩት ባልደረቦቻቸው እንዲፈቱ፣ የዩጋንዳ ጦር አገሪቱን ለቆ እንዲወጣና የታወጀው...
View Articleበደቡብ ክልል 60 አቃቢ ህጎች ከስራ መባረራቸው ተሰማ
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቃቢ ህጎቹ ከስነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ መባረራቸው ተግልጿል። የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች እንደገለጹት ከ100 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ የተለያዩ የዲሲፒሊን እርምጃዎችን ወስደዋል። ከ40 በላይ በሚሆኑ የእስር ቤቶች ሃላፊዎች ላይም እንዲሁ የዲሲፒሊን እርምጃ...
View Articleየአማራ ክልል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ይኖራቸል ብለው የሚጠረጥሩትን ሁሉ እንዲይዙ ታዘዙ
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ወር በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር የተካሄደውን የብአዴን እና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የዞን እና የወረዳ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ኢህአዴግ አሸባሪ እያለ ከሚጠራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በቀጥታም ሆነ...
View Articleየሩዋ ፈለግ ቀበሌ ነዋሪዎች ለሁለተኛ ቀን ከፖሊሶች ጋር ተፋጠዋል
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጽቢ ወንበርታ ወረዳ በሩሃ ቀበሌ ከመስኖ ግድብ ጋር በተያያዘ ሃሙስ እለት የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ እስከ አርብ ምሽት የቆየ ሲሆን፣ የወረዳው የአስተዳደር ሰራተኞች እና የደህንነት ሀይሎች አመጹን የቀሰቀሱት እነማን ናቸው አውጡ በማለት ከህዝቡ ጋር እየተወዛገቡ...
View Articleበዩክሬን የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ያንኮቪች መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን በተመለከተ ያወጣው አዲስ ህግ ያስቆጣቸው ዜጎች ወደ አደባባይ በመውጣት ከፖሊሶች ጋር እየተጋጩ ነው። መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን ለመገደብ ያወጣው አዲሱ ህግ በሌሎች የአውሮፓ አገራት ሳይቀር ተወግዟል። ተቃዋሚዎች...
View Articleበደቡብ ሱዳን ጦርነቱ ቀጥሏል
ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በአዲስ አበባ ሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ለማስማማት ውይይት ቢጀመርም፣ በመሬት ላይ እየተደረገ ያለውን ጦርነት ለማስቆም አልተቻለም። በዩጋንዳ መንግስት የሚደገፈው የመንግስት ጦር ቦር እየተባለ የሚጠራውን ስትራቴጂክ ከተማ...
View Articleመንግስት የቻይና ኩባንያዎች ላቀረቡት አቤቱታ መልስ ሰጠ
ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ብድር የሚሰጡ 2 ባንኮችን ጨምሮ 17 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት ስራዎችን ለተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ብቻ እየሰጡ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተከትሎ ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር መልስ መስጠቱን...
View Articleየደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለአገር ወይስ ለፖለቲካ ስርአቱ ነው የሚል ጥያቄ አነሱ
ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ ”የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ...
View Articleየደቡብ ሱዳን መሪ ተመድን ወቀሱ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ላይ ወቀሳቸውን የሰነዘሩት ድርጅቱ ራሱን እንደ ሁለተኛ መንግስት በመቁጥር የጦር መሳሪያዎችንና አማጽያንን አስጠልሏል በማለት ነው። ፕ/ር ሳልቫኪር የተመድ ዋና ጸሀፊ አገሪቱን ማስተዳደር የሚፈልጉ ከሆነ በግልጽ...
View Articleአዲሱ የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመት በግል ጋዜጦች ላይ ለሚወሰደው እርምጃ አመላካች ነው ተባለ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አቶ ዘርዓይ አስገዶምየኢትዮጵኢያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው መንግስት ከምርጫ 2007 በፊት በፕሬሱ ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ጠንካራ አስፈጻሚ...
View Articleበምስራቅ ሃረርጌ ከ59 ሰዎች በላይ መገደላቸውን የኦሮሞ ጥናት ማህበር አስታወቀ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ኢሌሞ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ጥቂት ወራት በአንያ፣ ማቶ እና ሙለቄ ቆላማ ወረዳዎች ላይ በፌደራል መንግስቱ እውቅና የተቋቋመውና ስልጠና የሚሰጠው ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩት ሃይሎች በኦሮሞዎች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት...
View Articleከሱዳን ጋር የሚደረገው የድንበር ውዝግብ የሞራልና የሶሻል ጥያቄ እንጅ የህግ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት...
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ ይህን የተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የደህንነት ሰራተኞች በተገኙበት በተደረገው ግምገማና ውይይት ላይ ነው። በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር የማካለል እንቅስቃሴ ከ1965 ዓም ጀምሮ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩት...
View Articleየኢትዮጵያ መንግስት ግብጽ ወደ አለማቀፉ ማህበረሰብ ለመሄድ ማሰቡዋን አጣጣለው
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጽ ባለስልጣናት የአባይን ግድብ በተመለከተ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር ሲያደርጉት የነበረውን ድርድር ካቋረጡ በሁዋላ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች ለጋሽ አጋራት ለመውሰድ መወሰናቸውን የግብጽ ባለስልጣኖች መናገራቸውን ተከትሎ ግብጽ...
View Articleበመንግስት ተቋማት ላይ ሙስና መስፋፋቱ ተነገረ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከለጋሽ አገሮች ባገኘው ድጋፍ ተመስርቶ የውጭ ባለሀብቶችን በማሳተፍ ባስደረገው ጥናት የመንግስት ግዢዎችና ኮንትራቶች ግልጽነት የጎደላቸው መሆናቸውን አረጋግጧል። የውጭ ባለሀብቶች አራት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ሙሰኞች ብለው እንደፈረጁዋቸው...
View Articleአወዛጋቢው ሱዳናዊ ባለሀብት የአማራን ክልል ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አባይ ወንዘን ተንተርሶ በሱዳናዊው ባለሀብት የተቋቋመው የስጋ ፣ የዶሮ፣ የዘይት፣ የአትክልትና ፍራፍሮ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ላለፋት አምስት ዓመታት የተወራለትን ያህል ማምረት እና ማሰራጨት ባለመቻሉ የክልሉ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቤሮ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ...
View Articleፈቃድ ከወሰዱ የውጭ ባለሃብቶች ብዙዎቹ ወደስራ አለመግባታቸው መንግስትን አስደነገጠ
ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ባለፉት 15 ዓመታት ከኤጀንሲው ፈቃድ የወሰዱ 6ሺህ 500 ፕሮጀክቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ ወደሥራ ባለመግባታቸው የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸውን ለመሰረዝ መወሰኑ ታወቀ፡፡ በዚሁ መሠረት 2 ሺህ...
View Articleበግብጽ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት መጣሱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ
ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ የሙባረክን መንግስት ያስወገደችበት 3ኛ አመት ለማክበር በምትዘጋጅበት ወቅት ነው አምነስቲ መግለጫውን ያወጣው። የሙባረክን መንግስት ከተወገደ በሁዋላ አገሪቱ ልትረጋጋ አለመቻሉዋን የገለጸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ በተለይም የሙርሲ መንግስት በወታደራዊ...
View Articleየአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ250 በላይ ሰዎችን አሰረ
ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎቹ የተሳሩት በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለከተሞች በመኪና ስርቆት፣ ማጅራት በመምታትና ሌሎች ወንጀሎች መፈጸማቸውን ጥናት ካካሄድኩ በሁዋላ ነው ብሎአል። ተያዙ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ፍድር ቤት ስለመቅረባቸው ኮሚሽኑ ያስታወቀው ነገር የለም።...
View Article