Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

አንድነት ፓርቲ ተቃውሞውን በሁሉም የአገሪቱ ክፍል እንደሚያቀጣጥል ገለጸ

$
0
0

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በባህርዳር ለታየው ህዝባዊ ተቃውሞ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ባለመሆኑ ተቃውሞውን በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ለመቀጠል ፍላጎት ያለው መሆኑን አመልክቷል።

አቶ አለምነው መኮንንን በፍርድ አደባባይ ለማቆም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክስ መስርቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

አቶ አለምነው በአማራው ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ጸያፍ ስድብ ተከትሎ በባህርዳር ልዩ የተባለ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ይታወቃል። ብአዴን እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠም።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles