Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

በሊቢያ ሚስቱንና የሶስት ወር ልጁን ትቶ የደረሰበት ያልታወቀው ሰው ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቀለ

$
0
0

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ ቤንጋዚ የሚኖር አንድ ሙስሊም  ኢትዮጵያዊ በጦርነት መሃል አልፎ ከ3 ወር ልጇ ጋር ለሶስት ቀናት ቤት ዘግታ የተቀመጠቸውን ኢትዮጵያዊት ማዳኑን ኢሳት በልዩ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ፣ ባልየው ከ4 ቀን በሁዋላ ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል።

በቀሌ አስፋው የተባለው ኢትዮጵያ ወደ ሊቢያ የሄደው በቅርብ ሲሆን፣ የሊቢያ ፖሊሶች መንገድ ላይ በድንገት እንደያዙት ገልጿል። ከተያዘ በሁዋላ  ስሙን ወደማያውቀው እስር ቤት መወሰዱን ገልጿል። ወደ ሊቢያ ለምን መጣህ ተብሎ መጠየቁንና መደብደቡን የገለጸው በቀለ፣ ከአራት ቀን በሁዋላ የልጁን ናፍቆት መቋቋም ባለመቻሉ ከገደሉኝም ይግደሉኝ ብሎ ከእስር ቤት ዘሎ ማምለጡንና በሰላም ከቤተሰቡ መገናኘቱን ገልጿል። ከ15 እስከ 20 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ተናግሯል።

ከኦሮምያ ክልል መምጣቱን የሚናገረው ኢትዮጵያዊ ፣ ቤተሰቡንና ልጆቹን ላተረፈለት ኢትዮጵያዊው ስደተኛ ምስጋናውን ገልጿል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles