ኢህአዴግ ለግንቦት7 የድርድር ጥያቄ አቀረበ
ህዳር ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደገለጹት ኢህአዴግ የእንደራደር ጥያቄውን በሁሉት ወር ጊዜ ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ ማቅረቡ ነው። ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢሳት ላቀረበው ጥያቄ በሰጠው የጽሁፍ መልስ “የእንደራደር” ጥያቄ እንደቀረበለት አምኖ፣...
View Articleበዱራሜ ከተማ በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎዱ
ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በከንባታ ጠንባሮ ዞን በዱራሜ ከተማ ገበያ ላይ በተነሳው ተቃውሞ አንድ ታዳጊ ሲገደል ሁለት ፖሊሶች ደግሞ ቆስለዋል። በርካታ ገበያተኞችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ግጭቱ የደረሰው የከተማው ግብር ሰብሳቢዎች አነስተኛ ነጋዴዎች ቡና መሸጥ እንዲያቆሙ...
View Articleበጅጅጋ የሚታየው ስረአት አልባነት ተባብሷል
ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ በማንኛውም ሰአት ዜጎች ቤታቸው በጸጥታ ሀይሎች ይፈታሻል። የጸጥታ ሀይሎችም ከሞባይል ስልክ ጀምሮ እስከ ላፕቶፕ እንዲሁም ገንዘብ ይወስዳሉ። የቀበሌ መታወቂያዎችን ሳይዙ ከሄዱ ደግሞ ተጠርጥረው ይያዛሉ። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጅጅጋ ለኢትዮጵያውያን...
View Articleኢህአዴግ ለግንቦት7 ያቀረበው የእንደራደር ጥያቄ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው
ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች በስልክ እየሰጡ ባለው አስተያየት ግንቦት7 ከኢህአዴግ ጋር መነጋገሩን አይደግፉም። አብዛኞቹ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ “ኢህአዴግ ተዳክሟል፣ ኢህአዴግ የሚታመን ድርጅት አይደለም” የሚሉ ናቸው። በዚህ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን...
View Articleበመርካቶ በደረሰ ቃጠሎ መጠኑ ያልታወቀ ንብረት ወደመ
ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦንብ ተራና እና ጆንያ ተራ የሚባሉት አካባቢዎች ዛሬ ቀን ላይ በከፍተኛ የእሳት አደጋ የተጠቁ ሲሆን የከተማዋ የእሳት አደጋ በጊዜው ባለመድረሱም በነዋሪዎች ከፍኛ ተወቅሷል። የመስተዳድሩ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግኑኝነት ሰራተኛ አቶ ንጋቱ ማሞ በ10...
View Articleበኢትዮጵያ የሚታየው የግብር አሰባሰብና ሙስና ህዝቡን እያስመረረ ነው
ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በደብረማርቆስ ከተማ ተደርጎ በነበረው የህዝብ ስብሰባ ላይ ነርካታ ነጋዴዎች በታክስ መማረራቸውን ገልጸዋል። መቶ አለቃ ስመኝ መኩሪያው እንዳሉት መንግስትን አክብረን በቫት ብንገባም በአንድ አነስተኛ የንግድ ሱቅ በየወሩ እስከ 73 ሺ ብር ተጠይቀን ፤...
View Articleሳውድ አረቢያ የውጭ ዜጎችን ማስወጣቱዋን እንደምትቀጥል አስታወቀች
ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ወር ጀምሮ ህጋዊ ወረቀት የላቸውም በሚል የውጭ ዜጎችን ማባረር የቀጠለችው ሳውድ አረቢያ፣ ከአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ትችት ቢደርስባትም፣ ዜጎችን ማስወጣት እንደምትቀጥል አስታውቃለች። አረብ ኒውስ እስካሁን በተወሰደው እርምጃ 126 ሺ ሰዎች...
View Articleበላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ወረዳ አንድ አውቶቡስ ተገልብጦ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአደጋው 40 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስኤም ከአቅም በላይ ጭነት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። በጭልጋ ወረዳ ደግሞ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪና ተገልብጦ ተሽከርካሪዎች ለመተላላፍ ባለማቻላቸው መቸገራቸውን...
View Articleመንግስት ለቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አባላት የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር እንቅስቃሴ መጀመሩ ታወቀ
ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ተሀድሶ አልወሰዱም በሚሉና በተለያዩ ሰበቦች የጡረታ መብታቸው ላልተከበረላቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት፣ የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል። የመንግስት ሹሞች የቀድሞ ወተዳሮቹን ፎርም...
View Articleየመርካቶ ነጋዴዎች በእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ክስ ሊመሰርቱ ነው
ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመርካቶ በተለምዶ ጆንያ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ከቀትር በኃላ የደረሰውን የእሳት አደጋ በወቅቱ ከመቆጣጠር ይልቅ ጉቦ ለማግኘት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በድርድር ጊዜ በማጥፋታቸው ንብረታችንን እንድናጣ አድርጎናል ያሉ ነጋዴዎች የአዲስአበባ ከተማ...
View Articleጅጅጋ በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ስር ናት
ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በሚል የጅጅጋ ከተማ በፌደራል ፖሊስ አባላት መወረሯን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማውን ከተቆጣጠሩት በሁዋላ ልዩ ፖሊስ እየተባሉ የሚጠሩት ሀይሎችን ወደ ዳር የገፉዋቸው ሲሆን፣ ፖሊሶቹ በየተወሰኑ...
View Articleከሳውድ አረቢያ ከሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የመንግስት እንቅስቃሴ እየተተቸ ነው
ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከሳዑዲዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ቁጥሩ መንግስት አስቀድሞ ካሰበው እጅግ አሻቅቧል፡፡ በዚህ ም ምክንያት ተመላሾቹን ለመቀበልና ለማቋቋም መንግስት በቂ በጀት አለመያዙ...
View Articleበ2006 ዓ.ም ከስድስት ሚልየን በላይ ህፃናት ትምህርት አቋረጡ
ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅድመ መደበኛ ት/ቤት ገብተው መማር ከሚገባቸው እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ሀፃናት ውስጥ 23 በመቶዎቹ ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው ሰነድ ያስረዳል። ከ1ኛ አስከ 4ኛ ክፍል ድረስ የትምህርት ገበታቸው ላይ የተገኙ ተማሪዎች...
View Articleበቦንጋ መምህራን አድማ ሊጠሩ ነው
ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ መምህራን ፣ መንግስት ለአባይ ግድብ በማለት ያለፈቃዳቸው የቆረጠባቸውን ደሞዝ በአስቸኳይ ካልመለሰ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። መምህራኑ ዛሬ ወርሀዊ ደሞዛቸውን ለመቀበል ወደ ባንክ ሲሄዱ ለአባይ ግድብ በሚል...
View Articleየቁጫ ነዋሪዎች መኖር አልቻልንም ሲሉ ምሬታቸውን ገለጹ
ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ መፍቴ አጥቶ እንደቀጠለ ባለበት ወቅት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የአነጋግረናቸው የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል። በዛሬው እለት በርካታ የአገር ሽማግሌዎች የጸጥታ ሀይሎች...
View Articleበማንዴላ ሞት አለም ሀዘኑን እየገለጸ ነው
ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ደቡብ አፍሪካውያን ለነፃነት አባታቸውና ለቀድሞ መሪያቸው ለኔልሰን ማንዴላ ሀዘናቸውን ለመግለጽ ወደ ጁሀንስበርግበና ሶዌቶ እየተሰበሰቡ ሲሆን፤ ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ታዋቂ ሰዎችም በማንዴላ ሞት ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን በስዌቶ...
View Articleየቁጫ የአገር ሽማግሌዎች የዋስትና መብት ተከለከሉ
ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛው ፍርድ ቤት ታስረው ከተለቀቁ በሁዋላ ተመልሰው እንዲታሰሩ የተደረጉት የቁጫ ወረዳ የአገር ሽማግሌዎች፣ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ተመልሰው በአርባምንጭ እስር ቤት እንዲታሰሩ መደረጉን ከሽማግሌዎች አንዱ ገልጸዋል። ችግሩን ለፌደራል መንግስት አቤት ለማለት...
View Articleየሶማሊ ክልል ለመከላከያ አዛዦች አዛዦች የመክበሪያ ቦታ መሆኗን ምንጮች አስታወቁ
ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ ከፍተኛ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የህወሀት ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች ወደ ሶማሊ ክልል ሲመዱ ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ከፍተኛ ሀብት አጋብሰው እንደሚመለሱ ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ ተቀማጭነታቸው ጅጅጋ የሆኑት እና...
View Articleታላቁን የአፍሪካ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ የሚዘክር ዝግጅት ተካሄደ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአለማችን ታላላቅ መሪዎች፣ እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በዚህ ዝግጅት የማንዴላ የትግል ጉዜ ተዘክሯል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ይህን ታላቅ የታሪክ ሰው ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፤ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን አሳሪዎችንም ነጻ ያወጣ፣ሀሳብን ወደ ተግባር...
View Articleበቼክ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚፈጸመውን ጥቃት ተቃወሙ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት በላኩት መረጃ ሰኞ እለት ፕራግ በሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በጩኸትና የተለያዩ መፈክሮችን በመጠቀም አውግዘዋል። ያዘጋጁትን የተቃውሞ ደብዳቤ ለኢምባሲው ተወካይ ማስረከባቸውንም አክለው ገልጸዋል።
View Article