Quantcast
Channel: Amharic
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

የስዊድን ከፍተኛ አቃቢ ህግ በ13 የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ምርምራ በማድረግ ላይ ነው

$
0
0

ታኀሳስ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-አንድ ከፍተኛ አቃቢ ህግ ለስዊድን ሬዲዮ እንደገለጹት ምርጫ 97ትን ተከትሎ በህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ ጦር ለተገደሉ ንጹህ ዜጎች ተጠያቂዎች ናቸው የተባሉ 12 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና አንድ ስዊድን አገር በሚገኝ ሌላ ወታደራዊ አዛዥ ላይ ምርመራ  እየተካሄደ ነው።

ማስረጃዎች ተሰባስበው እንዳለቁ ክስ ሊመሰረት እንደሚችል የገለጹት አቃቢ ህጓ ፣ባለስልጣናቱ በየትኛውም አገራት ቢዘዋወሩ ተይዘው ለፍርድ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል።

ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት የስዊድን አቃቢ ህግ በጉዳዩ ላይ ምርምራ መጀመሩ፣ለቀረበው አቤቱታ ትኩረት መስጠቱን ያመለክታል።ኢትዮጵያውያን አሁንም www.ethdfr.com በሚለው የዌብሳይት አድራሻ በመግባት መረጃዎችን መስጠት ይችላሉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2145

Trending Articles