Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

ርእዮት አለሙ ምግብ ካቆመች 4ኛ ቀናትን ደፈነች

$
0
0

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እውቋ የብእር ሰው፣ የነጻነት ታጋይ፣ የዩኒስኮና የኢንተርናሽናል ውሜንስ  ሚዲያ ፋውንዴሽን አሸናፊ ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ ዛሬም በረሀብ አድማው ገፍታበታለች። እህቷ እስከዳር አለሙ እንደገለጸችው ዛሬ እርሷና የርእዮት እጮኛ የሆነው ስለሺ ሀጎስ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ቢሄዱም እንዳይገቡ ተከልክለዋል።

እጮኛዋ ስለሺ ለሰአታት ታግቶ በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች መደብደቡንም እስከዳር ተናግራለች  ርእዮት ከእናት፣ አበቷና የንስሀ አባታ በስተቀር ሌላ ሰው እንዳይጠይቃት በመደረጓ የረሀብ አድማውን መጀመሩዋ ይታወቃል።

በአለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በርእዮት ላይ የሚደርሰውን የመብት አፈና እየተቃወሙ ነው።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles