የግብፅ ልዑካን ቡድን በአባይ ግድብ ዙሪያ ከሱዳን ጋር ለመምከር ካርቱም ገባ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2 ፣ 2008 ዓም) በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል በአባይ ግድብ ዙሪያ ሊካሄድ የነበረው ድርድር መዘግየትን ተከትሎ፣ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ከሱዳን ጋር የሚመክር የልዑካን ቡድን ወደ ሃገሪቱ ላኩ። በሃገሪቱ የመስኖ ልማት ሚኒስትር ሆሳም ሞግሃዚ የተመራው ይኸው ልዩ የልዑካን ቡድን፣...
View Articleህወሃት ያገለላቸውን የቀድሞ አባላቱን እየመለሰ ነው ተባለ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2 ፣ 2015) የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት ) ማእከላዊ ኮሚቴ ከአመታት በፊት በጡረታ የተገለሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች በድጋሚ እንዲደራጁ አዘዘ። ባለፈው እሁድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመቀሌ ከተማ ጉባኤ ያካሄደው የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ፣ በትጥቅ ትግሉ ወቅት እንዲሁም...
View Articleበፍቼ ከተማ ባጃጅ አሽከርካሪዎች የስራማቆም አድማ አደረጉ
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በፍቼ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት መስሪያ ቤትስራችንን በአግባቡ ሊያሰራን አልቻለም በሚል ምክንያት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከትናንት ጀምረው የስራማቆም አድማ አድርገዋል። የከተማው መንገድ ትራንስፖርት ባጃጅ ለመንዳት የታክሲ አንድ ፈቃድ መያዝ...
View Articleበአቶ ሃብታሙ አያሌው መዝገብ የተከሰሱት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች በድጋሜ ተቀጠሩ
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሰው በ19ኛው ወንጀል ችሎት ነጻ የተባሉት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሃብታሙ አያሌው፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ም/ል ሰብሳቢ የነበረው የሽዋስ አሰፋ፣ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ም/ል ስብሳቢና የደቡብ ተወካይ የነበረው...
View Articleበማላዊ በተለያዩ እስርቤቶች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በደል እየተፈፀመባቸው ነው
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በማላ ዊ የድንበር ጠባቂዎች የተያዙ ከ317 በላይ ኢትጵያዊያን ስደተኞች በተለያዩ እስርቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው መሆኑን አጃን ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። የማላዊ ፍርድ ቤት በስደተኞች ላይ...
View Articleበሲዳማ ዞን በተነሳ ግጭት ጉዳት እየደረሰ ነው
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ ፣ ወታራና ጉጉማ በሚባሉ አካባቢዎች ከ2004 ዓም ጀምሮ በእየአመቱ የሚቀሰቀሰው ግጭት ሰሞኑን አገርሽቶ፣ እስካሁን 2 ሰዎች በከባድ ሁኔታ ተጎድተው አዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሲገቡ፣ መጠኑ ያልታወቀ ንብረትም ወድሟል። በቦንኬ...
View Articleበኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተነሳው ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው እሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያውያንና በሱዳን መንግስት ወታደሮች መካከል የተነሳው ጦርነት መቀጠሉን ከአካባቢው የደረሱን መረጃዎች ያመለካታሉ።ኢትዮጵያውያን ታጣቂዎች፣ ከዚህ ቀደም ማንነታቸው ያልታወቁ የሱዳን ታጣቂዎች 8 ኢትዮጵያውያንን ለሹፌርነት እንቀጥራችሁዋለን...
View Articleየአለማቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች መንግስት በድርቅ ለተጎዱት ዜጎቹ በቂ ገንዘብ እንዲመድብ ጠየቁ
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚገኙ 8 ሚሊዮን 200 ሺ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚሹ፣ በከተማ ውስጥ የሚኖሩ 4 ሚሊዮን ተረጅዎች እንዳሉ በመንግስት እና በአለማቀፍ ድርጅቶች ይፋ ከሆነ በሁዋላ፣ የአለማቀፍ ድርጅቶች መንግስት ለልማት በሚል የመደበውን...
View Articleየኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች በፈጠሩት ችግሮች የኦሞና የቱርካና ሃይቅ የመድረቅ አደጋ ከፊታቸው ተጋርጧል ተባለ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙት የቱርካና ሃይቅና የኦሞ ወንዝ ኢትዮጵያ በምትከተለው የኢንዱስትሪ ዘመቻ ምክንያት የመድረቅ እና የአየር ንብረት መዛባት አደጋን ማስከተሉንና በዚህም ለውጥ ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ሂውማንራይትስ ወች በጥናት...
View Articleየኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ፥ ESFNA ቶሮንቶን በአዘጋጅነት መረጠ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ፥ ESFNA በካናዳ የቶሮንቶን ከተማ የ2016 የስፖርት ክብረ በዓል ዓስተናጋጅ እንድትሆን መርጧል። ውሳኔው የተላለፈው፥ በኢትዮ-ስታር ቶሮንቶ የእግር ኳስ ክለብ ዓስተባባሪነት በቶሮንቶ ካናዳ በተዘጋጀው፥ የESFNA ዓመታዊ...
View Articleበሰሜን ጎንደር የአርባ ፀጓር ፀባሪያ ነዋሪዎች ባለፉት ሃያ አራት ዓመታ ውስጥ ብአዴን ምንም እንዳልሰራላቸው ተናገሩ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተከዜ ወንዝ ጫፍ ላይ የምትኘውና የዋግና የበለሳ ነዋሪዎች መተላለፊያ የሆነችው አርባ ፀጓር ወረዳ ደርግን ለመጣል በተደረገው የትግል ወቅት የኢህአፓና የኢሕዲን መተላለፊያ መስመር የነበረች ሲሆን በወቅቱ የድሮው ኢሕዲን የአሁኑ ብአዴን ታጋዮች የነበሩት ለሕዝቡ የኑሮ...
View Articleበሁመራ ከ500 በላይ የሞተር አሽከርካሪዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞተር ሳይክል ሰዎችን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ህይወታቸውን የሚመሩ 500 ያክል ወጣቶች ስራ እንዲያቆሙ በመታዘዛቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል። ሰራተኞቹ በድንገት አቁሙ በመባላቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ተቸግረዋል። መንግስት አማራጭ ስራ ሳይፈጥር...
View Articleመንግስት ለመከላከያ ሰራዊት ምዝገባ አዲስ ቅስቀሳ ጀመረ
ጥቅምት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው አመት ጀምሮ እንደ አዲስ በተጀመረው የሰራዊት ምልመላ የተፈለገውን የሰራዊት ቁጥር ማግኘት የተቸገረው መንግስት፣ ሰሞኑን ደግሞ በአንዳንድ ክልሎች የመከላከያ ሰራዊት አባላት በመኪና ላይ ሆነው ወጣቱ ለውትድርና እንደሚዘገብ በመቀስቀስ ላይ ናቸው። ከዚህ ቀደም...
View Articleቻይናዎች በኢትዮጵያውያን ላይ የመብት ጥሰት እየፈጸሙ እንደሆነ ታወቀ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 4 ፣ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች ላይ የሚፈጽመው በደል ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፌደሬሽን ገለጠ። በኢትዮጵያዊያን ሊሰሩ የሚችሉ ቀላል ስራዎች በውጪ አገር ዜጎች እየተሰሩ እንደሚገኙ...
View Articleዞን 9 ጦማሪያን በነጻ እንዲሰናበቱ ፍርድቤት ወሰነ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 5፡ 2008) የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድቤት በሽብርተኛ ወንጀል ክስ፣ የክስ ሂደታቸው በመታየት ላይ የነበሩ አራት ጦማሪያን ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ዛሬ አርብ ወሰነ። በጦማሪያኑ ላይ የመጀመሪያ ዙር ውሳኔውን ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀው ፍርድ ቤቱ...
View Articleየአምባሳደር ዘውዴ ረታ የቀብር ሥነስርዓት በቅድስት ስላሴ በተክርስቲያን ተፈጸመ
ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ፣ዲፕሎማትና የታሪክ ተመራማሪ የነበሩት የቀድሞ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ባለፈው ሳምንት እንግሊዝ ለንደን ውስጥ መንገድ ላይ በመውደቃቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። አምባሳደር ዘውዴ በአዲስ አበባ ከተማ ነሐሴ 7ቀን 1927 ዓ.ም...
View Articleየኔዘርላንድስ ፖሊስ አንድ በቀይ ሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ኢትዮጵያዊን አሰረ
ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማንነታቸው ያልተገለጸው የ61 አመቱ ኢትዮጵያዊ አምሰተልፊን በምትባል ከተማ ውስጥ የተያዙ ሲሆን፣ ግለሰቡን ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ ወይም አይመለሱ የሚልውን ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ የ90 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። ግለሰቡ በደብረማርቆስና መተከል አውራጃዎች በርካታ...
View Articleበሽብርተኝነት ሕግ ተከሰው አንድ ዓመት ከአምስት ወራት በእስር ሲንገላቱ የቆዩት የዞን ፱ ጦማሪያን በነጻ ተሰናበቱ
ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንደኛ ተከሳሽ ሶሊያና ሽመልስ በሌለችበት፣ሶስተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ ፣ አምስተኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔ፣ስድስተኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላ፣ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ የተሰናበቱ ሲሆን፣ ሁለተኛ ተከሳሽ በፍቃዱ ኃይሉ ከሽብር ክስ ነፃ የተባለ ቢሆንም ማአከላዊ...
View Articleየኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የዋጋ ንረቱን እያባባሰው ነው ተባለ
ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ የሚታየው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ ለታየው አጠቃላይ የዋጋ ንረት መባባስ አንድ ምክንያት መሆኑን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ አንድ የጥናት ሰነድ ጠቆመ፡፡ በምግብ ነክ ምርቶች ላይ ማለትም በምግብ ዘይት፣ ዱቄት፣ ፓስታና...
View Articleከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የዲጂታል ሸግግር በሙስና ምክንያት በታቀደው መሰረት ሳይሳካ ቀረ
ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ለሚደረግ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ቢደረግም አልተሳካም። ፕሮጀክቱ በ2001 ዓም ተጀምሮ በ3 አመታት ውስጥ መጠናቀቅ ነበረበት። ከብሮድካስት ባለስልጣን...
View Article