Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

በመጪው  የጥምቀት በዓል ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርቶችን  መልበስ አትችሉም ተባሉ፤ 

$
0
0

ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቲሸርቶቹ ላይ የሚያሳትሟቸውን ሀይማኖታዊ  ጥቅሶችም  በራሳቸው መምረጥ እንደማይችሉ ተነገሩ። ድርጊቱ  የግል የማመን መብታችንን የሚጋፋ ከመገሆኑም በላይ ሀይማኖታችንንም መድፈር ነው ያሉ ወጣቶች ቁጣቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

ፖሊሶች ከትናት ታህሳስ 1 ቀን ጀምሮ በ አዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች በመንቀሳቀስ ወጣቶች  ለመጪው የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሰማያዊ-ቲሸርት መልበስ እንደማይችሉ፣ እንዲሁም በቲሸርቶቻቸው ላይ የሚያሳትሟቸውን ሀይማኖታዊ ጥቅሶች  ፓሊሶች  እስከሚነግሯቸው ድረስ በራሳቸው ፍላጎት ማጻፍ እንደማይችሉ  በመቀስቀስ ላይ መሆናቸውን የቀበና፣ የምኒልክና የፈረንሳይ ሌጋሲዮን ወጣቶች ለኢሳት ገለጹ። ወጣቶቹ ሰማያዊ ቀለም ያለው ቲ-ሸርት መልበስ አትችሉም የተባሉበት ምክንያት በግልጽ ባይነገራቸውም፤ ጉዳዩ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ግምታቸውን ተናግረዋል።

መቶ መቶ ብር በማዋጣት ለበዓሉ የምንለብሰውን ቲሸርት እያሰራን በምንገኙበት  ወቅት  መንግስት  የምንለብሰውን ቲ-ሸርትና በቲሸርታችን ላይ የምናጽፈውን ጥቅስ እኔ ነኝ የምመርጥላችሁ ማለቱ ዓይን ያወጣ አምባገነንነት ብቻ ሳይሆን ለምእመናን  ያለውን ንቀትም ጭምር  የሚያሳይ ነው ብለዋል-ወጣቶቹ። ፖሊሶች ከትናንት ጀምሮ  ቅስቀሳ እያደረጉ ቢሆንም፤  የየሰፈሩ ወጣቶች ሊቀበሏቸው አልቻሉም። ይልቁንም  በፖሊሶቹ ቅስቀሳ የተበሳጩ  ወጣቶች  ቁጣቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ሂጃብ መልበስ በመከልከሉ በርካታ ሙስሊሞች ተቃውሟቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ይታወቃል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles